2017 (እ.አ.አ)
ጓደኛዬ በሞተ ጊዜ
ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ጓደኛዬ በሞተ ጊዜ

ጸሃፊዋ በዩታ፣ ዩ. ኤስ. ኤ. ነው የምትኖረው።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በአስራ አንደኛው ክፍሌ፣ ጓደኛዬ በአንጎል የደም መርጋት ታመመች እና በሚቀጥለው ቀን ሞተች። የቤተክርስቲያኗ አባል ብሆንም፣ እታገል ነበር። በህይወቴ በሙሉ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ አዳኝ ለማንኛውም ነገር ለመሄድ እንደምችል ተምሬ ነበር፣ ነገር ግን ከዚህ በፊት እንደዚህ የሆነን ነገር በህይወቴ መጥቶ አያውቅም ነበር።

ሰላም የሚሰጠኝ አንድ ነገር—ምንም ነገር—ለማግኘት በመጣር፣ ለብዙ ሰዓቶች አለቀስኩኝ። ከሞተች በኋላ በሚቀጥለው ምሽት፣ ወደ መዝሙር መፅሀፍ ሄድኩኝ። ገጾቹን ስገልጥ፣ “Abide with Me፤ ’Tis Eventide” በሚለው መዝሙር ላይ አረፍኩኝ (Hymns፣ no. 165)። ሶስተኛው አንቀጽ በጣም ነካኝ፥

ከእኔ ጋር ሁን፤ ምሽት ነውና፣

ምሽቱ ብቸኛ ነውና

ከአንተ ጋር ለመገናኘት ካልቻልኩኝ፣

ወይም ብርሀኔን በአንተ ካላገኘሁኝ።

የምፈራው የአለም ጭለማ፣

በቤቴ ይኖራል ብዬ እፈራለሁ።

አዳኝ ሆይ፣ በዚህ ምሽት ከእኔ ጋር ሁን፤

እነሆ፣ ምሽት ነውና።

ይህ አንቀጽ በብዙ ሰላም ሞላኝ። በዚያ ምሽት አዳኝ ከእኔ ጋር መገኘቱን ብቻ ሳይሆን ነገር ግንእኔ ምን እንደሚሰማኝ እንደሚያውቅ ተደራሁኝ። በመዝሙሩ የተሰማኝ ፍቅር በዚያ ምሽት እንድረዳ ከማድረግ በተጨማሪ በጸናኋቸው ሌሎች ፈተናዎች በሙሉ እንድረዳ እንዳደረገኝ አውቃለሁ።

አትም