2015 (እ.አ.አ)
ለአዳኝ ጊዜ ስጡ
ዲሴምበር 2015


የቀዳሚ አመራ መልእክት፣ ታህሳስ 2015 (እ.አ.አ)

ለአዳኝ ጊዜ ስጡ

ሌላ የገና ዘመን እና ከዚህም ጋር የአዲስ አመት መጀመሪያ እየደረሰብን ነው። የአዳኝን ልደት እያከበርን እና ለአዲስ አመቱ ውሳኔዎች እያደረግን ያነበረበት ጊዜ ትላንትና እንደነበረ ይመስላል።

በዚህ አመት ካሉን ውሳኔዎች መካከል፣ ለአዳኝ በህይወታችን ውስጥ ጊዜ ለመስጠት እና በልባችን ውስጥ ክፍል ለመስጠት ውሳኔ አድርገናልን? በእንደዚህ አይነት ውሳኔ ምንም ያህል ውጤታማ ብንሆንም፣ ሁላችንም የተሻለ ለማድረግ ምኞት እንዳለን እርግጠኛ ነኝ። ይሄ የገና ወቅት ጥረታችንን ለመመርመር እና ለማደስ መልካም የሆነ ጊዜ ነው።

በስራ በተጠመደ ህይወታችን ውስጥ፣ ትኩረታችንን ለማግኘት ብዙ ነገሮች እየተወዳደሩ በሚገኙበት፣ ክርስቶስን ወደ ህይወታችን እና ወደ ቤታችን ለማምጣት የህሊና እና የልብ ውሳኔ ጥረት ማድረጋችን አስፈላጊ ነው። እናም ከምስራቅ እንደመጡት አዋቂ ሰዎች፣ እኛም በእርሱ ኮኮብ ላይ ማተኮራችን እና እርሱን ለማምለክ1 መምጣታችን አስፈላጊ ነው።

በትውልድ ዘመናት በሙሉ፣ ከኢየሱስ የመጣው መልእክት ሁሌም አንድ ነው። ለጴጥሮስ እና ለአንድርያስ በገሊላ ባህር ዳር አጠገብ፣ በኋላዬ ኑ” አላቸው።2 ለፊልጶስም ይህ ጥሪ መጣ ተከተለኝ።3 በመቅረጫው ተቀምጦ ለነበረው ለሌዋውያንም ይህ መመሪያ መጣ፣ ተከተለኝ።4 እናም ለእናንተ እና እኔም፣ የምናዳምጥ ከሆንን፣ የሚጠራ አንድ አይነት ግብዣ ይመጣል፥ ተከተሉኝ።5

ዛሬ የእርሱ የእግር ኮቴን ስንከተል እና የእርሱን ምሳሌ ስንከተል፣ የሌሎችን ህይወት ለመባረክ እድሎች ይኖሩናል። ኢየሱስ እራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይጋብዘናል፥ እነሆ፣ ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል።6

በዚህ ገና አገልግሎት ልትሰጡት የሚገባችሁ ሰው አለን? ጉብኝታችሁን የሚጠብቅ ሰው አለ?

ከብዙ አመት በፊት ባለቤታቸው ወደሞተባቸው ሸምገል ወዳሉ ሴት ቤት ለገና ጉብኝት ሄድኩኝ። በዚያ እያለሁም፣ በሩ ተንኳኳ። በበሩ ፊትም በስራ የተጣመደ እና ታዋቂ ዶክተር ነበር። አልተጠራም ነበር፤ ግን፣ ብቸኛ የሆኑትን የእርሱን ታካሚ ለመጎብኘት መነሳሳት ተሰምቶት ነበር።

በዚህ በበዓል ዘመን፣ ከቤት ለመውጣት የማይችሉ ሰዎች የገና ጉብኝት ለማግኘት ይጓጓሉ። በአንድ ገና፣ የታመሙትን የሚንከባከቡበት ቦታ እየጎበኘሁ እያለሁ፣ ከአምስት አሮጊት ሴቶች ጋር ተቀምጬ እነጋገር ነበር፣ ከእነርሱም በእድሜ ከፍተኛዋ 101 አመታቸው ነበር። እርሳቸውም አይነ ስውር ነበሩ፣ ግን ድምጼን አውቀውት ነበር።

ኤጲስ ቆጶስ፣ በዚህ አመት ትንሽ ዘግይተሀል አሉኝ። የምትመጣም አልመሰለኝም ነበር።

ደስተኛ ጊዜ አብረን አሳለፍን። አንድ በሽተኛ ግን ወደ ውጪ በመስኮት በጉጉት እየተመለከቱ ልጄ ዛሬ ሊያየኝ እንደሚመጣ አውቃለሁ በማለት ይደጋግሙ ነበር። መምጣቱ አሳሰበኝ፣ ምክንያቱም ያልመጣበት ያለፉ የገና ዘመናት ነበሩና።

በዚህ አመት የእርዳታ እጆችን፣ የሚያፈቅር ልብን፣ እና ፈቃደኛ የሆነ መንፈስ የመዘርጋት ጊዜ አለ - በሌላ አባባልም፣ በአዳኛችን የተሰጠንን ምሳሌ ለመከተል እና እርሱ እንድናገለግል እንደሚፈልገን ለማገልገል። እርሱን ስናገለግል፣ የጥንት የሆቴል ቤት ጠባቂው እንዳደረገው፣7 በህይወታችን ውስጥ ለእርሱ ጊዜ ለመስጠት እና በልባችን ውስጥ ለእርሱ ክፍል ለመስጠት ያለንን እድል አንጥልም።

በሜዳ ለነበሩት እረኞች መልአክ በሰጠው መልእክት ውስጥ ያለውን አስደናቂ የተስፋ ቃል ልንረዳ እንችላለን፥ ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ። መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።8

በገና ስጦታዎችን ስንሰጥና ስንቀበል፣ ከሁሉም ስጦታዎች ሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ስጦታ-የዘለአለም ህይወት ይኖረን ዘንድ የአዳኛችን እና የቤዛችንን ስጦታን እናስታውስ፣ እንውደድ፣ እናም እንቀበል።

ለሰው ስጦታ ቢሰጠው እና ስጦታውን ባይቀበለው ምን ይጠቅመዋል? እነሆ፣ በተሰጠው አይደሰትም፣ ወይም በስጦታ ሰጪውም አይደሰትም።9

እርሱን እንከተል፣ እርሱን እናገልግል፣ እርሱን እናክብር፣ እናም በህይወታችን የእርሱን ስጦታ እንቀበል፣ ይህንን የምናደርገውም በአባት ሌሂ ቃላት በእርሱ ዘለዓለማዊው ፍቅር ክንዶች እንድንከበብ ዘንድ ነው።10

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘደንት ሞንሰን ክርስቶስን ወደ ህይወታችን እና ወደ ቤታችን ለማምጣት የህሊና እና የልብ ውሳኔ ጥረት እንድናደርግ ጠርተውናል። ከምታስተምሯቸው ጋር ይህን የህሊና ጥረት እንደግለሰብ እና እንደ ቤተሰብ ለማድረግ እንዴት እንደሚችሉ ለመወያየት አስቡበት። በዚህ ገና ለመጎብኘት ወይም ለማገልገል የሚችሉትን አንድ ሰው ወይም ቤተሰብ እንዲያስቡበት ለመጠየቅ አስቡ። በዚህ አመት የእርዳታ እጆችን፣ የሚያፈቅር ልብን፣ እና ፈቃደኛ የሆነ መንፈስ የመዘርጋት ጊዜ አለ።

አትም