2016 (እ.አ.አ)
ወላጅነት የተቀደሰ ተግባር ነው
ሴፕቴምበር 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ 2016 (እ.አ.አ)

ወላጅነት የተቀደሰ ተግባር ነው

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ መነሳሳትን እሹ። “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅን” መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከቷቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

የሰማይ አባታችን ትክክለኛ መርሆዎችን ፍቅር በተሞላበት ሁኔታ ውስጥ ለማስተማር እንዲረዳን ቤተሰቦችን መሰረተ። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ አሉ፣ “ልጃችሁን አሞግሱ እና እቀፉ፤ በተጨማሪም ‘እወድሃለሁ በሉ’፤ ሁልጊዜም ምስጋናችሁን ስጡ። መፍትሄ የሚሰጠውን ችግር ከሚወደደው ሰው በላይ አስፈላጊ አታድርጉት።”1

ሱዛን ደብሊው. ታነር፣ የቀድሞ የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዘደንት እንዲህ አስተማረች፣ “የሰማይ አባታችን መከተል ያለብንን ንድፍ ምሳሌ ሰጠ። ይወደናል፣ ያስተምረናል፣ ይታገሰናል እናም ነፃ ምርጫን ሰጥቶናል። … አንዳንድ ጊዜ ‘ማስተማር’ የሚለው ትርጓሜ ያለው ስነ-ስርዓት ከትችት ጋር ግራ ይጋባል። ልጆች---እንዲሁም በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች---ስህተትን ከመፈለግ በበለጠ ሁኔታ ከፍቅርና ከማበረታታት ባህሪን ያሻሽላሉ።”2

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ሽማግሌ ክዊንተን ኤል. ኩክ እንዳሉት፣ “በአማኝነት የቤተሰብ ጸሎት፣ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ የቤተሰብ የቤት ምሽት፣ የክህነት በረከቶች፣ እና የሰንበትን ቀን የመጠበቅ ልምድ ካለን፣ ልጆቻችን … በአስቸጋሪው ዓለም ውስጥ ምንም ነገር ቢያጋጥማቸውም እንኳን፣ በሰማይ ውስጥ ለዘላለማዊ ቤት ዝግጁ ይሆናሉ።”3

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት

1 ኔፊ 8፥37፤ 3ኔፊ 22፥13፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥40፤ 121፥41

ህያው ታሪኮች

“ከወጣት የወንድ የልጅ ልጆቼ መካከል አንዱ ሲለጠፍብኝ ጋዜጣ እያነበብኩኝ ነበር” አሉ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ አባል ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ። “በማነብበት ወቅት፣ ጣፋጭ ድምፁ በስተጀርባዬ ሲያስተጋባ በመስማቴ ተደስቼ ነበር። ከትንሽ ጊዜ በኋላ እራሱን በእኔና በጋዜጣው መካከል በሚገፋበት ወቅት የነበረኝን መደነቅ አስቡት። ፊቴን በእጆቹ ውስጥ በማድረግና አፍንጫውን ወደ እራሴ በመግፋት እንዲህ ጠየቀ፣ ‘አያቴ! አለህ?’

“… እዛ መኖር ማለት የወጣቶቻችንን ልቦች መረዳትና ከእነሱ ጋር መቆራኘት ማለት ነው። እናም ከእነሱ ጋር መቆራኘት ማለት ከእነሱ ጋር ማውራት ብቻ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ከእነሱ ጋር ነገሮችን ማድረግ ማለትም ጭምር ነው። …

“ማቀድና የማስተማሪያ ወቅቶችን ጥቅም መውሰድ አለብን። …

“… የበለጠ ስኖር፣ በወጣትነቴ ውስጥ በተለይም በወላጆቼ የተሰጡት የማስተማሪያ ወቅቶች ሕይወቴን እንደቀየሩትና ማንነቴን እንደሰሩት የበለጠ እገነዘባለሁ።”4

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Love, the Essence of the Gospel፣” Liahona፣ ነሐሴ 2011 (እ.አ.አ)፣ 4።

  2. ሱዛን ደብሊው. ታነር፣ “Did I Tell You … ?” Liahona ሚያዝያ 2003 (እ.አ.አ.)፣ 74።

  3. ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “The Lord Is My Light,” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ.)፣ 64።

  4. ሮበርት ዲ. ሄልስ፣ “Our Duty to God: The Mission of Parents and Leaders to the Rising Generation,” Liahona, ግንቦት 2010 (እ.አ.አ.)፣ 96፣ 95።

ይህን አስቡበት

ለምንድን ነው ወንጌልን በፍቅር ቋንቋና ምሳሌ በተሻለ ሁኔታ ማስተማር የተቻለው?