2017 (እ.አ.አ)
የኢላማው ማእከለኛ ነጥብ
ጃንዩወሪ 2017


ልጆች

የኢላማው ማእከለኛ ነጥብ

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ወንጌል ልክ እንደ የኢላማ ልምምድ ነው አሉ። ኢላማ ማድረግ ያለብን የበለጠ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ላይ ነው። በጣም ጠቃሚ የሆኑት ትእዛዛት እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ማፍቀር ናቸው። በእነዚህ ነገሮች ላይ የምናተኩር ከሆነ፣ ሁሌም የኢላማውን ማእከለኛ ነጥብ መምታት እንችላለን።

በቁራጭ ወረቀት ላይ ትልቅ ኢላማ የሚሆን ነገር ሳሉ። የሚከተለውን ዝርዝር ወላጅ እንዲያነብላችሁ አድርጉ። ከዝርዝር ውስጥ ካሉው አንዱ ነገር ለእግዚአብሔር እና ለሌለች ሰዎች ፍቅር እንድናሳይ የሚረዳን ነገር ከሆነ፣ በኢላማው መካከል ላይ ጻፉት ወይም ሳሉት።

አሻንጉሊቶቻችሁን ማካፈል

ከረሜላ መስረቅ

ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ

የሆነ ሰውን ባስቀያሚ ስም መጥራት

ፀሎቶችን ማድረግ

የሆነ ሰውን ማቀፍ

ከእህታችሁ እና ከወንድማችሁ ጋር መጣላት

አትም