2016 (እ.አ.አ)
ከፍቅር በኋላ፣ ከዛ ምን?
ሴፕቴምበር 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ 2016 (እ.አ.አ)

ከፍቅር በኋላ፣ ከዛ ምን?

ውዱ ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ፍቅር የወንጌል መሰረታዊ ነገር እንደሆነ አስተማሩ።”1

ፍቅር በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ኢየሱስ “የመጀመሪያውና ታላቁ ትዕዛዝ” ብሎ ጠራው እናም እያንዳንዱ የህግ ትንሹ መጠን እና የነቢያት ቃሎች በዛ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው አለ።2

ፍቅር በቤተክርስቲያን ውስጥ ለምናደርጋቸው ነገሮች ማዕከላዊ ምክንያት ነው። እያንዳንዱ ፕሮግራም፣ እያንዳንዱ ስብሰባ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ሆነን የምናከናውነው እያንዳንዱ ተግባር ከዚህ ባህሪ መፍለቅ አለበት—ምክንያቱም ካለ ልግስና፣ “የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር፣” ከንቱዎች ነን።3

ይህንን አንዴ በአእምሮአችንና በልባችን ከተገነዘብን፣ አንዴ ለእግዚአብሔርና ለጓደኛችን ፍቅራችንን ካወጅን—ከዛ በኋላ ምን?

ለሌሎች ርህራሄ እና ፍቅር መሰማት በቂ ነውን? ለእግዚአብሔርና ለጎረቤታችን ፍቅራችንን ማወጅ ለእግዚአብሔር ያለንን ሃላፊነት ያሟላልን?

የሁለቱ ልጆች ምሳሌ

በኢየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ የይሁዳ ሊቃነ ካህናትና ሽማግሌዎች በቃሎቹ ሊያጠምዱት ኢየሱስን ቀረቡት። ይሁን እንጂ፣ አዳኙ አንድን ታሪክ በመናገር ጉዳዩን ወደ ራሳቸው አዞረው።

“አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፣” በማለት ጀመረ። አባቱ ወደ አንደኛው ሄዶ በወይን አትክልቱ ውስጥ እንዲሰራ ጠየቀው። ነገር ግን ልጁ እምቢ አለ። በኋላ ግን “ተጸጸተና ሄደ”።

አባቱ ወደ ሁለተኛው ሄዶ በወይን አትክልቱ ውስጥ እንዲሰራ ጠየቀው። ሁለተኛው ልጅ እንደሚሄድ አረጋገጠለት፣ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ።

ከዛ አዳኙ ወደ ካህናትና ሽማግሌዎች ፊቱን መልሶ እንዲህ ጠየቀ፣ “ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው?”

አልሄድም ያለው ነገር ግን በኋላ ተጸጸቶ በወይን አትክልት ውስጥ ለመስራት የሄደው የመጀመሪያው ልጅ እንደነበረ መቀበል ነበረባቸው።4

አዳኙ ይህንን ታሪክ ትዕዛዛትን የሚያከብሩት ሰዎች እግዚአብሔርን በእውነት የሚወዱት ናቸው የሚለው ጠቃሚ መርሆ ላይ ትኩረት ለማድረግ ተጠቀመ።

ምናልባትም ለዚህ ነው ኢየሱስ ሰዎቹን የፈሪሳዊያኖችንና የጻፎችን ቃላት እንዲያደምጡና እንዲከተሉ ነገር ግን ምሳሌዎቻቸውን እንዳይከተሉ የጠየቀው።5 እነዚህ ሐይማኖተኛ አስተማሪዎች ያስተማሩትን አልተከተሉም። ስለሐይማኖት መናገር ይወዳሉ፣ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ መሰረታዊ ነገሩን አጥተውታል።

ተግባራት እና ደህንነታችን

አዳኙ ለደቀ መዛሙርቱ በሰጠው ከመጨረሻ ትምህርቶቹ መካከል በአንዱ፣ ስለመጨረሻው ፍርድ ተናገራቸው። ኃጢያተኞችና ፃድቃኖች ይለያያሉ። መልካሞቹ የዘላለም ሕይወትን ይወርሳሉ፤ ኃጢያተኞቹ ደግሞ ለዘላለም ቅጣት ይሰጣሉ።

በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነበር?

በተግባራቸው አማካኝነት ፍቅራቸውን ያሳዩ ሰዎች ድነው ነበር። ያላሳዩ ደግሞ ተወግዘው ነበር ።6 ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልና ለዋጋዎቹ እንዲሁም ለመርሆቹ በእውነት መለወጥ በቀን ተቀን ሕይወታችን ተግባሮች ውስጥ ይታያል።

በመጨረሻ ላይ ለእግዚአብሔርና ለጓደኞቻችን ፍቅር በቀላሉ ማወጅ ለደህነነት ብቁ አያደርገንም። ምክያቱም ኢየሱስ እንዲህ አስተምሯል፣ “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፤ ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ፣ የሚለኝ ሁሉ መንግሰተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።”7

ከፍቅር በኋላ ምን ይቀጥላል?

“ከፍቅር በኋላ፣ ከዛ ምን?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ ቀላልና ቀጥተኛ ሊሆን ይችላል። አዳኙን በእውነት ከወደድን፣ ልቦቻችንን ወደ እርሱ እናዘነብላለን፣ ከዛም በደቀ መዝሙርነት መንገድ ላይ እንጓዛለን። እግዚአብሔርን ስንወድ፣ ትዕዛዛቶቹን ለመጠበቅ እንጥራለን።8

ጓደኞቻችንን በእውነት ከወደድን፣ “ድሆችን እና የተቸገሩትን፣ የታመሙ እና የተሰቃዩትን” ለመርዳት እራሳችንን እንሰጣለን።9 እነዚህን እራስ ወዳድ ያልሆኑ የርህራሄና የአገልግሎት ተግባሮችን የሚያደርጉ፣10 የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ናቸው።

ይህ ከፍቅር በኋላ የሚመጣ ነገር ነው።

ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ ነገር ነው።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማለት ፍቅራቸውን ለእርሱና ለሌሎች በተግባራቸው የሚያሳዩ ሰዎች እንደሆኑ አድርገው ተረጎሙ። እንዲህ አስተማሩን፣ “አዳኙን በእውነት ከወደድን፣ ልቦቻችንን ወደ እርሱ እናዘነብላለን፣ ከዛም በደቀ መዛሙርትነት መንገድ ላይ እንጓዛለን።” የምታስተምሯቸውን ሰዎች በምን ዓይነት መንገድ ፍቅር በደቀ መዛሙርትነት መንገድ ላይ እንዲጓዙ እንዳበረታታቸወ ለመጠየቅ አስቡ። የራሳችሁን ልምዶች ማካፈልም ትችላላችሁ። በፍቅር ለመተግበር ለበለጠ ልግስናና ጥንካሬ እንዲፀልዩ ለመጋበዝ አስቡበት።

አትም