የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ ጉብኝት መልእክት፣ ሰኔ 2017 (እ.አ.አ)
የክህነት ሀይል ቃል ኪዳኖችን በመጠበቅ
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?
የአስራ ኡለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “ለሁሉም ያለኝ መልእክት ቢኖር፣ ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ እኛ እያንዳንዱን ሰዓት ‘በክህነት ሀይል ጥንካሬ በመባረክ፣’ ለመኖር መቻላችን ነው፣” ብለዋል።
“… በብቁነት በክህነት ስርዓት ስትሳተፉ፣ ጌታ ታላቅ ጥንካሬ፣ ሰላም፣ እና ዘለአለማዊ አስተያየት ይሰጣችኋል። “ጉዳያችሁ ምንም ቢሆን፣ ቤታችሁ ‘በክህነት ሀይል ጥንካሬ ይባረካል።’”1
የክህነት ሀይልን ወደ ህይወታችን እንዴት ለመጋበዝ እንችላለን? የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንድናስታውስ እንዳደረጉት፣ “ወደ ጥምቀት ውሀ የገቡት እና ቀጥለውም በጌታ ቤት መንፈሳዊ በረከትን የተቀበሉት ሀብትን እና አስደናቂ በረከቶችን ለመቀበል ብቁ ናቸው። መንፈሳዊ ስጦታ በእውነትም የሀይል ስጦታ ነው … [እናም] የሰማይ አባታችን በሀይሉ ለጋስ ነው።” ወንዶች እና ሴቶች በቤተመቅደስ ውስጥ “በትርጉም የክህነት ሀይል በሆነው በአንድ አይነት ሀይል እንደሚባረኩ” እንድናስታውስ አድርገውናል።2
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሊንዳ ኬ. በርተን እንዳሉት፥ “የክህነት ሀይል ሁላችንም በቤተሰባችን እና እቤታችን ውስጥ፡ለማግኘት የምንፈልገው ስለሆነ፣ ያን ሀይል በህይወታችን ውስጥ ለመጋበዝ እኛ ምን ማድረግ ያስፈልገናል? የክህነት ሀይልን ለማግኘት የግል ጻድቅነት አስፈላጊ ነው።”3
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ ፕሬዘደንት “በትሁትነት ራሳችንን በጌታ ፊት ስናቀርብ እና እንዲያስተምረን ስንጠይቀው፣ የእርሱን ሀይል ለማግኘት የምንችልበትን ለማሳደግ እኛ ምን ለማድረግ እንደምንችል ያሳየና” ብለዋል።4
ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ
1ኔፊ 14፥14፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36፤ 132፥20: reliefsociety.lds.org
© 2017 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message, June 2017 ትርጉም። Amharic። 97926 506