2017 (እ.አ.አ)
ወደ ማእከሉ ማለም
ጃንዩወሪ 2017


የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣ ጥር 2017 (እ.አ.አ)

ወደ ማእከሉ ማለም

በቅርቡ፣ የቀስት ውርወራ ጥበብን ሲለማመዱ የነበሩ ቡድኖችን አየሁ። ይህንን በመመልከት ብቻ፣ በቀስት እና በቀስት መወርወሪያው ላይ ጠቢብ መሆን ከፈለጋችሁ ጊዜንና ልምምድን እንደሚጠይቅ ግልፅ ሆነልኝ።

የተሳካለት ቀስተኛ ለመሆን ባዶ ግድግዳ ላይ በማለም እና ከዚያም ቀስቱ ባረፈበት ዙሪያ የኢላማውን ምልክት በመሳል ዝናን ማሳደግ የምትችሉ አይመስለኝም። ኢላማውን የማግኘትን እና የኢላማውን መሀከለኛ ነጥብ የመምታትን ጥበብ መማር አለባችሁ።

ኢላማዎቹን መሳል

መጀመሪያ አልሞ ከዚያም በኋላ ኢላማውን መሳል ትንሽ የማይመስል ነገር ነው፣ ነገር ግን አንዳንዴ እኛ እራሳችን በሌላ የህይወት ሁኔታዎች ላይ ያንኑ ተመሳሳይ ባህሪይ እንመለከታለን።

እንደ ቤተክርስቲያን አባላት፣ በወንጌል ፕሮግራሞች፣ ጉዳዮች፣ እናም እንዲሁም ቀልብ የሚስቡ፣ ጠቃሚ ወይም የሚያስደስቱ ከሚመስሉ ትምህርቶች ጋር የመያያዝ ዝንባሌ አለን። ኢላማውን በእነርሱ ዙሪያ ለመሳል እንፈተናለን፣ ያም ደሞ የወንጌልን ማዕከል እያለምን እንደሆነ እንድናምን ያደርገናል።

ይህን ማድረግ ቀላል ነው።

ለአመታት እጅግ በጣም ጥሩ ምክርን እና መነሳሳትን ከእግዚአብሔር ነብይ ተቀብለናል። እንዲሁም ከብዙ ህትመቶች፣ ከመመሪያ መፅሀፍት እናም ከቤተክርስቲያኗ ማስተማሪያ መፅሃፍት ምሬትን እና መብራራትን ተቀብለናል። የምንወደውን የወንጌል እርእስ በቀላሉ መምረጥ፣ በዙሪያው የኢላማውን ማእከለላዊ ነጥብ መሳል፣ እናም የወንጌል ማእከልን እንዳገኘን አድርገን ማቅረብ እንችላለን።

አዳኝ ያብራራል

ይህ ችግር ለኛ ጊዜ ለየት የሚል አይደለም። በጥንት ጊዜ፣ የሃይማኖት መሪዎች ከብዙ መቶ ትእዛዛት መካከል የትኛው የበለጠ እንደሆነ በደረጃ በማስቀመጥ፣ ልቆ በመመልከት፣ እናም በመከራከር እጅግ ብዙ ጊዜዎችን አሳልፈዋል።

አንድ ቀን የሀይማኖት ምሁራን ቡድን አዳኙን ወደ ሙግት ውስጥ እንዲገባ ተፈታተኑት። ጥቂቶች መስማማት ወደ ቻሉበት ጉዳይ ላይ ጠንካራ ሀሳቡን እንዲሰጥ ጠየቁት።

“መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ሲሉ ጠየቁት።

እንግዲህ ሁላችንም ኢየሱስ እንዴት እንደመለሰ እናውቃለን፥ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

“ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርስዋም ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትለው ናት።

“በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”1

እባካችሁ የመጨረሻውን አረፍተ ነገር ተገንዘቡ፤ “በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”

አዳኝ ኢላማውን ብቻ አይደለም ያሳየን ነገር ግን ኢላማውን ማእከላዊ ነጥብ ለይቶ አሳይቶናል።

ኢላማውን መምታት

እንደ ቤተክርስቲያን አባላት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ስምን በራሳችን ላይ ለመውሰድ ቃል ገብተናል። በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ ስለ እግዚያአብሔር ለመማር ጥረት እንደምናደርግ፣ እንድንወደው፣ በእርሱ ላይ እምነታችንን እንደምናሳድግ፣ እንደምናከብረው፣ በእርሱ መንገድ እንደምንሄድ፣ እናም ለእርሱ ምስክር ሆነን ፀንተን እንደምንቆም መረዳት አለ።

ስለ እግዚአብሔር የበለጠ ስንማር እና ለእኛ ያለው ፍቅር የበለጠ ሲሰማን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መጠን የሌለው መስእዋት መለኮታዊ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነ የበለጠ እንገነዘባለን። እናም የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ይቅር መባል ተአምር ወደ ሚመራው ትክክለኛ የንስሀ መንገድን እንድንጠቀም ያነሳሳናል። ይህ ሂደት በዙሪያችን ላሉት ታላቅ ፍቅር እና ርህራሄ እንዲኖረን ያስችለናል። ከምናውቀው ባሻገር ማየትን እንማራለን። ሌሎችን በሀጢያታቸው፣ በስህተታቸው፣ በጥፋታቸው፣ በፖለቲካ ግንዛቤያቸው፣ በሀይማኖት አቋማቸው፣ በብሄራቸው ወይም በቆዳ ቀለማቸው የመውቀስ ወይም የመፍረድ ፈተናን እንቋቋማለን።

የምናገኛቸው ሰዎችን ሁሉ የሰማይ አባት ልጅ እንደሆኑ፣ እንደ ወንድም ወይም እህት አድርገን እናያቸዋለን።

በመርዳት እና በፍቅር ለሌሎች እንደርሳለን፣ ለመወደድ ቀላል ያልሆኑትን ሰዎችንም እንኳን ሳይቀር። ከሚያዝኑት ጋር እናዝናለን መፅናናትን ለሚሹ መጽናናትን እንሰጣለን።2

እናም ስለ ትክክለኛው የወንጌል ኢላማ መጨነቅ እንደማይገባን እንገነዘባለን።

ኢላማው ሁለቱ ታላቅ ትእዛዛት ናቸው። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።3 ይህንን ስንቀበል፣ ሌሎች ሁሉም መልካም ነገሮች ለእኛ ይሆኑልናል።

ዋናው ትኩረታችን፣ ሀሳባችን፣ እናም ጥረታችን ሁሉን ቻይ በሆነው እግዚአብሔር ላይ ፍቅራችንን በማሳድግ እና ለሌሎችም ልባችንን በመክፈት፣ ትክክለኛውን ኢላማ ማግኘታችንን እና ኢላማውን ማእከላው ነጥብ ላይ እያነጣጠርን እንደሆንን እናውቃለን — ይህም እውነተኛ የኢየሱስ ደቀ ማዛሙርት ወደ መሆን ይመራል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ይህንን መልእክት ከማካፈላችሁ በፊት “Our Savior’s Love” (Hymns, no. 113 ) የሚለውን መዝሙር ልትዘምሩ ትችላላችሁ። ከዚያ የምትጎበኙዋቸውን ሰዎች በራሳቸው ህይወት ውስጥ በኢላማው ላይ እንዲያነፀባርቁ ማበረታታ ትን አስቡ። “እግዚያብሔርን አፍቅር” እና “ባልንጀራክን እንደራስክ አድርገህ አፍቅር” ( ማቴዎስ 22፥37፣ 39ተመልከቱ) የሚሉትን ሁለት ታላቅ ትእዛዛት ሁሌም ተግባራቸውን እንዲመሩዋቸው ለማረጋገጥ የሚያስችላቸው መንገዶችን መወያት ትችላላችሁ። የራሳችሁን ህይወት በክርስቶስ ላይ ያተኮራችሁባቸውን መንገዶች ማካፈል እና ያም እንዴት እንደባረካችሁ ምስክርነታችሁን ማካፈልም ትችላላችሁ።

አትም