ልጆች
የኢላማው ማእከለኛ ነጥብ
ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ወንጌል ልክ እንደ የኢላማ ልምምድ ነው አሉ። ኢላማ ማድረግ ያለብን የበለጠ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ላይ ነው። በጣም ጠቃሚ የሆኑት ትእዛዛት እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ማፍቀር ናቸው። በእነዚህ ነገሮች ላይ የምናተኩር ከሆነ፣ ሁሌም የኢላማውን ማእከለኛ ነጥብ መምታት እንችላለን።
በቁራጭ ወረቀት ላይ ትልቅ ኢላማ የሚሆን ነገር ሳሉ። የሚከተለውን ዝርዝር ወላጅ እንዲያነብላችሁ አድርጉ። ከዝርዝር ውስጥ ካሉው አንዱ ነገር ለእግዚአብሔር እና ለሌለች ሰዎች ፍቅር እንድናሳይ የሚረዳን ነገር ከሆነ፣ በኢላማው መካከል ላይ ጻፉት ወይም ሳሉት።