2017 (እ.አ.አ)
ለሰላም መፀለይ
የካቲት 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ለሰላም መፀለይ

ደራሲዋ በኤሪዞና፣ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።

ወላጆቼ በብዛት ከቤተክርስቲያን በኋላ ስብሰባ ይካፈላሉ፣ እና እኔ ሶስቱ ታናናሽ ወንድሞቼን እጠብቃለሁ እናም ምሳ ሲሰሩ አግዛቸዋለሁ—በብዛት ቶሎ ተሰላች እና ተናዳጅ ቢሆኑም። ሁሌ መጣላት ከጀመሩ፣ ትንሹን ችግር በቶሎ መፍታት እችላለሁ። ነገር ግን አንዳንዴ ጥል ከተነሳ በኋላ ሰላም ማውረድ ይከብዳል ምክንያቱም እሰላቻለሁና።

አንድ ከሰአት በኋላ ላይ፣ ወንድሞቼ በተለየ ሁኔታ መግባባት ከብዷቸው ነበር። በመበሳጨቴ ምክንያት ሰላም ለማውረድ ያደረኩት ጥረት እንዲያውም ነገሮችን የሚያባብስ ሆኖ አገኘሁት። ስለዚህ የራሴን ምሳ ሰራሁ እና መናገር አቆምኩ። በስተመጨረሻም፣ እንዲህ በማለት አሳወኩ፣ “ልፀልይ ነው። እባካችሁ ለደቂቃ ፀጥ ልንል እንችላለን?” እነርሱ ሲረጋጉ፣ ምግቡ እንዲባረክ ጠየኩ። ፀሎቴን ከመጨረሴ በፊት፣ ይህንን ጨመረኩ፣ “እና ሰላም ፈጣሪዎች እንድንሆን እባክህ እርዳን።”

በመጀመሪያ፣ ያልሰሙ መሰሉ እና እንደገና መጣላት ጀመሩ። ተበሳጭቼ ነበር ነገር ግን በተቻለኝ መጠን አፍቃሪ እና ፀጥተኛ መሆን እንደነበረብኝ አወቅኩኝ ምክንያቱም ለሰላም ገና ፀለዬ ነበርና። ከደቂቃ በኋላ፣ በጣም መረጋጋት ተሰማኝ። ምንም ነገር ሳልናገር ተመገብኩ፣ እና ከቆይታ በኋላ ወንዶቹ ልጆች መጣላት አቆሙ። የተሰማኝ ሰላም የቀላሉ ፀሎት መልስ እንደነበር አስተዋልኩ። ሰላም ፈጣሪ ለመሆን ፀልያለሁ፣ እና ለመጮህ በጣም በሚፈታተን ጊዜ ውስጥ በዝምታ እንድቆይ የሰማይ አባት ረድቶኛል። እርሱ በእውነት ሰላም ሊሰጠን እንደሚችል አውቃለሁ።

አትም