2016 (እ.አ.አ)
ትዕዛዛትን መጠበቅ እና ሌሎችን መውደድ
ሴፕቴምበር 2016


ወጣቶች

ትዕዛዛትን መጠበቅ እና ሌሎችን መውደድ

ስለፍቅር ስናስብ፣ ብዙ ጊዜ ወደ አእምሮአችን የሚመጡ የመጀመሪያ ነገሮች የፍቅር ፊልሞች፣ ቸኮሌቶች፣ እና አበባዎች ናቸው። ነገር ግን ፍቅር—እውነተኛ ፍቅር—ከዛ በላይ የበለጠ ጥልቅና የበለጠ እራስ ወዳድ ያልሆነ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ባለው ፍቅር የተነሳ ለእኛ ኖረ እንዲሁም ሞተ። በእርግጥ፣ ሁለቱ ታላቅ ትዕዛዛት እግዚአብሔርን መውደድና ሌሎችንም መውደድ ናቸው (ማቴዎስ 22፥36-40 ተመልከቱ)። ነገር ግን ሌሎችን እንደምንወዳቸው እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ለአባቱ ስለሰራውና ሰላልሰራው ስለሁለት ወንድ ልጆች የክርስቶስ ምሳሌን አካፈሉ። አባቱን የታዘዘው ልጅ ብቻ በእውነት እንደሚወደው አዳኙ አስገነዘበ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ስንጠብቅ፣ እንደምንወደውና ወደ እርሱ መመለስ እንደምንፈልግ እናሳያለን።

ነገር ግን ሁሉንም እንደምንወዳቸው እንዴት ማሳየት እንችላለን? ፕሬዘደንት ኡክዶርፍም ያንን አስረድተዋል፥ “ጓደኞቻችንን በእውነት ከወደድናቸው ‘ድሆችን እና የተቸገሩትን፣ የታመሙ እና የተሰቃዩትን’ ለመርዳት እራሳችንን እንሰጣለን። እነዚህን እራስ ወዳድ ያልሆኑ የርህራሄና የአገልግሎት ተግባሮችን የሚያደርጉ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ናቸው።”

ስለዚህ ወላጆቻችሁን፣ ወንድማችሁን ወይም እህታችሁን፣ ወይም ጓደኛችሁን በሚቀጥለው ጊዜ ስታዩ ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር ለማሳየት እነሱን ለማገልገል አስቡ። እነሱንና እናንተን ደስተኛ ብቻ አይደለም የሚያደርጋችሁ፣ ነገር ግን የሰማይ አባታችሁንም ደስተኛ ያደርገዋል።

አትም