2016 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች
ጁን 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ ጉብኝት መልእክት ሰኔ 2016 (እ.አ.አ)

የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። ለአለም አዋጅን መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከትዋቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪመረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

ለደህንነት እና ከፍ ከፍ ለመደረግ አስፈላጊ የሆኑት ስርዓቶች በሙሉ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙ ናቸው። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት “ቃል ኪዳኖችን መግባት እና መጠበቅ ማለት ከሰማይ አባታችን እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመተሳሰር መምረጥ ነው” ብለዋል።1

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት አባል ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን እንዳሉት፣ “ጌታ እንዳለው፣ ‘በስርዓቶች ውስጥ … የአመላክነት ሀይል ተገልጿል።’

“ለሚጠመቀው መንፈስ ቅዱስ ለሚቀበለው እና በየጊዜው ቅዱስ ቁርባንን ለሚወስደው ለእያንዳንዱ ብቁ ሰው ከእግዚአብሔር የሚመጡ ልዩ በረከቶች አሉ።”2

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት አባል ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንዳሉት “ወንዶች እና ሴቶች ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ፣ ሁለቱም በአንድ አይነት መንፈሳዊ ሀይል ተባርከዋል፣ ይህም የክህነት ሀይል ነው …

“… ሁሉም ወንዶች እና ሴቶች በህይወታቸው እዳታ ለማግኘት ይህን ሀይል ለመጠቀም ይችላሉ። ከጌታ ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን የገቡ እና እነዚያን ቃል ኪዳኖች የሚያከብሩ የግል ራዕይ ለመቀበል፣ በመላእክት አገልግሎት ለመባረክ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር፣ የወንጌልን ሙላት ለመቀበል፣ እና በመጨረሻም፣ አብ ያላቸውን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ጎን ወራሾች ለመሆን ይችላሉ።”3

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት

1 ኔፊ 14፥14፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥13፤ 97፥8፤ 109፥22

ህያው ታሪኮች

በ2007 (እ.አ.አ) በፔሩ ከነበረ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ አራት ቀን በኋላ፣ የሰባዎች አባል ሽማግሌ ማርከስ ቢ. ናሽ ከቅርንጫፍ ፕሬዘደንት ዌንቼስላኦ ኮንዴ እና ከባለቤታቸው ፓምላ ጋር ተገናኙ። “ሽማግሌ ናሽ እህት ኮንዴን ትትንሽ ልጆቻቸው እንዴት እንደጎኑ ጠየቋቸው። ፈገግ በማለት፣ በእግዚአብሔር መልካምነት ሁሉም ደህና ናቸው ብለው መለሱ። ስለኮንዴ ቤትም ጠየቁ።

“‘ጠፍቷል፣’ ብለው መለሱ።

“… ’እና ግን፣’ ሽማግሌ ናሽ እንዳመለከቱት፣ ‘ስንነጋገር ፈገግ ትያለሽ።’

“’አዎን፣’ ብለው መለሱ ‘ጸልያለሁ እና በሰላም ላይ ነኝ ያለሁት። የሚያስፈልጉን ሁሉ አሉን። እርስ በራስ እንገኛለን፣ ልጆቻችን አሉን፣ በቤተመቅደስ ታትመናል፣ ይህች አስደናቂ ቤተክርስቲያን አለችን፣ እናም ጌታ አለን። በእግዚአብሔር እርዳታ እንደገና ለመገንባት እንችላለን።’ …

“ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን መግባት እና መጠበቅ ውስጥ በችግር ውስጥ ፈገግ እንድንል፣ ስቃይን ወደ ድል እንድንቀይር እንድንችል የሚያደርገን ምንድን ነው … ?”

“ምንጩም እግዚአብሔር ነው። ይህን ሀይል ለመጠቀም የምንችለው ከእርሱ ጋር በገባናቸው ቃል ኪዳኖች በሙል ነው።”4

ማስታወሻዎች

  1. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ “The Power, Joy, and Love of Covenant Keeping,” Liahona፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 111።

  2. ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “Power in the Priesthood,” Liahona፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 92።

  3. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Men and Women in the Work of the Lord፣” Liahona፣ ሚያዝያ 2014 (እ.አ.አ)፣ 48–49።

  4. ዲ፣ ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “The Power of Covenants፣” Liahona፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 19፣ 20–21 ተመልከቱ።

ይህን አስቡበት

የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች እንዴት ሊያጠናክሩን እና ሀይል ሊሰጡን ይችላሉ?

አትም