2016 (እ.አ.አ)
ጋብቻ በእግዚአብሔር የተሰጠ ነው።
ፌብሩወሪ 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ የካቲት 2016 (እ.ኤ.አ)

ጋብቻ በእግዚአብሔር የተሰጠ ነው

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር አዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከትዋቸውን ሰዎች ባርኳቸው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

ነብያት፣ ሀዋሪያት እና መሪዎች በወንድ እና በሴት መካከል ያለ ጋብቻ የእግዚአብሔር ስርዓት እንደሆነ እና ቤተሰብም የፈጣሪ እቅድ ዋና ክፍል እንደሆነ በክብር በማወጅ” ቀጥለዋል።1

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዲህ ብለዋል፥ በወንድ እና በሴት ላይ የተገነባ ጋብቻ ያለ ቤተሰብ የእግዚአብሔር እቅድ እንዲበዛ የተሻለ መዋቅርን ያቀርባል። 

እኛም ቢሆን ማንኛውም ሟች አካል ይህንን መለኮታዊ የሆነ የጋብቻ ስነ ስርዓት መለወጥ አይችልም።2

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዘደንት የሆኑት ቦኒኤ ኤል. ኦስካርሰን፣ እንዲህ ብለዋል፥ ሁሉም ሰው፣ የትዳር ሁኔታቸው ወይም የልጆቻቸው ቁጥር ብዛት ምንም ቢሆንም፣ በቤተሰብ አዋጅ ውስጥ የተገለፀውን የጌታን እቅድ ተከላካዮች መሆን ይችላሉ። የጌታ እቅድ ከሆነ፣ የኛም እቅድ መሆን አለበት!3

ሽማግሌ ክርስቶፈርሰን ንግግራቸውን ቀጥለውም፥ አንዳንዶቻችሁ ለማግባት የምትችሏቸውን በማጣት፣ በአንዳንድ አይነት ጾታ ጋር በመማረክ፣ አካላው ወይም አእምሮአዊ መጋረዶች፣ ወይም በቀላሉ የውድቀት ፈራቻን በሚያጠቃልሉ ምክንያቶች የጋብቻ በረከትን ተከልክላችኋል። ወይም አግብታችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን ያ ጋብቻ አብቅቶለታል። አንዳንዶቻችሁ ያገባችሁ እና ልጅ መውለድ የማትችሉ ናችሁ። 

ይህ ቢሆንም፣ ሁሉም ሰው በትውልዱ በሚገለጠው መለኮታዊ እቅድ ላይ መሳተፍ ይችላል።4

ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች

ዘፍጥረት 2፥18 – 24፤; 1 ቆሮንጦስ 11፥11፤ ; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥15 – 17

ህያው የሆኑ ታሪኮች

በወጣት ወንዶች አጠቃላይ አመራራር ሁለተኛ አማካሪ የነበሩት፣ ወንድም ሌሪ ኤም. ጊብሰ፣ አሁን ሚስታቸው የሆኑት፣ ሸርሊይ እነዲህ ስሉ አስታውሰዋል፥

እወድካለሁ ምክንይቱም እኔን ከምትወደው የበለጠ ጌታን እንደምትወድ ስለማውቅ። 

ያ መልስ በልቤ ውስጥ ቀረ። 

[እናም] ከሁሉም ነገር በላይ ጌታን እንደምወድ ሁሌም እንዲሰማት እፈልጋለሁ።5

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አባል ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር እንዲህ ብለው አስተማሩ፥ በቃልኪዳን ጋብቻ ግንኙነት ውስጥ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ዋና ክፍል ነው። [አስቡት] አዳኝ ያለው የሶስት መዐዘን የላይኛው ጫፍ ነው፣ ከታች አነዱ ማዐዘን ስር ሴት አለች እንዲሁም ወንዱ ደሞ በሌላኛው የማዐዘን ስር በመሆን። አሁን ለየብቻቸው እና ደረጃ በደረጃ ‘ወደ ክርስቶስ ሲመጡ’ እና ‘በእሱ ፍፁም ለመሆን ሲጥሩ’ በሴትዋ እና በወንዱ መካከል ያለው ግንኙነት ምን እንደሚከሰት አስቡ።(ሞሮኒ 10፥32)። በእሱ እንዲሁም በአዳኝ ምክንያት፣ ወንዱ እና ሴትዋ በአንድነት ይቀራረባሉ።”6

ማስታወሻዎች

  1. ቤተሰብ፥ ለአለም አማጅ፣ Liahona፣ ህዳር 2010፣ 129።

  2. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ Why Marriage, Why Family, Liahona, ግንቦት 2015፣ 52።

  3. ቦኒኤ ኤል. ኦስካርሰን፣ Defenders of the Family Proclamation፣ Liahona, ግንቦት 2015፣ 15።

  4. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ Why Marriage, Why Family፣ 52።

  5. ሌሪ ኤም፣ ጊብሰን፣ Fulfilling Our Eternal Destiny፣ Ensign,የካቲት 2015፣ 21–22።

  6. ዴቪድ ኤ. ቤድናር Marriage Is Essential to His Eternal Plan፣”Liahona፣ሰኔ 2006፣ 54።

ይህን አስቡበት

በግሌ እና ደረጃ በደረጃ ‘ወደ ክርስቶስ ለመምጣት’ ምን ያክል ጥርት እያረኩ ነው?

አትም