2017 (እ.አ.አ)
እኔ እንደወደድኳችሁ
የካቲት 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የካቲት 2017 (እ.አ.አ)

“እኔ እንደወደድኳችሁ”

ከጥቂት አመታት በፊት ሉዊስ የሚባል ጓደኛዬ ረጋ ስላለች እና መልካም ስለሚባልላት እናቱ ተወዳጅ ታሪክ አካፈለኝ። እርሷ ስትሞት፣ ለወንድ እና ሴት ልጆቿ የተወችው በምሳሌ፣ በመስዋእትነት፣ በታዥነት ውስጥ የነበረ ሀብትን እንጂ የገንዘብ ሀብት አልነበረም።

የቀብር ስርአት ላይ የህይወት ታሪክ ከተነገረ እና ወደ መቃብር አሳዛኙ ጉዞ ከተደረገ በኋላ፣ ብዙ የሆኑት የቤተሰብ አባላት እናት የተወችውን ትንሹን ንብረት ተከፋፈሉ። ከእነርሱ ውስጥ፣ ሉዊስ ማስታወሻ እና ቁልፍ አገኘ። ማስታወሻው እንዲህ የሚል መምሪያ ነበረው፥ “በዳርኛው መኝታ ክፍል፣ በኮመዲኖዬ ታችኛው መሳቢያ ውስጥ፣ ትንሽ ሳጥን አለ። የልቤን ሀብት ይዟል። ይሄ ቁልፍ ደግሞ ሳጥኑን ይከፍታል።”

እናታቸው የነበራት እና ቆልፋ ለማስቀመጥ የሚያበቃ ዋጋ ያለው ነገር ምን ሊሆን እንደሚችል ሁሉም አሰቡ።

ሳጥኑ ከተቀመጠበት ቦታ ተነሳ እና በቁልፉ እርዳታ በጥንቃቄ ተከፈተ። ሉዊስ እና ሌሎቹ የሳጥኑን ይዘት ሲፈትሹ፣ የእያንዳንዱን ልጆች ፎቶ በተናጠል አገኙ፣ የልጁ ስም እና የልደት ቀን አብሮ ነበር። ሉዊስ እቤት ውስጥ የተሰራ የፍቅር ማስታወሻን ስቦ አወጣ። የእራሱ እንደሆነ ባስተዋለው፣ እንዲሁ በተፃፈ የልጅ እጅ ጽሁፍ፣ ከ60 አመት በፊት የጻፈውን ቃላት አነበበ፥ “ውድ እናቴ፣ እወድሻለሁ።”

ልቦች አዝነው፣ ድምፆች ለስልሰው፣ እና አይኖች ረጥበው ነበር። የእናት ሀብት የዘለአለማዊ ቤተሰቧ ነበር። ጥንካሬው ደግሞ የተገነባው “እወድሀለሁ” ወይም “እወድሻለሁ” በሚል አለታማ መሰረት ላይ ነው።

በዛሬው አለም፣ በቤት ውስጥ ከሚያስፈልገው በላይ ያ የፍቅር አለታማ መሰረት የትም ቦታ አይፈለግም። ፍቅርን የቤተሰባቸው ህይወት ዋና ክፍል ካደረጉ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤቶች ውስጥ ካልሆነ በቀር አለም የዛን መሰረት ምሳሌ ከየትም ልታገኝ አይቻላትም።

የአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ነን ለምንል ሰዎች፣ ይህንን ጥልቅ መመሪያ ሰጥቷ፥

“እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፣ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”1

እርስ በእርስ በመዋደድ ትዕዛዙን የምንጠብቅ ከሆነ፣ በደግነትና በክብር፣ በየቀኑ ግንኙነታችን ፍቅራችንን በማሳየት እርስ በራሳችን ልንንከባከብ ይገባል። ፍቅር መልካም ቃላትን፣ በትእግስት የተሞላ ምላሽን፣ እራስ ወዳድ ያልሆነ ተግባርን፣ የሚረዳ ጆሮን፣ ይቅር ባይ የሆነ ልብን ይሰጣል። በሁሉም ግንኙነቶቻችን ውስጥ እነዚህና ሌሎች እነዚህን መሰል ባህሪዎች በልባችን ውስጥ ያለውን ፍቅር ያረጋግጣሉ።

ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ (1910-2008 እ.አ.አ) ይህን አስተዋሉ፥ “ፍቅር… በቀስተ ደመና መጨረሻ ላይ ያለ የወርቅ ማሰሮ ነው። ነገር ግን ከቀስተ ደመና መጨረሻም በላይ ነው። ፍቅር በስተመጀመሪያም አለ፣ እና በማእበላማ ቀን ባለ ሰማይ ላይ በሞላ የሚፈነጥቅ ውበት ከሱ ይመነጫል። ፍቅር ልጆች የሚያነቡለት ደህንነታቸው፣ ወጣቶች የጓጉለት፣ ጋብቻን አንድ የሚያደርግ ማጣበቂያ፣ እና በቤት ውስጥ የሚኖሩ አውዳሚ መቃቃሮችን የሚያስወግድ ማለስለሺያ ነው፤ የእርጅና ሰላም ነው፣ በሞት ውስጥ የሚያበራ የፀሀይ ብርሃን ተስፋ ነው። በቤተሰብ፣ በጓደኞች፣ በቤተክርስቲያን፣ እና በጎረቤቶች ግንኙነት ውስጥ በእሱ የሚደሰቱ ምን ያህል ሀብታም ናቸው።”2

ፍቅር የወንጌል የመጀመሪያ ፍሬ ነገር፣ እንዲሁም የሰው ነብስ ዘውዳዊ ባህሪ ነው። ፍቅር ለተጎዱ ቤተሰቦች፣ ለክፉ ማህበረሰቦች፣ እና ለታመሙ ህዝቦች መዳኒት ነው። ፍቅር ፈገግታ፣ የእጅ ማውለብለብ፣ ደግ አስተያየት፣ እና ሙገሳ ነው። ፍቅር መስዋእት፣ አገልግሎት፣ እና እራስ ወዳድ አለመሆን ነው።

ባሎች፣ ሚስታችሁን አፍቅሩ። በክብር እና በማበረታታት ተንከባከቧቸው። እህቶች፣ ባላችሁን አፍቅሩ። በክብር እና በማበረታታት ተንከባከቧቸው።

ወላጆች፣ ልጆቻችሁን ውደዱ። ለእነርሱ ፀልዩላቸው፣ አስተምሯቸው፣ እናም መስክሩላቸው። ልጆች፣ ወላጆቻችሁን ውደዱ። አክብሮት፣ ምስጋና፣ እና ታዛዥነታችሁን አሳዩዋቸው።

ያለ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅር፣ ሞርሞን እንደሚመክረው፣ “[እኛ] ከንቱዎች ነን።”3 ፀሎቴ እንዲህ የሚለውን የሞርሞንን ምክር እንድንከተል ነው።፣ “በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ፤ የእግዚአብሔር ልጆች [እንሆን] ዘንድ፣ እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደእርሱ እንሆናለን።”4

አትም