2018 (እ.አ.አ)
ለእያንዳንዷ እህት በስም ጸልዩ
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መሰረታዊ መርሆች፣ መጋቢት 2018 (እ.አ.አ)

ለእያንዳንዷ እህት በስም ጸልዩ

ለእያንዳንዷ እህት በስሟ በትህትና ስንጸልይ በጉብኝት ለምናስተምራቸው ፍቅራችን እና የመንፈስ ምሪት ይጨምራል።

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

ቅዱሳት መጻህፍት ለሌሎች በስም ለጸለዩ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ምሳሌዎች ይጋራሉ። በጣም ድራማዊ ከሆኑት ውስጥ የወጣቱ አልማ አባት ነው። መልአክ ለወጣቱ አልማ እንዲህ በማለት ተናገረው፣ አባቱ ስለአንተ እምነት በመስጠት እጅግ አብልጦ ይጸልያል ፤ ስለዚህ፣ ለዚህ ዓላማ የእግዚአብሔርን ኃይልና ስልጣን ለማሳመን መጣሁ፣ በእምነታቸው የተነሳ የአገልጋዮቹ ፀሎት መልስ ያገኝ ዘንድ። (ሞዛያ 27፥14)።

እርስ በእርስ መጸለያችን ጌታ ሊሰጠን የሚፈልጋቸውን በረከቶች ለመቀበል ልባችንን ይከፍታል። የጸሎት አላማው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለወጥ አይደለም፣ ነገር ግን ለእኛ እና ለሌሎች እግዚአብሔር ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነውን በረከቶች ለማግኘት ነው፣ ነገር ግን እነዚህን ለማግኘት የግድ መጠየቅ አለብን።1

አንዲት እህት በህይወቷ አስቸጋሪ ጊዜ፣ በስልክ ወይም ቀላል የጽሑፍ መልእክት ከሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎችዋ በተለይም ጨለማ በሆኑ ቀናት እንደመጣ ተናግራለች። ከፍ መደረግን በትክክል መቼ እንደሚያስፈልጋት ያወቁ ይመስላል። በጉብኝትም ጊዜ ሆነ በራሳቸው ጊዜ ለእርሷ መጸለያቸውን ታውቃለች።

እያንዳንዷ እህት በየቀኑ እና በሌሊት በልባዊ ጸሎት ብትጸልይ ወይም ፣ በተሻለም፣ ጌታ እንዳዘዘው ያለማቋረጥ የምትጸልይ ከሆነ፣ የሚኖረውን የጋራ ጥንካሬን አስቡት የቀድሞው የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ጁሊ ቢ. ቤክ።2 ለምንጎበኟቸው ሰዎች መጸለያችን በግልም እና እንደ የኋለኛው ቀን ሴቶች ያጠነክረናል።

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ እንደተናገሩት፥ ልባቸውን ለማወቅ መንገዱን ይጸልዩ። እነርሱን ለመርዳት እና እግዚያብሄር ለነርሱ ባለው ፍቅር ስሜት በቻላችሁት መጠን ሁሉንም በማድረግ እግዚያብሄር እንድታደርጉ የሚያደርገውን ማወቅ አለባችሁ።”3

ማስታወሻዎች

  1. የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ጸሎት”

  2. Julie B. Beck, “What Latter-day Saint Women Do Best: Stand Strong and Immovable,” Liahona, Nov. 2007, 110.

  3. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “ክህነት እና የግል ጸሎት፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 85።