2017 (እ.አ.አ)
በደንብ የመፅናት ሽልማት
ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)

በደንብ የመፅናትሽልማት

በወጣትነቴ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ጠቢብ ለሆነ የዲስትሪክት መሪ እንደ አማካሪ አገለግል ነበር። ሁልጊዜም ሊያስተምረኝ ይጥር ነበር። በአንድ ውቅት የሰጠኝን ምክር አስታውሳለሁ፥ “ከሰው ጋር ስትገናኝ፣ እነርሱን በመጥፎ ችግር ውስጥ እንዳሉ አድርገህ ተመልከታቸው፣ እናም ከግማሽ በላይ ለሚሆን ጊዜ ትክክል ትሆናለህ።” እርሱ ክፉ አሳቢ ነው ብዬ አስብ ነበር። አሁን፣ ከ50 አመት በኋላ፣ አለምን እና ህይወትን እንዴት በደንብ እንደተረዳ ይገባኛል።

ሁላችንም የሚያጋጥሙን ፈተናዎች አሉን—አንዳንድ ጊዜም በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ፈተናዎች ናቸው። እኛ ከእርሱ ጋር ለዘለአለም ለመኖር እንችል ዘንድ እንድንጸዳ እና ፍጹም እንድንሆን ጌታ እንድንፈተን እንደሚፈቅድ እናውቃለን።

ጌታ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን በሊብርቲ እስር ቤት ውስጥ ፈተናዎቹን የመፅናት ሽልማት ለዘለአለም ህይወት ብቁ ለማድረግ እንደሚረዳው አስተምሮታል፥

“ልጄ፣ በነፍስህ ሰላም ይኑርህ፤ ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ነው፤

“ከእዚያም፣ በመልካም ይህን ከጸናህ፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ከፍ ያደርግሀል፤ ጠላቶችህንም በሙሉ ታሸንፋቸዋለህ” (ት. እና ቃ. 121፥7–8).

በህይወት ውስጥ ብዙ ነገሮች ስለሚደበድቡን በደንብ ለመፅናት አስቸጋሪ ይመስል ይሆናል። ዝናብ በሌለበት ጊዜ በሰብሎች ላይ ለሚመካ ቤተሰብም እንዲህ ይመስል ይሆናል። እነርሱም “ለምን ያህል ጊዜ ለመቋቋም እንችላለን? ብለው ያስቡ ይሆናል። እያደገ ያለውን የቆሻሻ እና የፈተናዎች ጎርፍ መቋቋምን ለሚጋፈጠው ወጣትም እንዲሁ ሊመስለው ይችላል። ባለቤት እና ቤተሰብን ለመደገፍ የሚያስፈልገውን ስራ ለማግኘት የሚረዳውን ትምህርት ወይም ስልጠና ለማግኘት ለሚታገለው ወጣትም እንዲሁ ሊመስለው ይችላል። ስራ ለማግኘት ለማይችለው ወይም ስራው ወይም ንግዱ ከተዘጋ በኋላ ከስራ ለወጣውም ሰው እንዲሁ ሊመስል ይችላል። በህይወት መጀመሪያ ወይም ከጊዜ በኋላ ለእነርሱ ወይም ለሚያፈቅሯቸው ለሚመጣባቸው፣ ጤንነታቸው እና የሰውነት ጥንካሬአቸው ለሚወድቅባቸውም እንዲሁ ሊመስል ይችላል።

ነገር ግን የሚያፈቅር እግዚአብሔር እንደዚህ አይነት ፈተናዎች በፊታችን ያቀረበው ችግሮችን ለመፅናት መቻላችንን ለማየት ሳይሆን እነዚህን በደንብ ለመፅናት እና በዚህም ለመጽዳት እንደምንችል ለማየት ነው።

ሽማግሌ ፓርሊ ፒ. ፕራት (1807-57) እንደ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል በተጠሩበት ጊዜ የቀዳሚ አመራር እንዳስተማሯቸው፥ “ትኩረትህን በሙሉ በሚያስፈልገው ስራ ላይ ነው የተሳተፍከው፤ … የተወለወለ ምሶስ ሁን። … በፍጹም ለመወልወል ብዙ ችግሮች፣ ብዙ ስራዎች፣ እና ብዙ ስቃዮችን መፅናት አለብህ። … የሰማይ አባትህ ይህን ይፈልጋል፤ ሜዳው የእርሱ ነው፤ ስራው የእርሱ ነው፤ እናም እርሱም… ያፅናናሀል … እናም ከፍ ያደርግሀል።”1

በዕብራውያን መፅሐፍ ውስጥ፣ ጳውሎስ በደንብ ከመፅናት ስለሚመጣው ፍሬ ተናግሯል፥ “ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” (ዕብራውያን 12፥11)።

ፈተናዎቻችን እና ችግሮቻችን ለመማር እና ለማደግ እድል ይሰጡናል፣ እናም የእኛንም ፍጥረትን ለመቀየር ይችላሉ። በስቃያችን ወደ አዳኝ ለመዞር ከቻልን፣ ስንጸና ነፍሳችን ይወለወላል።

ስለዚህ፣ መጀመሪያ ማስታወስ የሚያስፈልገው ሁልጊዜ መጸለይ ነው ( ት. እና ቃ. 10፥5፤ አልማ 34፥19–29 ተመልከቱ)።

ተቃውሞው፣ ፈተናው፣ ወይም በአካባቢያችን ያለው ሁከታ ምንም ቢሆን፣ ሁለተኛው ነገርትእዛዛትን ለመጠበቅ መጣር ነው ( ሞዛያ 4፥30 ተመልከቱ)።

የሚደረገው ሶስተኛው አስፈላጊ ነገርም ጌታን ማገልገል ነው ( ት. እና ቃ. 4፥220፥31ተመልከቱ)።

በመምህር አገልግሎት ውስጥ፣ እርሱ ለማወቅ እና ለማፍቀር እንችላለን። በጸሎት እና በእምነት አገልግሎት ከጸናን፣ የአዳኝን እጅ እና የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ተፅዕኖን ማወቅ እንጀምራለን። የቤተክርስቲያኗ ለጊዜ እንዲህ አይነት አገልግሎት ሰጥተናል እናም ያ ጓደኝነት ተሰምቶናል። ስለዚያ ጊዜ ስታስቡ፣ በእናንተ ውስጥ ለውጥ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። ክፉ ለማድረግ ያለው ግፊት የቀነሰ ይመስላል። መልካም የማድረግ ፍላጎት ይጨምራል። እናንተን በደንብ የሚያውቁትና የሚያፈቅሯችሁም ስለእናንተ እንዲህ ይላሉ፥ “እናንተ በተጨማሪ ደግ እና ትእግስተኛ ሆናችኋል። አንድ አይነት ሰውም አትመስሉም።”

እናንተ አንደዚህ አይነት ሰው አልነበራችሁም። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ተቀይራችኋል ምክንያቱም በፈተናችሁ በእርሱ ላይ ተመክታችኋልና።

እርሱን ከፈለጋችሁ እና ካገለገላችሁ፣ ጌታ በፈተናችሁ እናንተን ለመርዳት እንደሚመጣ እናም በዚህ ሂደት ነፍሳችሁ እንደሚያጸዳ ቃል እገባላችኋለሁ። በፈተናዎቻችሁ ሁሉ እምነታችሁን በእርሱ ላይ እንድትጥሉ አብረታታችኋለሁ።

እግዚአብሔር አብ ህያው እንደሆነ እና እያንዳንዱን ጸሎቶች እንደሚሰማና እንደሚመልስ አውቃለሁ። ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የኃጢያቶቻችንን ሁሉ ዋጋ እንደከፈለ እና ወደ እርሱ እንድንመጣ እንደሚፈልግ አውቃለሁ። አብ እና ወልድ እኛን እንደሚጠብቁና በደንብ የምንጸናበት እና ወደ ቤት እንደገና የምንመጣበትን መንገድ እንዳዘጋጁልን አውቃለሁ።

ማስታወሻ

  1. Autobiography of Parley P. Pratt፣ ed. ፓርሊ ፒ. ፕራት ዳግማዊ (1979)፣ 120።

አትም