2016 (እ.አ.አ)
በትከሻዎቹ ላይ ያስቀምጣችኋል እናም ወደ ቤት ይሸከማችኋል።
ሜይ 2016


የሴቶች የቤት ለቤት መልእክት፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)

በትከሻዎቹ ላይ ያስቀምጣችኋል እናም ወደ ቤት ይሸከማችኋል።

ልክ እንደ መልካም እረኛ የጠፋ በጉን እንደሚያገኝ፣ ወደ ዓለም አዳኙ ልባችሁን የምታነሱ ከሆነ ያገኛችኋል።

በልጅነቴ ከማስታውሳቸው ሁሉ የሚያስፈራኝ ከእንቅልፌ ያነቃኝ በርቀት የአየር ወረራ ማስታወቂያ ጥሪ ነበር። ብዙ ሳይቆይ፣ ሌላ ድምፅ፣ የአውሮፕላኑ ድምጽ አየሩን እንደሚያንቀጠቅጥ አይነት እስከሚመስል ድረስ በቀስታ ይጨምራል። በእናታችን በደንብ በመሰልጠን እኛ እያንዳንዳችን ልጆች ቦርሳችንን ይዘን ኮረብታ ላይ ወዳለው ወደ ቦምብ መጠለያ እሮጥን። በጭለማው ውስጥ ስንሮጥ፣ አረንጓዴ እና ነጭ ብልጭታዎች ከሰማይ ወርደው ቦንቡ የሚመታውን ቦታ ይጠቁማሉ። በሚያስገርም ሁኔታ፣ እነዚህን ብልጭታዎች የገና ዛፍ ብለው ይጠሯቸዋል።

አራት አመቴ ነው፣ እናም ለአለም ጦርነት ምስክር ነኝ።

ድሬዝድን

ቤተሰቤ ከኖሩበት ሳይርቅ የሚገኝ የድሬዝድን ከተማ ነበር። በዚያ የሚኖሩት እኔ ያየሁትን በአንድ ሺህ እጥፍ የሚሆን ነበር ያዩት። በብዙ ሺህ ኪሎግራም ቦምቦች ምክንያት የነበረ በጣም ትልቅ የእሳት አውሎ ንፋስ በድረዝደን ውስጥ በሙሉ አለፈ፣ 90 በመቶ ከተማውን ደመሰሰው እናም በሚያልፍበትም ከቆሻሻ እና አምድ በስተቀር ምንም አልተወም።

በአጭር ጊዜ፣ አንዴ “የጌጥ ሻንጣ” የተባለ ስም የተሰጠው ቦታ አልነበረም። የጀርመን ጸሀፊ ስለመደምሰሱ እንዲህ ጻፈ፣ “ወብቷ የተገነባወ በአንድ ሺህ አመት ነበር፣ በአንድ ምሽት ይህም በሙሉ ተደመሰሰ።”1 በልጅነቴ የራሴ ህዝብ በጀመሩት ጦርነት ምክንያት የነበረው ጥፋት እንዴት ለመታደስ እንደሚችል አይታየኝም ነበር። በአካባቢያችን ያለው አለም ሙሉ በሙሉ ተስፋ የሌለው እና የወደ ፊት ነገር የሌለው ነበር።

ባፈው ዓመት ወደ ድሬዝደን ለመመለስ እድል ነበረኝ። ከጦርነቱ ሰባ አመት በኋላ፣ ይህም እንደገና “የጌጥ ሻንጣ” ነው። የፈረሱት ነገሮች ተጠርገዋል፣ እናም ከተማው ታድሷል እናም ተሻሽሏል።

በጉብኝቴ ፍራውንኪርችህ፣ የሴት ወይዘሮ ቤተክርስቲያንን ቆንጆ የሉተር ቤተክርስቲያን አየሁ። በመጀመሪያ በ1700 (እ.አ.አ) የተገነባው፣ ይህም የድረዝደን የሚያብረቀርቅ ሀብት ነበር፣ ነገር ግን ተሰባብሮ ነበር። ለብዙ አመታት እንደዚያ ቀረ፣ በመጨረሻም ፍራውንኪርችህ እንደገና እንዲገነባ ተወሰነ።

ከፈረሰው ቤተክርስቲያን ለመጠቀም የሚቻልባቸው ድንጋዮች ተሰብስበው እና ተዘርዝረው ነበር፣ እናም ከተቻለ እንደገና በሚገነባበት ጊዜ ተጠቅመውባቸው ነበር። ዛሬ በእሳት የጠቆሩት ድንጋዮች የውጪው ግድግዳ ላይ እንደ ምልክት ይታያሉ። እነዚህ “ጠባሶች” የዚህ ህንጻ የጦርነት ታሪኮች ማስታወሻ ብቻ ሳይሆኑ የተስፋ ሀውልት—ከአመድ አዲስ ህይወት ለመፍጠር ሰው ስላለው ችሎታ ታላቅ ምሳሌ ናቸው።

ስለድረዝደን ታሪክ ሳሰላስል እና በፍጹም የተደመሰሰውን እንደገና ስለገነቡት ብልህነት እና ውሳኔ ስገረምበት፣ የመንፈስ ቅዱስ አስደሳች ተፅዕኖ ተሰማኝ። በእርግጥም ሰው የተሰበረ ከተማን ውድመት፣ ፍርስራሽ፣ እና ቅሪት፣ ከወሰደ እና ወደሰማይ ከፍ ያለ የሚያነሳሳ ህንጻ ለመገንባት ከቻለ፣ ሁሉን ቻይ አባታችን የወደቁትን፣ የሚታገሉትን፣ እና የጠፉትን ልጆቹን በዳግም ለመመለስ ምን ያህል ተጨማሪ ችሎታ አለውን?

ህይወታችን እንዴን አይነት ውድመት እንዳለው ምንም ግድ የለውም። ኃጢያታችን እንዴት እንደቀላ፣ ምሬታችን እንዴት ጥልቅ እንደሆነ፣ እኛም እንዴት ብቸኛ፣ የተጣልን፣ ወይም ልባችን የተሰበረ መሆኑም ግድ የለውም። ተስፋ የሌላቸውም፣ ተስፋ ቆርጠው ያሉትም፣ እምነትን የከዱትም፣ ሀቀኝነታቸውን አሳልፈው የሰጡትም፣ ወይም ከእግዚአብሔርን ፊታቸውን ያዞሩ እንደገና ለመገንባት ይችላሉ። ልዩ ከሆኑት አንዳንድ የጥፋት ልጆች በስተቀር፣ እንደገና ለመገንባት የማይችል የተሰባበረ ምንም ህይወት የለም።

የወንጌል አስደሳች ዜና ይህ ነው፥ በውድ የሰማይ አባታችን እና መጨረሻ በሌለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል በተሰጠው የደስታ እቅድ ምክንያት፣ ከውድቀት ለመዳን ከመቻላችን በተጨማሪ፣ ስጋዊ አስተሳሰብን ለማለፍ እና የዘለአለም ህይወት ወራሾች እና ለመግለጽ የማይቻለው የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች ለመሆን እንችላለን።

የጠፋው በግ ምሳሌ

በአዳኝ አገልግሎት ጊዜ፣ የእርሱ ዘመን የሀይማኖት መሪዎች “ኃጢያተኞች” ብለው ከሚጠሯቸው ጋር ኢየሱስ ጊዜ ማሳለፉን ተቃውመው ነበር።

ምናልባት ለእነርሱ ኃጢያተኛ ጸባዮችን ተቀባይ ወይም ደጋፊ እንደሆነ ይመስላቸው ነበር። ምናልባት እነርሱ ኃጢያተኞች ንስሀ እንዲገቡ የሚያደርግ መልካም መንገድ እነርሱን መውገዝ፣ ማሳለቅ፣ እና ማሳፈር ነው ብለው ያምኑ ነበር።

ፈሪሳውያኖች እና ጸሀፊዎች የሚያስቡትን አዳኝ ሲገነዘብ፣ ታሪክ ነገራቸው፥

“መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?

“ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል።”2

ከመቶ አመቶች በኋላ፣ ይህም ምሳሌ የጠፋውን በግ ለመመለስ እና የጠፉትን ለመርዳት በስራ እንደምንጠራበት ትርጉም ተሰጥቶታል። ይህም በእርግጥ ትክክለኛ ቢሆንም፣ በዚህ ላይ ተጨማሪ እንደሚኖረው አስባለው።

የኢየሱስ አላማ፣ በመጀመሪያ፣ ስለመለካሙ እረኛ ስራ ለማስተማር መሆን ይችል ነበርን?

ለአስቸጋሪው ልጁ እግዚአብሔር ስላለው ፍቅር እያስተማረ መሆኑ ይችላልን?

የአዳኝ መልእክት እግዚአብሔር ስለጠፉት በሙሉ ያውቃል--እናም እርሱም ያገኛቸዋል፣ ይደርስላቸዋል፣ እናም ያድናቸዋል፣ የሚል ሊሆን ይችላልን?

ያ ከሆነ፣ በግ ለዚህ መለኮታዊ እርዳታ ብቁ ለመሆን ምን ማድረግ አለበት?

ውስብስብ በሆነው መለኪያ ነጥቦቹን ለማስላት እንዴት መጠቀም እንደሚችል ማወቅ አለበትን? ያለበትን ቦታ ለመግለፅ ጂ.ፒ.ኤስ መጠቀም አለበትን? ለእርዳታ ለማግኘት ጥሪ ማስተላለፍ የሚችል ፕሮግራምን መፍጠር አለበትን? መልካሙ እረኛ መጥቶ ከማዳኑ በፊት በጉ በስፖንሰር ደጋፍ ማግኘት ያስፈልገዋልን?

አይደለም። በጭራሽ አይደለም! በጉ ለመለኮታዊ መዳን ብቁ የሚሆነው በመልከካ እረኛ ስለሚወደደ ብቻ ነው።

ለእኔ፣ የጠፋው በግ ምሳሌ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከሚገኑ መልእክቶች ሁሉ በላይ ተስፋ የሚሰጥ ጥቅስ ነው።

አዳኛችን፣ መልካሙ እረኛ፣ እናንተን ያውቃችኋል እንዲሁም ይወዳችኋል። ያውቃችኋል እንዲሁም ይወዳችኋል።

ስትጠፉ ያውቃል፣ እናም የት እንዳላችሁም ያውቃል። ሀዘናችሁን ያውቃል። ጸጥተኛ ልመናችሁንም። ፍርሀታችሁንም። እምባዎቻችሁንም።

በራሳችሁ መጥፎ ምርጫዎች ወይም እናንተ ለመቆጣጠር በማትችሉበት ጉዳዮች ቢሆንም፣ እንዴት እንደጠፋቹ ግዴታ የለውም።

የሚያስብበት አናንተ ልጆቹ መሆናችሁ ነው። እናም ያፈቅራችኋል። ልጆቹን ይወዳል።

ስለሚወዳችሁ፣ ያገኛችኋል። በደስታ በትከሻው ላይ ያደርጋችኋል። ወደቤት ሲያመጣችሁ፣ ለአንድ እና ለሁሉም እንዲህ ይላል፣ “የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ።”3

ምን ማድረግ አለብን?

ነገር ግን እናንተም ምን ማድረግ አለብን? ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። በእርግጥ ለመዳን ከመፈለግ በላይ ማድረግ አለብኝ።

አፍቃሪው አባታችን ልጆቹ በሙሉ ወደ እርሱ እንዲመለሱ ፍላጎት ቢኖረውም፣ ማንንም ወደ ሰማይ በግድ አይመልስም።4 እግዚአብሔር ያለፍቃዳችሁ አያድናችሁም።

ምን ማድረግ አለብን?

ግብዣው ቀላል ነው፥

“ወደ እኔ … ዙሩ።”5

“ወደ እኔ ኑ።”6

“ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ።”7

እኛ ለመዳን እንደምንፈልግ የምናሳየው እንዲህ ነው።

ይህም ትንሽ እምነት ያስፈልገዋል። ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ። አሁን እምነትን ለመሰብሰብ የማትችሉ ከሆናችሁ፣ በተስፋ ጀምሩ።

እግዚአብሄር እንዳለ አሁን ለማለት የማትችሉ ከሆነ፣ እንደሚገኝ ተስፋ ማድረግ ትችላላችሁ። ለማመን መፈለግ ትችላላችሁ።8 ይህም ለመጀመሪያ ብቁ ነው።

ከዚያም፣ በዚያ ተስፋ መሰረት በመስራት፣ ወደ ሰማይ አባት ቅረቡ። እግዚአብሄር ፍቅሩን ወደ እናንተ ይዘረጋል፣ እናም የማዳን እና የመቀየር ስራው ይጀምራል።

ከጊዜ በኋላም፣ እጁን በህይወታችሁ ውስጥ ትገነዘባላችሁ። ፍቅሩ ይሰማችኋል። በእርሱ ብርሀን ለመራመድ እና የእርሱን መንገድ የመከተል ፍላጎት በእያንዳንዱ የእምነት እርምጃዎቻችሁ ያድጋል።

እነዚህን የእምነት እርምጃዎች “ታዛዥነት” ብለን እንጠራቸዋልን።

በእነዚህ ቀናት ይህ ተወዳጅ ቃል አይደለም። ነገር ግን ታዛዥነት በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የተወደደ ሀሳብ ነው፣ ምክንያቱም “የወንጌሉን ህግጋትና ስርዓቶችን በማክበር፣ የሰው ዘር ሁሉ በክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ አማካኝነት መዳን እንደሚችሉ” እናውቃለን።9

በእምነት ስንጨምር፣ በታማኝነት ማደግም አለብን። ቀደም ብዬ ስለ ድሬዝደን ውድመት ያዘነን የጀርመን ደራሲ ጠቅሻለሁ። እንዲሁም ይህንን ሐረግ ፃፈ “Es gibt nichts Gutes, ausser: Man tut es.” የሰለስቲያል ቋንቋን ለመናገር ለማይችሉት፣ ይህ እንዲህ ይተረጎማል “ካላደረጋችሁት በስተቀር ምንም መልካም የለም።”10

እናንተ እና እኔ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ልብ በሚነካ መንገድ እንናገር ይሆናል። በሀይማኖት ርዕስ ባላችሁ ቅን ምሁር ትርጉም ሌሎችን ለማስገረም እንችል ይሆናል። ስለሀይማኖት እንዘምር እና “በላይ ስላለው ቤታችን እናልም” ይሆናል።11 ነገር ግን እምነታችን እንዴት እንደምንኖር ካለወጠ—እምነታችን በየቀኑ የምንወስንበት ላይ ተፅዕኖ ከሌለው—ሀይማኖታችን በከንቱ ነው፣ እናም እምነታችንም፣ ያልሞተም ቢሆንም፣ በእርግጥም ደህና አይደለም እና በመጨረሻም፡ለመሞት አደጋ ላይ ነው ያለው።12

ታዛዥነት የእምነት የህይወት ደም ነው። በታዛዥነት ነው ወደ ነፍሳችን ብርሀንን የምንሰበስበው።

ነገር ግን ታዛዥነትን አንዳንዴ እንደማንረዳው ሀሳብ አለን። ታዛዥነትን ወደ መጨረሻ የምንደርስበት እንደሆነ ሳይሆነ፣ በራሱ መጨረሻ እንደሆነ እንመለከተው ይሆናል። ወይም የምናፈቅራቸውን፣ በሚቀጥል ሙቀት እና በተደጋጋሚ ድብደባ፣ ወደ ተቀደሱ እና ሰማያዊ ነገሮች ለማስተካከል የምሳሌ ታዛዥነት መዶሻን በትእዛዛት የብረት ቅርፅ ማውጫ ላይ እንቀጠቅጥ ይሆናል።

ምንም ጥርጥር የለውም፣ ወደ ንስሀ መግባት በጥብቅ ሀይል መጠራት የሚያስፈልገን ጊዜዎች አሉ። በእርግጥም፣ በዚህ አይነት ብቻ መደረስ የሚችሉ አንዳንዶችም አሉ።

ነገር ግን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የምናከብርበትን ምክንያት የሚገልጽ ሌላ ምሳሌ አለ። ታዛዥነት ነፍሳችንን ወዳልሆንበት የማጣመም፣ ወይም የመጠምዘዝ፣ እና የመቀጥቀጥ ሂደት ላይሆንም ይችላል። በዚህ ምትክ፣ በምን እንደተሰራን ለማወቅ የምንችልበት ሂደት ሊሆን ይችላል።

በሀያሉ እግዚአብሔር የተፈጠርን ነን። የሰማይ አባታችን ነው። እኛም ቃል በቃል የእርሱ የመንፈስ ልጆች ነን። በጣም ውድ በሆኑ እና በጣም በተነጠሩ መለኮታዊ ነገሮች የተሰራን ነን፣ እና በዚህም በውስጣችን መለኮታዊ ነገሮች የያዝን ነን።

በዚህ ምድር ላይ ግን ሀሳባችን እና ስራዎቻችን በተበከነው፣ ቅዱስ ባልሆነውም እና ንጹህ ባልሆነው እንቅፋት ይሆንብናል። የአለም አቧራ እና ቆሻሻ የውልድ መብታችንን እና አላማችንን እንዳንረዳ እና እንዳናውቅ በማድረግ ነፍሳችን ላይ እንከን ያደርግበታል።

ነገር ግን ይህ ሁሉ በእውነት ማን እንደሆንን ለመቀየር አይችሉም። የፍጥረታችን መሰረታዊ መለኮታዊነት ይቀራል። ልባችንን ወደ ውድ አዳኛችን ለማዞር ስንመርጥ እና በደቀመዛሙርትነት መንገድ እግራችንን ስናሳርፍ፣ ታዕምራታዊ ነገር ይደርሳል። የእግዚአብሄር ፍቅር ልባችንን ይሞላል፤ የእውነት ብርሀን አዕምሮአችንን ይሞላል፤ ኃጢያት ለመስራት ያለንን ፍላጎት እናጣለን፤ እናም በጭለማ ለመራመድ ከዚህ በኋላ አንፈልግም።13

ታዛዥነትን እንደ ቅጣት ሳይሆን ወደ መለኮታዊ እጣ ፈንታችን የሚወስድ ነጻ እንደሚያደርገን መንገድ እንመለከተዋለን። እናም ቀስ በቀስ፣ ሙስናው፣ አቧራው፣ እና የዚህች አለም ገደብ እየወደቁ ይሄዳሉ። በመጨረሻም፣ በውስጣችን የሚገኘው ታላቅ ዋጋ ያለውም የሰማይ ሰው ዘለአለማዊ መንፈስ ይገለጻል፣ እናም የመልካምነት ብርሀን ፍጥረታችን ይሆናል።

ለመዳን ብቁ ናችሁ

ወንድሞችና እህቶች፣ እግዚአብሔር በእውነት እንደሆንን እንደሚያየን—እና ለመዳን ብቁ እንደሆንን እንደሚያየን እመሰክራለሁ።

ህይወታችሁ እንደተበላሸ ይሰማችሁ ይሆናል። ኃጢያት ሰርታችሁም ይሆናል። የፈራችሁ፣ የተናደዳችሁ፣ ያዘናችሁ፣ ወይም በጥርጣሬ የተሰቃያችሁ ይሆናል። ነገር ግን መልካሙ እረኛ የጠፋውን በግ እንዳገኘው፣ ልባችሁን ወደ አለም አዳኝ ከፍ ካደረጋችሁ፣ እርሱ ያገኛችኋል።

ያድናችኋል።

ከፍ ያደርጋችኋል እናም በትከሻው ያስቀምጣችኋል።

ወደቤትም ተሸክሞ ይወስዳችኋል።

ሟች እጆች የተሰባበረውን እና የተደመሰሰውን ውብት ወዳለው የማምለኪያ ቦታ ለመቀየር ከቻሉ፣ የሚወደን የሰማይ አባት እኛን ለመገንባት እንደሚችል እና እንደሚገነባ መተማመን እንችላለን። እቅዱ እኛ ከነበርንበት በጣም ታላቅ--ልናስብበት ከምንችለው በላይ ታላቅ--ወደሆነ ነገር ለመገንባት ነው። በደቀመዛሙርትነት መንገድ በእያንዳንዱ የእምነት እርምጃ፣ ለመሆን ወደተመደብንበት ወደ ዘለአለማዊ ክብር እና መጨረሻ ወደሌለው ሰዎች እያደግን እንሄዳለን።

ይህም ምስክርነቴ፣ በረከቴ፣ እና ትሁት ጸሎቴ ነው፣ በቅዱሱ መምህራችን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም