2016 (እ.አ.አ)
አባታችን፣ መካሪያችን
ጁን 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሰኔ 2016 (እ.አ.አ)

አባታችን፣ መካሪያችን

የነገሮች መስሪያ አካላት የያዘ ሳጥንን ከፍታችሁ፣ የመስሪያ መመሪያውን አውጥታችሁ፣ እና “ይህ ምንም የሚገባ አይደለም” ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?

አንዳንዴ፣ ምርጥ ሀሳቦች እና ውስጣዊ ጥንካሬ ቢኖረንም፣ የመስሪያ ክፍልን እናወጣና “ይህ ምን ይደረግበታል?” ወይም “ይህ እንዴት ይገባል?” ብለን እንጠይቃለን።

ሳጥኑን ስንመለከት እና “መገንባት ያስፈልገዋል - 8 አመት እና ከዛ በላይ” የሚለውን ማስታወቂያ ስናይ ንዴታችን ይጨምራል። አሁንም ፍንጭ ስለሌለን፣ ይህ በራስ መተማመናችንን ወይም የግል አስተያየታችንን ከፍ አያደርገውም።

አንዳንዴ በወንጌልም እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች አሉን። የዚህን አንዳንድ ክፍሎች ስንመለከት፣ ራሳችንን እናካለን እናም ክፍሉ ለምን እንደሚሆን እናሰላስላለን። ወይም ሌላን ክፍል ስንመረምር፣ በሙሉ ለመረዳት በጣም ከጣርን በኋላም እንኩዋን፣ ያ ክፍል ለምን እንደተጨመረ ለማወቅ እንደማንችል መወሰናችንን እንረዳለን።

የሰማይ አባታችን መካሪያችን ነው።

መልካም እድል ሆኖ እድሜአችን ወይም ጉዳያችን ምንም ቢሆን እነዚህ መመሪያዎች ይሰራሉ። ወንጌልን እና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ሰጥቶናል። የቤዛነት እቅድን፣ የደህንነት እቅድን፣ እንዲሁም የደስታን እቅድ፣ በጥርጣሬዎች ወይም በህይወት ፈተናዎች ሁሉ፣ “እንኩ፣ መልካም እድል። በራሳችሁ መፍትሄ አግኙበት” በማለት ብቻችንን አልተወንም።

ትዕግስተኛ ከሆንን እና በትሁት ልብ እና በተከፈተ አዕምሮ ከተመለከትን፣ እግዚአብሔር ለህይወት ደስታችን ስለሰጠን የእርሱ ፍጹም መመሪያዎችን በተሻለ መንገድ እንድንረዳ ብዙ መሳሪያዎች እንደሰጠን እናገኛልን።

  • የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና እና ሀሳቦቻችንን እና ስራዎቻችንን ከእርሱ ቃል ጋር አንድ ለማድረግ በምንጥርበት ጊዜ፣ የግል፣

  • እርሱን በ24/7 ለማግኘት የምንችልበትን የእምነት ጸሎት እና የልብ ፍላጎት ልመና ሰጥቶናል።

  • በዘመናችን የእግዚአብሔር ቃልን የሚገልጹ እና በምድር እና በሰማይ ለማተሳሰር ወይን ለማተም ስልጣን ያላቸውን የዚህ ዘመን ነቢያት እና ሐዋሪያትን ሰጥቶናል።

  • ደህንነታቸውን በፍርሀት፣ በመንቀጥቀጥ፣ እና ተመሳሳይነት በሌለው ደስታ ሲያከናውኑ እርስ በራስ በመረዳዳት አብረው የሚሰሩ አማኞች ድርጅት የሆነችወን ቤተክርስቲያኑን በዳግም መልሷል።1

  • በእርሱ የተጻፉ ቃላት የሆኑትን ቅዱሳት መጻህፍቶች ሰጥቶናል።

  • በደቀመዛሙርትነት ጉዞአችን የሚረዱን የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ሰጥቶናል። አብዛኛዎቹ እነዚህ አስደናቂ መሳሪያዎች በ LDS.org ውስጥ ይገኛሉ።

የሰማይ አባት እነዚህን ያህል ብዙ እርዳታዎች ለምን ሰጠን? ስለሚያፈቅረን ነው። እና ምክንያቱም፣ እርሱ ራሱ እንዳለው፣ “ይህ የእኔ ስራ እና ክብር ነው- የሰውን ሟች አለመሆንን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት።”2

በሌላ አባባልም፣ የሰማይ አባት የእኛ እግዚአብሔር ነው፣ እናም እግዚአብሔር አማካሪያችን ነው።

የሰማይ አባታችን የልጆቹን ፍላጎት ከማንም ሰው በላይ ያውቃል። ይህም እኛን በእያንዳንዱ መንገድ ለመርዳት፣ ወደእርሱ ለመመለስ በምንጓዝበት አስደናቂ ጊዜአዊ እና መንፈሳዊ እርዳታ የሚሰጥበት ስራው እና ግርማው ነው።

እያንዳንዱ አባት መካሪ ነው

በአለም አንዳንድ ክፍሎች ውስጥ፣ አባቶች በቤተሰቦች እና በህብረተሰቦች በሰኔ ወር ውስጥ ይከበራሉ። ወላጆችን ማክበር ሁሌም መልካም ነገር ነው። አባቶች ለቤተሰቦቻቸው ብዙ መልካም ነገሮች ያደርጋሉ እናም ብዙ ተወዳጅ ባህርይ አላቸው። አባቶች በህይወት ውስጥ ካላቸው ሀላፊነቶች ሁሉ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ሁለቱ ጥሩ ምሳሌ መሆን እና መካሪ መሆን ናቸው። አባቶች ልጆቻቸውን ምን ትክክል እንደሆነ እና ምን ትክክል እንዳልሆነ ከመንገር በላይ ነው የሚያደርጉት፤ የመመሪያ መፅሀፍ ወደ እነርሱ ከመወርወር እና ህይወትን በራሳቸው እንዲማሩባት ከመጠበቅ በላይ ነው የሚያደርጉት።

አባቶች ውድ ልጆቻቸውን ያማክራሉ እናም በመልካም ምሳሌአቸው ታማኝ ህይወት እንዴት እንደሚኖር ያሳዩአቸዋል። አባቶች ልጆቻቸውን ለብቻቸው አይትዉም ግን ለመርዳት ወደ እነርሱ በፍጥነት ይሄዳሉ፣ ሲደናቀፉም እንዲነሱ ይረዷቸዋል። አንዳንዴ ጥበብ ሀሳብ ሲያቀርብም፣ ከሚማሩበት ሁሉ ይህ የሚሻል እንደሆነ በመረዳት አባቶች ልጆቻቸው እንዲታገሉ ይፈቅዳሉ።

ሁላችንም መካሪዎች ነን።

የምድር አባቶች ይህን በራሳቸው ልጆች ላይ ሲያደርጉ፣ እድሜ፣ የሚገኙበት ቦታ፣ ወይም ጉዳይ ምንም ቢሆን የመካሪነት መንፈስ ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ ማቅረብ የሚገባን ነገር ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንደሆኑ አስታውሱ፤ ሁላችንም ከአንድ የዘለአለም ቤተሰብ የመጣን ነን።

በዚህም አስተያየት፣ ሁላችንም መካሪዎች እንሁን …- ለመድረስ እና እኛ የተሻለ ማንነት ያለን እንድንሆን እርስ በእርስ በመረዳዳትም። የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን፣ እንደ እርሱ የመሆን ችሎታ አለን። እግዚአብሔርን እና ሰዎችን ማፍቀር፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ማክበር፣ እና የክርስቶስን ምሳሌ መከተል ወደ ሰማይ ወላጆቻችን ፊት የሚወስዱን ቀጥተኛ፣ ጠባብ፣ እና አስደሳች መንገድ ናቸው።

የስነፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔር ስለእኛ በጣም በማሰብ ለእኛ መካሪ ከሆነ፣ ምናልባት እኛም የቆዳ ቀለማቸው፣ ዘራቸው፣ የህብረተሰብ ኢኮኖሚ ሁኔታቸው፣ ቋንቋቸው፣ ወይም ሀይማኖታቸው ምንም ቢሆን ወደ ሰዎች ለመርዳት መድረስ እንችላለን። የሚያነሳሱ መካሪዎች እንሁን እናም የሌሎችን - የልጆቻችንን ብቻ ሳይሆን ደግሞም በአለም አቀፍ የሚገኙትንም የእግዚአብሔር ልጆችን ህይወት እንባርክ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የምታስትምሯቸውን የሰማይ አባት የመከራቸውን ጊዜ እንዲያስታውሱ በመጠየቅ ጀምሩ። በዚያ ጊዜ እና የምድር አባታቸው በሚመክራቸው ጊዜ መካከል ስለነበረው አንድነት እንዲያስቡበት ለመጠየቅም ትችላላችሁ። በተመከሩበት ያሉትን አንድነቶች እንዲጽፉም ጋብዟቸው። ለሌሎች የተሻለ ምሳሌ ለመሆን በሚጥሩበት የጻፏቸውን ነገሮች በምሳሌ እንዲከተሉም ጠይቋቸው።

አትም