2016 (እ.አ.አ)
ምርጫዎች
ሜይ 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)

ምርጫዎች

ከቀላሉ ስህተት ይልቅ ሁሌም ከባዱን ትክክለኛ ምርጫ እናድርግ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ዛሬ መደበኛ መልእክቴን ከመጀመሬ በፊት፣ በሚከተሉት ቦታዎች በመጪው ወራት እና አመታት ውስጥ የሚገነቡትን አራት አዲስ ቤተመቅደሶች ማሳወቅ እፈልጋለሁ፤ ኩዪቶ፣ ኢኳዶር፤ ሀረሬ፣ ዚምባብዌ፤ ብሌም፣ ብራዚል፤ እና ሁለተኛ ቤተመቅደስ በሊማ፣ ፔሩ።

በ1963 (እ.አ.አ.) የአስራሁለት ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ስሆን፣ በመላ ቤተክርስቲያኗ 12 በስራ ላይ ያሉ ቤተ-መቅደሶች ነበሩ። ከሁለት ሳምንት በፊት በፕሮቮ ከተማ ማዕከል ቤተ-መቅደስ መመረቅ በኋላ አሁን በመላው ዓለም 150 በስራ ላይ ያሉ ቤተ-መቅደሶች ይገኛሉ ። በእነዚህ ቅዱስ ቤቶች ስለምንቀበላቸው በረከቶች ምንኛ አመስጋኞች ነን።

አሁን ወንድሞችና እህቶች፣ በዚህ ጠዋት ትንሽ ሃሳቦችን ላካፍላችሁ እድሉን በማግኘቴ ምስጋናዬን ለመግለፅ እፈልጋሁ።

በቅርቡ ስለ ምርጫዎች እያሰብኩኝ ነበር። የታሪክ በር በትንሽዬ ማዞሪያዎች ላይ እንደሚንጠለጠል ተነግሯል፣ እናም የሰዎችም ሕይወት እንደዚሁ ነው። የምንመርጣቸው ምርጫዎች እጣፈንታችንን ይወስናሉ።

የቅድመ ምድራዊ ሕይወታችንን ስንተውና ወደ ምድር ስንመጣ፣ የነፃ ምርጫን ስጦታ ይዘን መጣን። ግባችን የሰለስቲያል የክብር ደረጃን ማግኘት ነው እናም የምናደርጋቸው ምርጫዎች በትልቅ ክፍሉ ግባችላ ላይ መድረስ አለመድረሳችንን ይወስናል።

አብዛኛዎቻችሁ በልዊስ ካሮል ዓይነተኛ ልቦለድ ውስጥ {1}የአሊስን የምናብ ቦታ ጀብዱ ታወቃላችሁ። ከፊቷ በሁለት ተቃራኒ አቅጣጫ ወደሚያመሩ መንገዶች ላይ እንደደረሰች ታስታውሳላችሁ። ወደ የትኛው መንገድ መዞር እንዳለባት ስታሰላስል፣ አሊስ “የትኛውን መንገድ ልከተል?” ብላ ከጠየቀችው ከቼሻየር ድመት ጋር ተገናኘች።

ድመቱም መለሰ፣ “ያየሚወሰነው የት መሄድ በምትፈልጊው ላይ ነው። የት መሄድ እንደምትፈልጊ ማወቅ ካልቻልሽ፣ የምትሄጂበት መንገድ ምንም ለውጥ አያመጣም።”1

እንደ አሊስ ሳይሆን እኛ የት መሄድ እዳለብን እናውቃለን እናም የምንወስደው መንገድ ለውጥ ያመጣል፣ ምክንያቱም በዚህ ሕይወት ውስጥ የምንከተለው መንገድ ወደሚቀጥለው ሕይወታችን መድረሻ ይመራልና።

በራሳችን ውስጥ ከጠላቱ አሰራሮች በጣም ውጤታማ መከላከያ የሚሆን ታላቅና ኃይለኛ እምነትን ማለትም የሚደግፈንና ትክክለኛውን የመምረጥ ፍላጎታችንን የሚያጎለብት እውነተኛ እምነትን ለመገንባት እንምረጥ። ካለእንደዚህ አይነት እምነት ወዴትም መሄድ አንችልም። ከእንደዚህ ዓይነት እምነት ጋር ግባችንን ማከናወን እንችላለን።

ምንም እንኳን በብልኃት መምረጣችን አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሞኝ ምርጫዎችን የምናደርግበት ጊዜዎች አሉ። በአዳኙ የተሰጠ የንስሃ ስጦታ ወደምንሻው የሰለስቲያል የክብር ደረጃ ወደሚያመራው መንገድ መመልስ እንድንችል የመንገድ ድባባችንን ለማስተካከል ያስችለናል።

ሁሉም የሚከተሉትን ላለመከተል በመበርታታ እንቀጥል። ከቀላሉ ስህተት ይልቅ ሁሌም ከባዱን ትክክለኛ ምርጫ እናድርግ።

ይሄን ለመምረጥ ወይም ያንን ለመምረጥ በእያንዳንዱ ቀናት የምናደርጋቸውን ውሳኔዎች ስናሰላስል፣ ክርስቶስን ከመረጥን፣ ትክክለኛውን ምርጫ መርጠናል ማለት ነው።

ይሄ እንዲሆን ከልብ የመነጨ እና ትሁት ጸሎቴ ነው፣ በጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻ

  1. Adapted from Lewis Carroll, Alice’s Adventures in Wonderland (1898), 89.

አትም