2016 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር ምስል መፈጠር
ማርች 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ መጋቢት 2016 (እ.አ.አ)

በእግዚአብሔር ምስል መፈጠር

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅን መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከትዋቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

“ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ …

“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍጥረት 1፥26–27)።

እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን ነው፣ እናም እኛን በመልኩ ነው የፈጠረን። ስለዚህ እውነት ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ አሉ፥ “አባታችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን የሚያዳምጥበት ጆሮዎች አሉት። ስራችንን የሚመለከትበት አይኖች አሉት። እኛን የሚያነጋግርበት አፍ አለው። ርህራሄ እና ፍቅርን የሚሰማበት ልብ አለው። እውነተኛ ነው። ህያው ነው። በመልኩ የተፈጠርን ልጆቹ ነን። እርሱን እንመስላለን እናም እርሱም እኛን ይመስላል።”1

“የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሰዎችን በሙሉ በሙሉ እና በፍጹም አስተያየት እንደ እግዚአብሔር ልጆች ይመለከታሉ፤ እያንዳንዱ ሰው ከመጡበት፣ በፍጥረት፣ እና በችሎታቸው መለኮታዊ እንደሆኑ ይመለከቷቸዋል።”2 እያንዳንዱ “የሰማይ ወላጆች ተወዳጅ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጅ” ናቸው።3

“[ነቢዩ] ጆሴፍ ስሚዝ እርሱ የተቀበለው አይነት ዘለአለማዊ ህይወት ልጆቹ እንዲቀበሉ እግዚአብሔር እንደሚፈልግ ተምሮም ነበር።”4 እግዚአብሔር እንዳለው፣ “እነሆ፣ ይህም ስራዬ እና ግርማዬ ነው - ለሰው ሟች አለመሆንን እና የዘለአለም ህይወት ለማምጣት” (ሙሴ 1፥39)።

ተጨማሪ ቅዱስ መጻህፍት

ዘፍጥረት 1፥26–27፤ 1 ቆሮንቶስ 3፥17፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥1

ከቅዱሳት መጻህፍት

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የያሬድ ወንድም ያሬዳውያንን በውሀ ተሻግረው ወደ ቃል ኪዳን ምድር ተሸክመው ለመውሰድ የተሰሩትን ስምንት መርከቦች ብርሀን የሚያገኝበትን መንገድ ይፈልግ ነበር። እርሱም “ከአለት አቅልጦ አስራ ስድስት ትናንሽ ድንጋዮች አደረገ” እናም እግዚአብሔር “በጨለማም እንዲያበሩ” በጣቱ “እንዲነካቸው” ጸለየ። እና እግዚአብሔርም “እጁን ዘርግቶ ድንጋዮቹን አንድ በአንድ በጣቱ ነካቸው።” መጋረጃው ከያሬድ ወንድም አይኖቹ ተወሰዱ፣ እናም “የጌታን ጣት ተመለከተ …እንደ ሰው ጣት ነበር። …

“እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ የምናገርህን ቃላት ታምናለህን?

“እናም እርሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ አዎን፣ ጌታ ሆይ።”

እናም “ጌታ እራሱን [ለያሬድ ወንድም አሳየ]” እናም እንዲህ አለ፣ “አንተ በእኔ አምሳል መፈጠርህን ተመልክተሃልን? አዎን፣ ሰዎች ሁሉ እንኳ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተፈጠሩት በእኔ አምሳል ነው።” (ኤተር 3፥1–17ተመልከቱ።)

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “I Know That My Redeemer Lives፣” in Conference Report, ሚያዝያ 1966፣ 63።

  2. Gospel Topics, “Becoming Like God,” topics.lds.org{100}፤ ደግሞም ሙሴ 7፥31–37ተመልከቱ።

  3. “ቤተሰብ፥ ለአለም አማጅ፣” Liahona፣ ህዳር 2010፣ 129።

  4. Gospel Topics, “Becoming Like God,” topics.lds.org; see also Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007)፣ 221 ተመልከቱ።

ይህን አስቡበት

እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር ምስል እንደተፈጠረ ማወቅ እርስ በራስ ባለን ግንኙነት እንዴት ይረዳናል?

አትም