2017 (እ.አ.አ)
የክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ የእግዚአብሔር ፍቅር ማስረጃ ነው
የካቲት 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ የካቲት 2017 (እ.አ.አ)

የክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ የእግዚአብሔር ፍቅር ማስረጃ ነው

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ መነሳሳትን እሹ።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

ከሞት እንድንነሳ እና የዘለአለማዊ ህይወት አቅም እንዲኖረን ለማድረግ የሰማይ አባታችን ብቸኛ ልጁን መስጠቱን መረዳታችን የእግዚአብሔርን ማለቂያ የሌለው እና ጥልቅ ፍቅር እንዲሰማን ይረዳናል። አዳኛችንም ይወደናል።

“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? …

“ሞት ቢሆን፣ ህይወትም ቢሆን፣መላእክትም ቢሆኑ፣ ግዛትም ቢሆን፣ ያለውም ቢሆን፣ የሚመጣውም ቢሆን፣ ኀይላትም ቢሆኑ፣

“ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ”(ሮሜ 8፥35፣ 38-39)።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ፣ የአስራ ሁለቱ ሀዋርያት ጉባኤ አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እንዲህ አሉ፥ “የአዳኝ በጌተሰማኒ የነበረው ስቃይ እና በመስቀሉ ላይ የነበረው ጣር፣ ፍትህ በእኛ ላይ የነበራትን እዳ በመክፈል እኛን ከሀጢያት አዳነን። እርሱ ምህረትን ያበዛል እናም ንስሃ የሚገቡትን ይቅር ይላል። በማዳን እና በየዋህነት ለምናሳልፈው ማንኛውም መከራን በማካስ የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ የፍትህን እዳንም ጨምሮ ያሳካል። ‘እነሆም፣ እርሱ በሁሉ ሰዎችን ህመም፣ አዎን፣ በአዳም ቤተሰብ አባል በሆኑት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረታት፣ በወንድም፣ በሴትም፣ በልጆችም ህመም ይሰቃያል’ (2 ኔፊ 9፥21፤ ደግሞም አልማ 7፥11-12 ተመልከቱ)።”1

ክርስቶስ “[እኛን] በእጁ መጻፍ ቀርፆናል።”(ኢሳይያስ 49፥16)። ሊንዳ ኬ. በርተን፣ አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘዳንት፣ እንዲህ አሉ፣ “ያ ታላቅ የፍቅር ድርጊት አንድያ ልጁን እስኪልክ እና ፍፁሙን ልጁን ለእኛ ሀጢያት፣ ለልብ ህመማችን፣ እና በየራሳችን ህይወት ውስጥ ፍትሀዊ ለማይመስሉ ነገሮች ሁሉ እንዲሰቃይ እስኪያደርግ ድረስ የሰማይ አባታችን እኛን ስለመውደዱ ተንበርክከን በትሁት ፀሎት እንድናመሰግነው እያንዳንዳችንን ሊያደርገን ይገባል።”2

ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ

ዮሀንስ3፥162 ኔፊ 2፥6–7፣9reliefsociety.lds.org

ማስታወሻዎች

  1. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “Redemption፣” Liahona፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 110።

  2. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ “Is Faith in the Atonement of Jesus Christ Written in Our Hearts?” Liahona፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 114።