ልጆች
ፍቅርን ማሳየት
ኢየሱስ የአንድን አባትና የሁለት ወንዶች ልጆቹን ታሪክ አካፈለ። አባት በወይን አትክልት ውስጥ ይሰራ ነበር እናም ሁለት ወንድ ልጆቹን እንዲረዱት ጠየቀ። የመጀመሪያው ልጅ በመጀመሪያ እምቢ አለ ነገር ግን በኋላ ለመርዳት ወደ ወይን አትክልት ስፍራው መጣ። ሁለተኛው ልጅ እንደሚረዳ ተናገረ፣ ነገር ግን ሳይረዳ ቀረ። ኢየሱስ የመጀመሪያው ልጅ በመታዘዝ የበለጠ ፍቅር ለአባቱ እንዳሳየ አስተማረ።
ይህን ታሪክ ተውኑ! ከዛ ለሰማይ አባት ፍቅርን ለማሳየት የምታደርጉትን ሶስት ነገሮች ፃፉ ወይም ሳሉ።