ወጣቶች
የምስክርነቴ መሰረት
ደራሲዋ በአይደሆ፣ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።
የ16 አመት ልጅ እያለሁ፣ ጓደኛዬ ከምስዮኖች ጋር ወደ ቤታችን መጣ። የመጀመሪያው ውይይት ከሆነው በወር ውስጥ፣ ጥያቄዊቼ ሁሉ በግልፅ ተመልሰውልኝ ነበር። በዳግም ስለተመለሰው ወንጌል መልእክቶች ሙሉ እውነትነት መንፈስ ቅዱስ እንደመሰከረልኝ ተሰማኝ። ከዚ በፊት ተሰምቶኝ ከነበረው የተለየ ነበር፣ እናም ሁሉም ነገሩ እውነት እንደነበሩ አውቄ ነበር።
ቢሆንም፣ ከዚ በፊት ከነበረው የበለጠ ተቃውሞ እና ተቃርኖ አጋጠመኝ። ብቻዬን የሆንኩ፣ የደከምኩ፣ እናም ግራ የገባኝ ያህል ተሰማኝ። ትክክለኛውን ነገር እያደረኩ ቢሆን ኖሮ፣ ለምን ነው ብዙ መከራ ያጋጥምኝ የነበረው? መከራዎቼ ለእኔ ጥቅም እንዴት እንደነበሩ ሊገባኝ አልቻለም ነበር። ምስዮናዊያኖቹ በትምህርት ቀን መሀከል ላይ ቢሆንም፣ እንድፆም እና እንድፀልይ አስተማሩኝ። ነገሮች መሸከም ከሚቻለው በላይ ሲደርሱ ከልቤ ሁሉ ነገር አወጣለሁ እናም ወዲያው የመንፈስ መፅናናት ይሰማኛል።
የጥምቀቴ ሳምንት በመከራዎች የተሞላ ነበር። አለቃዬ ጥምቀቴን ዘልዬ የአንድ ሰውን ቦታ ተክቼ ካልሰራሁ እንደሚያባረኝ አስፈራራኝ፣ በኩላሊት ጠጠር ምክንያት ሆስፒታል ገባሁ፣ እናም ወላጆቼ ቤታችንን ለቅቄ እንድሄድ ጠየቁኝ። ብዙ ነገሮች ከቁጥጥሬ ውጪ በሆኑበት ጊዜ፣ ማድረግ የምችለው አንድ ነገር ወደ ጌታ መመለስ ነበር።
እያንዳንዱ እነዚያ መከራዎች ለእኔ ጥቅም ሆነው ተገኙ። እነርሱ ስለወንጌል ትምህርቶች እንርማር ረዱን፣ ይህም ለምስክሬ የምስክርነቴ መሰረት አዘጋጀልኝ።