2017 (እ.አ.አ)
የስም ባጅ የሌለው ሚስዮን
ሰኔ 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

የስም ባጅ የሌለው ሚስዮን

በትምህርት ቤት ውስጥ በርዕስ ላይ የተቃረነ አስተያየት ያለውን ለማካፈል ሰውን የሚያስፈራ አይነት የግል ባህሪያ ያለው አስተማሪ ነበረኝ። አንድ ቀን ስለ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሚስዮኖች ርዕስ ለመነጋገር ጀመርን። ጥያቄዎቹን ለመመለስ እችል ነበር፣ ነገር ግን እንዳልመልስ ስሜት ተሰማኝ። ስለዚህ እርሱ ለጊዜው እርካታ የሚያገኝበትን ብቻ መልስ ሰጠሁት።

ለሚቀጥሉት ለተወሰኑ ሳምንቶች ግን ስለንግግራችን ለማሰብ ለማቆም አልቻልኩም። በመጨረሻም፣ ስለሚስዮን ስራ የሚናገሩትን ሀረጎች ላይ ምልክቶች ያለው መፅሐፈ ሞርሞን ለእርሱ ለመስጠት ሀሳብ መጣልኝ። ይህ ሀሳብ አስፈራኝ፣ ነገር ግን ይህም በአቋም ጸና። ይህም መከተል ያለብኝ ምሪት እንደሆነ አወቅሁኝ።

ከሁለት ወራት ያህል በኋላ፣ መጸሐፈ ሞርሞንን አዘጋጀሁ። ቀኑን በሙሉ መፅሐፉ በቦርሳዬ ውስጥ ተቀምጦ አወጥቼ መስጠት እንዳለብኝ ከባድ ስሜት ይሰማኝ ነበረኝ። በክረምት እረፍት ከመውጣታችን በፊት ይህን ለእርሱ ለመስጠት ያሳለፍኩት ሶስት ሰከንዶች በህይወቴ በሙሉ ከነበሩ አስፈሪ አጋጣሚዎችከፍተኛ ሆኖ ነበር የተሰማኝ።

በተመለስንበት በመጀመሪያው ቀን፣ በክፍሉ አጠገብ አለፍኩኝ እናም ለመግባት ፈርቼ ነበር። ከዚያም ሲጠራኝ ሰማሁት፣ እናም ካርድ ሰጠኝ። ይህንንም በመተላለፊያው ቆሜ አነበብኩት። ምልክት ያደረጓቸውን ሀረጎች “በጥልቅ” እንዳጠና፣ እና በእምነቴ አንዳንድ ምክንያቶች እያየ እንደመጣ ጻፈልኝ።

አሁን ወንጌልን ሳካፍል ደስ ይለኛል፣ እናም በቅርብ የሰማይ አባቴን በሚስዮን ለማገልገልም ከዚህ በላይ ደስታ ይሰማኛል።

አትም