2017 (እ.አ.አ)
አንድ ፈገግታ ለውጥ ማምጣት ይችላል
ጃንዩወሪ 2017


ወጣቶች

አንድ ፈገግታ ለውጥ ማምጣት ይችላል

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ለተግባሮቻችን መኖር ያለብንን ሁለት ግቦች ለይተው አስቀምጠዋል፤ እግዚአብሔርን ማፍቀር እና ባልጀሮቻችንን ማፍቀር። ነገር ግን አንዳንዴ ሌሎችን ማፍቀር እንዲህ ቀላል አይደለም። በህይወታችሁ ውስጥ ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ለመኖር ከባድ የሚሆኑ ወቅቶች ሊያጋጥማችሁ ይችላል—በእርግጥም አንድ ሰው ጎድቷችኋል ወይም ለመግባባት ወይም ከሆነ ሰው ጋር ተግባብቶ መኖር አስቸጋሪ ሆኖባችኋል። በእነኚህ ጊዜያት፣ ከጓደኞቻችሁ፣ ከቤተሰቦች፣ ከሰማይ አባት፣ እናም ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰምቷችሁ የነበረውን ፍቅር ለማስታወስ ሞክሩ። በእነኛ ሁኔታዎች ውስጥ የተሰማችሁን ሀሴት አስታውሱ እናም ሁሉም ሰው ይህንን አይነት ፍቅር ቢኖረው ኖሮስ ብላችሁ ለማሰብ ሞክሩ። ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ሴት ወይም ወንድ ልጅ እንደሆነ እናም የእሱ እና የእናንተ ፍቅር እንደሚገባው አስታውሱ።

ከእሱ ወይም እርሷ ጋር ለመግባባት አስቸግሯችሁ ስለነበር በህይወታችሁ ውስጥ ያለን አንድ ሰው አስቡ። በፀሎቶቻችሁ ውስጥ አካትቷቸው እናም ልባችሁን ለእነርሱ እንዲከፍትላችሁ የሰማይ አባትን ጠይቁ። ወዲያውም እሱ እነሱን እንደሚያያቸው እነሱን ማየት ትጀምራላችሁ፥ ልክ ፍቅር እንደሚገባው ከልጆቹ አንዱ።

ከፀለችሁ በኋላ፣ አንድ መልካም ነገርን አድርጉላቸው! ምናልባትም የጋራ ፕሮግራሞች ወይም ከጓደኞች ጋር ጉዞ መሄድ ላይ ጋብዟው። በቤት ስራቸው ላይ እርዳታ ለመስጠት ጠይቁ። “ሰላም ናችሁ” በሏቸው አናም ፈገግ በሉላችው። በሁለታችሁም ህይወት ውስጥ … ትናንሽ ነገሮች ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ!

አትም