2017 (እ.አ.አ)
ለስራው የተጠራ
ሰኔ 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሰኔ 2017 (እ.አ.አ)

ለስራው የተጠራ

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ስሚዝ ሽማግሌ ሒበር ሲ. ኪምባልን [1801-1868 (እ.አ.አ)] “የደህንነት በርን ለመክፈት” ወደ እንግሊዝ አገር እንደሚስዮን እንዲያገለግል ሲጠራ፣ ሽማግሌ ኪምባል ብቁ ባለመሆን ስሜት ተይዞ ነበር።

“አቤቱ ጌታ፣ ምላሱ የተሳሰረበት ሰው ነኝ፣ እናም ለዚህ አይነት ስራ ተገቢ ሰው አይደለሁም” ብሎ ጻፈ።

ይህም ሆኖ ግን፣ ሽማግሌ ኪምባል ይህን በመጨመር፣ ጥሪውን ተቀበለ፣ “እነዚህ አስተሳሰቦች ከሀላፊነት መንገዴ አላዞሩኝም፤ የሰማይ አባቴን ፍላጎት በተረዳሁ ጊዜ፣ በምንም አደጋ፣ ሁሉን ቻይ በሆነው ሀይሉ እንደሚደግፈኝ፣ እና በሚያስፈልገኝ ብቁነት በሙሉ እንደሚባርከኝ በማመን ለመሄድ ቁርጠኝነት ተሰማኝ።”1

በሙሉ ጊዜ ሚስዮን እንድታገለግሉ የተጠራችሁ ወጣት ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ወደ ስራው የተጠራችሁት፣ እንደ ሽማግሌ ኪምባል፣ “እግዚአብሔርን ለማገልገል ፍላጎት” ስላላችሁ (ት. እና ቃ. 4፥3) እና እናንተ የተዘጋጃችሁ እና ብቁ ስለሆናችሁ ነው።

የተጋባችሁት አገልጋዮች፣ እናንተም ለስራው የተጠራችሁት በዚህ ምክንያት ነው። እናንተ ግን የምታመጡት የማገልገል ፍላጎትን ብቻ ሳይሆን ደግሞም የሰማይ አባት እውነትን የሚፈልጉትን የወንድ እና ሴት ልጆቹን ሊነካ የሚችልበትን በመስዋዕት፣ በፍቅር፣ እና በተሞክሮ ያገኛችሁትን ጥበብ ይዛችሁ ትመጣላችሁ። ሌሎችን በማገልገል ጌታን ካላገለገልን በስተቅቀር፣ በፍጹም እሱን በእውነት ለመውደድ እንደማንችል እንደተማራችሁ የተረጋገጠ ነው።

እንደ ሚስዮን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ላይ፣ እናንተም እምነትን እና ፅናትን፣ ብርቱነትን እና ልበ ሙሉነትን፣ ቆራጥነት እና ዘላቂነት፣ ወሳኝነትን እና ተግባራዊነትን ትጨምራላችሁ። ተግባራዊ የሆኑ ሚስዮኖች በሚስዮን ቦታ ውስጥ ታዕምራቶችን ለማምጣት ይችላሉ።

ፕሬዘደንት ጆን ቴይለር [1808–87 (እ.አ.አ)] ለሚስዮኖች አስፈላጊ ባህሪያት የሆኑትን እንዲህ ዘርዝረዋል፥ “የወንጌል ተሸካሚ እንዲሆኑ የምንፈልጋቸው ወንዶች [እና ሴቶች እና የተጋቡ አገልጋዮች] በእግዚአብሔር እምነት ያላቸው ሰዎች፤ በሀይማኖታቸው እምነት ያላቸው ሰዎች፤ ክህነታቸውን የሚያከብሩ ወንዶች፤ እግዚአብሔርም ሊያምንባቸው የሚችሉ ሰዎች ናቸው። በመንፈስ ቅዱስ እና በእግዚአብሔር ሀይል የተሞሉ ሰዎችን[፣]… የክብር፣ አቋም ያላቸውን፣ እና የምግባረ መልካምነትና ንጹህነት ሰዎችን እንፈልጋለን።”2

ጌታ እንዳወጀው፥

“ስለሆነም እነሆ እርሻው ነጥቷል አዝመራውም ዝግጁ ነው፤ እናም አስተውሉ፣ በጥንካሬው የሚያጭድ እንዳይጠፋ ዘንድ በጎተራው ይከምራል፣ ነገር ግን ለነፍሱ ደህንነትን ያመጣል፤

“እናም እምነት፣ ተስፋ፣ ለጋስነትና ፍቅር፣ ሙሉ አይኑን ወደ እግዚአብሔር ክብር ከማድረግ፣ ጋር ለስራው ብቁ ያደርጉታል።” (ት. እና ቃ. 4፥4–5)።

ጥሪአችሁ የመጣው በመንፈስ ምሪት ነው። እግዚአብሔር የጠራውን፣ እግዚአብሔር ብቁ እንደሚያደርገው እመሰክራለሁ። በጌታ አትክልት ስፍራ ውስጥ በጸሎት ስትተጉ የሰማይ እርዳታን ትቀበላላችሁ።

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያለውን፣ በዚህ ዘመን መጀመሪያ ላይ ለሚስዮኖች ጌታ የሰጠው አስደሳች ቃል ኪዳን የእናንተ ይሆናል፥ “በፊታችሁም እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል” (ት. እና ቃ. 84፥88)።

ስታገለግሉ፣ የበለጸገ ዘለአለማዊ ትዝታዎችን እና ጓደኝነትን ትገነባላችሁ። እንደ ሚስዮን ቦታ ታላቅ ስጦታ የሆነ የደስታ አዝመራን የሚያምርት ምንም ቦታ አላውቅም።

አሁን ለማንኛውም ምክንያት በሚስዮን ቦታ የተመደቡበትን ጊዜ ለመፈጸም ለማይችሉት ለካህናት፣ ለእህቶች፣ እና ለተጋቡ ሚስዮኖች፥ ጌታ ይወዳችኋል። ለመስዋዕታችሁ ምስጋና አለው። ተስፋ የሚያስቆርጣችሁን ያውቀዋል። ልታደርጉት የምትችሉት ስራ ከእርሱ እንዳላችሁ እወቁ። ሰይጣን ሌላ ነገር እንዳይነግራችሁ አትፍቀዱ። ዝቅ አትበሉ፤ አትደናቀፉ፤ ተስፋ አትቁረጡ።

ቤተክርስቲያኗን ለመምራት ከተጠራሁ ከአጭር ጊዜ በኋላ እንዳልኩት፥ “አትፍሩ። ተደሰቱ። ከፊታችሁ ያለው እንደ እምነታችሁ ብሩህ ነው።”3 ያም ቃል ኪዳን አሁንም ለእናንተ እውነት ነው። ስለዚህ እምነታችሁን እንዳታጡ አድርጉ፣ ምክንያቱም ጌታ በእናንተ ላይ እምነትን አላጣምና። ቃል ኪዳኖቻችን ጠብቁ እናም ወደፊት ሂዱ።

አለም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያስፈልጋታል። ጌታ፣ የትም ብናገለግል፣ የሚስዮን ልብ ያላቸውን ቅዱሳኑን በሙሉ ይባርካል።

ማስታወሻዎች

  1. ሒበር ሲ ኪምባል፣ በኦርሰን ኤፍ ውትኒ፣ Life of Heber C. Kimballውስጥ፣ 3rd ed. (1967)፣ 104።

  2. Teachings of Presidents of the Church: John Taylor (2001)፣ 73።

  3. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Be of Good Cheer፣” Liahona፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 92።

አትም