2016 (እ.አ.አ)
በአየር ነውጥ ውስጥ በሰላም ማረፍ
ፌብሩወሪ 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የካቲት 2016 (እ.ኤ.አ)

በአየር ነውጥ ውስጥ በሰላም ማረፍ

ምስል
በፕሬዘደንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ

እሩቅ ባልሆነ ጊዜ በፊት፣ እኔ እና ባለቤቴ፣ ሀሪየት፣ አየር ማረፊያ ሆነን የሚገርመውን አውሮፕላን ሲያርፍ እንመለከት ነበር። ንፋሳማ ቀን ነበር፣ እናም ሀይለኛ ንፋስ ሊያርፍ ያለ እያንዳንዱ አውሮፕላንን እያወዛወዘ አቅጣጫ እንዲቀይሩ እና እንዲንቀጠቀጡ ያደርግ ነበር።

በተፈጥሮ እና በማሽኑ መካከል ያልውን ግብ ግብ እየተመለከትን ሳለን፣ አእምሮዬ የራሴ የበረራ ስልጠና እና እዛ ወደ ተማርኩት መርሆች እንዲሁም ከዛ በኋላ ሌሎች አብራሪዎችን በስልጠና ወደ አስተማርኳቸው ወደ ኋላ ተመለሰ።

በአየረሩ ነውጥ ጊዜ ከፍሬኑ ጋር አትታገሉ፣” ብዬ እነግራቸው ነበረ። ተረጋግታችሁ ቆዩ፤ ቶሎ አትወስኑ። አይናችሁን ከማረፍያው መስመር መሃል ላይ እንዳትነቅሉ። ለመሄድ ከምትፈልጉት መንገድ ከከወጣችሁ፣ የፍጥነት ግን በጥንቃቄ የተመዘነ እርምታ አድርጉ። የአውሮፕላናችሁ አቅም ላይ እመኑ። ከአየር ነውጡ በመፅናት ውጡ።

ልምድ ያላቸው አብራሪዎች በዙሪያቸው የሚከሰቱት ነገሮች ላይ ሁሌም ቁጥጥር እንደሌላቸው ይረዳሉ። የአየር ነውጡን በቀላሉ ማጥፋት አይችሉም። ዝናብን ወይም የበረዶ ዝናብን ማጥፋት አይችሉም። ንፋሱ መንፈሱን እንዲያቆም ማድረግ ወይም አቅጣጫውን ማስቀየር አይችሉም።

ነገር ግን አውሎ ንፋስን ወይም ጠንካራ ንፋስን መፍራት—እንዲሁም በእነሱ ሽባ መሆን ስህተት እንደሆነም ይረዳሉ። ሁኔታዎች ከሀሳብ ያልዘለሉ ሲሆኑ በትክክለኛው መስመር ላይ መቆየት እና በመንደርደሪያው ላይ በተቻለ መጠን እንከን የለሽ ሆኖ መቆየት በሰላም የማረፊያ መንገድ ነው።

አንዱ ከዛ ሌላኛው አውሮፕላን ተራ በተራ ሲያርፉ ስመለከት እና አብራሪ በነበርኩበት አመታት የተማርኳቸውን መርሆዎች ሳስታውስ ሳለሁ፣ በዚህ ውስጥ ለቀን ተቀን ህይወታችን የሚሆን ትምህርት ይኖር ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ።

ህይወት በመንገዳችን ላይ የሚያስቀምጠውን ማእበሎች ሁሌም መቆጣጠር አንችልም። እንዳንዴ ነገሮች በቀላሉ አይሳኩልንም። በጥርጣሬ፣ ፍራቻ፣ ሀዘን፣ ወይም ጭንቀት የተወዘወዝን እና የተመታን መስሎ ሊሰማን ይችላል።

በነዚህ ወቅቶች፣ መልካም እየሄዱ ባልሆኑ ነገሮች ሁሉ መጨነቅ እና ችግሮቻችንን የአስተሳሰቦቻችን ማዕከል ማድረግ ቀላል ነው። ፈተናው በአዳኝ እና የእውነት ምስክር ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በምንጋፈጣቸው ፈተናዎች ላይ ማድረጋችን ነው።

ነገር ግን በህይወታችን ሙሉ ባሉት መከራዎች በማለፍ ለመጓዝ ያ ትክክለኛው መንገድ አይደለም።

ልክ ልምድ ያለው አብራሪ ትኩረቱን በመዐበሉ ላይ እንደማያደርገው ነገር ግን የመንደርደሪያውን እና ትክክለኛውን የማረፊያ ነጥብ መዐከል ላይ እንደሚያደርገው ፣ እንዲሁም እኛም ትኩረታችንን በእምነታችን ማዕከል ላይ፣ በአዳኛችን ላይ፣ በእርሱ ወንጌል ላይ፣ እናም በሰማይ አባታችን እቅድ ላይ እነዲሁም ወደ ሰማያዊ እጣ ፈንታ በሰላም የመመለስ ወደ ሆነው የመጨረሻ ግባችን ላይ ማድረግ አለብን። በእግዚአብሄር መተማመንን እና በደቀመዛሙረትነት መንገድ ላይ መቆየትን የጥረቶቻችን ትኩረት ማድረግ አለብን። አይኖቻችንን፣ ልባችንን፣ እናም አእምሮአችንን መኖር እንዳለብን የምናውቀውን ኑሮ መኖር ከመኖር ላይ ማንሳት የለብንም።

እምነታችንን ማሳየት እናም በደስታ ትዛዛቶቹን በመጠበቅ የሰማይ አባትን መተማመን ደስታን እና ክብርን ያመጣልናል። በመንገዱ ላይ ከቆየን፣ ምንም ያህል ጠንካራ መስሎ ቢታይም ነውጥን እንወጣዋለን እናም ወደ ሰማያዊ ቤታችን በሰላም እንመለሳለን።

በዙሪያችን ያሉ ሰማዮች የጠሩ ይሁኑም ወይም በሚያስፈራሩ ደመናዎች የተሞሉ፣ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንደመሆናችን መጠን፣ ያንን ካደረግን፣ የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ ቀስ በቀስ እንደሚዘጋጁ በማወቅ፣ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን መንግስት እና ፅድቁን እንሻለን (የማትዮስ ወንጌል 6፥33)።

ምን አይነት የሚጠቅም የህይወት ትምህርት ነው!

ችግሮቻችን ላይ አጥብቆ የምናሰላስል ከሆንን፣ ትግሎቻችን፣ ጥርጣሬዎቻችን፣ እናም ፍራቻዎቻችን የበለጠ አስቸጋሪ ነገሮች ይሆናሉ። ነግር ግን በመጨረሻው ሰማያዊ መድረሻ እና እግዚአብሔርን በመውደድ፣ ባልንጀሮቻችንን በማገልገል የደቀመዝሙር መንገድን የመከተል ደስታ ላይ የበለጠ ካተኮርን — በድካም እና በነውጥ ውስጥ በውጤታማነት የመጓዝ ችሎታ ይኖረናል።

የተወደዳችሁ ጓደኞች፣ የሟች ኑሮአችን ንፋሶች ሁከት በዙሪያችን ምንም ያህል ቢጮኅም፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሁሌም በሰማይ አባት መንግስት ውስጥ በሰላም ለማረፈፍ የተሻለ መንገድ ያቀርባል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ “በእግዚአብሔርን መተማመን እና በደቀመዛሙረትነት መንገድ ላይ መቆየትን የጥረቶቻችን ትኩረት እንድናደርግ” መክረውናል። የምታስተምሯቸውን ሰዎች አንዳንዴ መከራዎችን ሲጋፈጡ “ በሰማያው የመጨረሻ መድረሻችን እና የደቀመዛሙርት መንገድን በመከተል የሚመጡትን ደስታዎች ላይ” እነርሱ እንዴት እንደሚያተኩሩ ለመጠየቅ አስቡበት። በአስቸጋሪ ወቅቶች በምስክርነታቸው ላይ እና በክርስቶስ ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ እና አንዱን ወይም ሌሎቹን ሀሳብ በህይወቶቻቸው ውስጥ በተግባር ለማዋል የሚችሉበትን መንገዶች እንዲያስቡ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ።

አትም