2017 (እ.አ.አ)
አንድ ይሆኑ ዘንድ
ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)

አንድ ይሆኑ ዘንድ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?

ምስል
Relief Society seal

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዳስተማሩት፣ “ኢየሱስ ከአብ ጋር ፍጹም አንድነትን፣ በስጋ እና በመንፈስ፣ ያገኘው ለአብ ፈቃድ ራሱን ታዛዥ በማድረግ ነው።”

“… የእነርሱን ፍላጎት የእኛ ታላቅ ፍላጎት እስከምናደርገው ድረስ፣ በእርግጥም ከእግዚአብሔር እና ከክርስቶስ ጋር አንድ አንሆንም። እንደዚህ አይነት ተቀባይነት በአንድ ቀን የሚደረስበት አይደለም፣ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ በኩል፣ በጊዜ አብ በእርሱ ነው እንደሚባለው እርሱ በእኛ ነው እስከሚባል ድረስ፣ ፈቃደኛ ከሆንን ጌታ ያስተምረናል።”1

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሊንዳ ኬ. በርተን ወደዚህ አንድነት እንዴት እንደምንሰራ አስተምረዋል፥ “ቃል ኪዳኖቻችንን መግባት እና መጠበቅ እንደ አዳኝ ለመሆን ያለንን የልብ ውሳኔ የምንገልጽበት ነው። የሚስማማው ነገር ቢኖር በሚወደደው መዝሙር ሀረጎች ውስጥ የሚገለጹትን አስተሳሰብ ለማግኘት በመጣር ነው፥ ‘ አንተ በምትፈልገኝ ኤዳለሁ። … አንተ እንድናገር የምትፈልገውን እላለሁ። … አንተ እንድሆን በምትፈልገኝ እሆናለሁ።’”2

ሽማግሌ ክርስቶፈርሰን እንዳስታወሱን፣ “የክርስቶስን መንገድ ቀን ተቀን እና በየሳምንቱ ለመከተል ስንጥር፣ መንፈሳችን የራሱን መብለጥ ያረጋግጣል፣ በውስጣችን ያለው ጦርነት ረጋ ይላል፣ እናም ፈተናዎች ማስቸገራቸውን ያቆማሉ።”3

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ኔል ኤፍ. ሜሪያት ፍላጎታችንን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ጋር ለማሰለፍ በመጣር ስለሚመጡ በረከቶች እንደመሰከሩት፥ “ነገሮችን በራሴ መንገድ የመፈለግ የስጋዊ ፍላጎትን ለማጥፋት ታግዬ ነበር፣ በመጨረሻም የእኔ መንገድ ከኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ እጥረት ያለው፣ የተገደበ፣ እና ታናሽ እንደሆነ ተረዳሁ። ‘[የሰማይ አባታችን] መንገድ በዚህ ህይወት ወደ ደስታ እና በሚመጣው አለም ወደ ዘለአለም ህይወት የሚመራ መንገድ ነው።’”4 ከሰማይ አባታችን እና ከልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ጋር አንድ ለመሆን በትህትና እንጣር።

ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ

ዮሀንስ 17፥20–21ኤፌሶን 4፥13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥27፤ reliefsociety.lds.org

ማስታወሻዎች

  1. ዲ. ቶድ ክርስትፈርሰን፣ “That They May Be One in Us፣” Liahona፣ ህዳር 2002 (እ.አ.አ)፣ 72፣ 73።

  2. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ “The Power፣ Joy፣ and Love of Covenant Keeping፣” Liahona፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 111።

  3. ዲ. ቶድ ክርስትፈርሰን፣ “That They May Be One in Us፣” 71።

  4. ኔል ኤፍ. ሜሪያት፣ “Yielding Our Hearts to God፣” Liahona፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 32።

አትም