2021 (እ.አ.አ)
ወደ ራዕይ መርህ እደጉ
ጥር 2021 (እ.አ.አ)


“ወደ ራዕይ መርህ እደጉ፣” ሊያሆና፣ ጥር 2021(እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ጥር 2021(እ.አ.አ)

ወደ ራዕይ መርህእደጉ

ጌታ ሊሰጣችሁ የሚፈልገውን መገለጥ ትቀበሉ ዘንድ በተሻለ መልኩ እና በብዛት ለመስማት አስፈላጊ ተግባሮች እንድታደርጉ አበረታታችኋለለሁ።

ተክል

ምስል ከ Getty Images

በመስከረም 30፣ 2017፣ ከአጠቃላይ ጉባኤው የከሰዓት ክፍለ ጊዜ በኋላ፣የምወደው የአስራ ሁለቱሃዋርያት ጉባኤ አባል ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማየት ሆስፒታል ጋር ወረድኩ። ከጥቂት ቀናት በፊት የልብ ህመም ካጋጠመው ጀምሮ በሆስፒታል ሲታከም ነበረ።

አስደሳች ጉብኝት ነበረን፣ እና እየተሻለው ይመስል ነበር። እንዲሁም በራሱ ሲተነፍስ ነበር፣ ይህም ጥሩ ምልክት ነበር።

ሆኖም በዚያ ምሽት፣ አሁድ ወደ ሆስፒታሉ መመለስ እንዳለብኝ መንፈስ ለልቤ እና ለአእምሮዬ ተናገረኝ። በእሁድ ማለዳው የአጠቃላይ ጉባኤ ክፍለ ጊዜ ወቅት፣ ያ ጠንካራ ስሜት ተመለሰ። ምሳን መዝለል እና የማለዳው ክፍለ ጊዜ እንዳበቃ ወደ ሽማግሌ ሄልስ አልጋ በፍጥነት መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ፣ ሄድኩም።

በደረስኩበት ወቅት፣ ሽማግሌ ሄልስ ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደገባ ማየት ቻልኩኝ። በሚያሳዝን መልኩ፣ ከደረስኩኝ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ አረፈ፣ ነገር ግን ባረፈበት ወቅት ከውድ ሚስቱ ከሜሪ፣ እና ከሁለት ልጆቻቸውጋር በመሆንጎአጠገቡ ስለነበርኩ አመስጋኝ ነኝ።

የመንፈስ ቅዱስ ሹክሹክታ በሌላ መንገድ ላደርግ የማልችለውን ነገር እንዳደርግ ስላነሳሳኝ ምንኛ አመስጋኝ ነኝ። እናም ስለመገለጥ እውነታ እና ሰማያት ድጋሚ ስለመከፈታቸው ምንኛ አመስጋኝ ነኝ።

በዚህ ዓመት የግል እና የመማሪያ ክፍል ጥናት ትኩረታችን የሚሆነው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ነው። እነዚህ “የመለኮት ራዕዮች እና በመንፈስ አነሳሽነት የተነገሩ አዋጆች” የሚያጠኗቸውን እና በሚሰጡት መለኮታዊ ምሪቶች ላይተግባራዊ እርምጃ የሚወስዱ ሁሉ ይባርካሉ። “ሁሉም ሰው በሁሉም ቦታ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ድምፅን እንዲሰማ፣” ይጋብዛሉ1 ምክንያቱም በእውነት “የጌታ ድምፅ ለሁሉም ሰው ነውና” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 1፡2)።

አደጋ፣ ጨለማ፣ ማታለል

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳስታወሰን አካላዊ እና መንፈሳዊ አውሎ ነፋሶች በምድር ላይ የህይወት ክፍሎች ናቸው። ከዳግም ምጽዓቱ አስቀድሞ ስለሚሆነው በተመለከተ፣ አዳኙ ታላቅ የመከራ ቀናት እንደሚኖሩ ተንብዩዋል። “ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” ብሏል (ጆሴፍ ስሚዝ—ሜቴዎስ 1፡29)።

ይህንን መከራ የሚያባብሰውእየጨመረ የመጣው በዙሪያችን ያለው ጨለማ እና ማታለል ነው። ኢየሱስ ለደቀማዛሙርቱ እንደነገራቸው፣ ከመመለሱ በፊት “ክፋት ይበዛል” (ጆሴፍ ስሚዝ—ሜቴዎስ 1፡30)።

ሰይጣን ያለውን ሃይል አደራጅቶ የጌታን ስራ እና በጌታ ስራ የተጠነመድነውን በመቃወም ላይ ነው። እየገጠሙን ያሉት አደጋዎች እየጨመሩ በመምጣታቸው፣ መለኮታዊ ምሪት ለማግኘት ያለን ፍላጎትከዚህ በላይ ሆኖ አያውቅም እንዲሁም—የእኛን አማላጅ፣ አዳኝ እና መድሃኒትየሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን—ድምፅ ለመስማት የምናደርገው ጥረት አንዳሁኑ ጊዜ ያሀል አስቸኳይ ሆኖ አያውቅም።

የቤተክርስቲያኑ ፕሬዘዳንት ተብዬ እንደተጣራሁ ብዙም ሳልቆይ እንዳልኩት፣ ጌታ ሃሳቡን ለእኛ ለመግለፅ ዝግጁ ነው። ያ እኛን ከባረከበት ታላላቅ በረከቶች ውስጥ አንዱ ነው።2

በእኛ ቀን፣ “ብትጠይቁ፣በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ትቀበላላችሁ” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፡61)ሲል ቃል ገብቷል።

ለልመናዎቻችን ምላሽ እንደሚሰጥ አውቃለሁ።

እርሱን እንዴት እንደምንሰማው

መንፈስ እንዴት እንደሚናገር ማወቅ ዛሬ ላይ አስፈላጊ ነው። የግል ራዕይ ለመቀበል፣ መልሶችን እና ጥበቃን ለማግኘት እንዲሁም አቅጣጫን ለመቀበል ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ያስቀመጠልንን ንድፍ እናስታውሳለን።

በመጀመሪያ፣ በቅዱሳን መፅሃፍት ውስጥ ራሳችንን እናጠልቃለን። ይህ ማድረግ አእምሯችንን እና ልባችንን ለአዳኝ ትምህርቶች እና እውነቶች ክፍት ያደርግልናል። የክርስቶስ ቃል “[እኛ] ማድረግ ያለብንን ነገሮች ሁሉ [ለእኛ] ይነግረናል” (2 ኔፊ 32፡3)፣ በተለይም በዚህ እርግጠኛ በማይኮንባቸው እና በሁከት ወቅት።

በመቀጠልም እንፀልያለን። ፀሎት መነሳሳትን ይጠይቃል፣ ስለዚህም ራሳችንን በጌታ ፊት በትህትና ዝቅ እናደርጋለን፣ በመደበኛነት ልንሄድ የምንችልበት ፀጥ ያለ ቦታ እንፈልጋለን እናም ልባችንን ወደ እርሱ እናፈሳለን።

ጌታ “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ፤ ለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል” ይላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88:63)።

ወደ ጌታ መቅረብ መጽናኛን፣ ማበረታቻን፣ ተስፋን እና ፈውስን ያመጣል። ስለዚህም፣ ስል ጭንቀቶቻችን እና ስለድካሞቻችን፣ ስለናፍቆታችን እና ስለምንወዳቸው ሰዎች፣ ስለጥሪያችን እና ስለጥያቄዎቻችን በስሙ እንጸልያለን።

ከዛም እናዳምጣለን።

ፀሎታችንን ከጨረስን በኋላ ለጥቂት ጊዜ በጉልበቶቻችን ተንበርክከን የምንቆይ ከሆነ፣ ሃሳቦች፣ ስሜቶች እና አቅጣጫ ወደአእምሯችን ይመጣሉ። እነዚህ ግንዛቤዎች መመዝገብ ጌታ እንድንወስዳቸው የሚፈልገውን እርምጃዎች ማስታወስ እንድንችል ይረዱናል።

የምታጠና ሴት

ይህን ሂደት በመድገም ላይ ሳለን፣ በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቃሎች “ወደ ራዕይ እናድጋለን።”3

ራዕይ ለመቀበል ብቁ የሆነ

የመንፈስ ቅዱስን የሚያንሾኳሹክ ድምጽ የመለየት ችሎታችንን ማጥራት እና ራዕይ የመቀበል አቅማችንን ማሳደግ ብቁነትን ይጠይቃል። ብቁነት ፍፁምናን አይጠይቅም፣ ነገር ግን ለበለጠ ንፁህና መጣርን ይጠይቅብናል።

ጌታ እለታዊ ጥረት፣ እለታዊ መሻሻል፣ እለታዊ ንሰሃ ይጠብቃል። ብቁነት ንፁህነትን ያመጣል እና ንፁህነት ለመንፈስ ቅዱስ ያበቃናል። “መንፈስ ቅዱስን ለ [እኛ] መሪ” አድርግን ስንወስድ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45:57)፣ ለግል ራዕይ ብቁ እንሆናለን።

የሰማያዊ መመሪያ በርን ከመክፈት እያስቆመን ያለ ነገር ካለ፣ ንስሃ መግባት ሊያስፈልገን ይችላል። ንሰሃ የጌታን ድምጽ በተደጋጋሚ እና በግልፅ መስማት እንችል ዘንድ በሩን እንድንከፍት ይረዳናል።

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ አባል ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “መለኪያው ግልፅ ነው፣” ሲሉ አስተምረውናል። “የሆነ የምናስበው፣ የምናየው፣ የምንሰማው ወይም የምናደርገው ነገር ከመንፈስ ቅዱስ የሚያርቀን ከሆነ፣ ያንን ነገር ማሰብ፣ ማየት፣ መስማት እና ማደረግ ማቆም አለብን። ያ ለማዝናናት የታሰበው ነገር፣ ለምሳሌ ከመንፈስ ቅዱስ የሚለየን ከሆነ፣ ይህ አይነት መዝናናት ለእኛ አይሆንም። በብልግና፣ በጨካኝ ወይ ጨዋነት በጎደለው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ማደር ስለማይችል፣ በግልፅ እነዚህ ነገሮች ለእኛ የተገቡ አይደሉም።”4

ከፍ ያለ ንጽህና እና መታዘዝን ከፆም፣ በትጋት ከመፈለግ፣ ቅዱሳን መፅሃፍትን እንዲሁም የህያው ነብያትን ቃላት ከማጥናት እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን ከመስራት ጋር ሲጣመር፣ ሰማያት ይከፈታሉ። ጌታም በምላሹ፣ ቃል ኪዳኑን ይፈፅማል፡ “አእምሮህን እንዲያበራ፣ ነፍስህን በደስታ እንዲሞላ ከመንፈሴ እሰጥሃለሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11:13)።

መታገስ ያስፈልገን ይሆናል፣ ነገር ግን እግዚአብሄር በራሱ መንገድ በራሱ ጊዜ ይናገረናል።

የመረዳት መንፈስ

ኢዮብ፣ “በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፦ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክም ማስተዋል ይሰጣቸዋል” ብሎ ተናግሯል(ኢዮብ 32:8)። በዚህ አዲስ አመት፣ ጌታ ሊሰጣችሁ የሚፈልገውን መገለጥ ትቀበሉ ዘንድ በተሻለ መልኩ እና በብዛት ለመስማት አስፈላጊ ተግባሮች እንድታደደርጉ አበረታታችኋለሁ።

ሽማግሌ ሄልስ በጥቅምት 2017 ከማለፉ በፊት፣ ለአጠቃላይ ጉባኤ አጭር ንግግር ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም ማድረግ አልቻለም። በዚያ ንግግር፣ “እምነታችን በጌታ መገኘት ውስጥ እንድንሆን ያዘጋጀናል ብሎ ፅፏል።”5

ራዕይን ስንቀበል፣ ሃሳቡን ሲገልጥልን፣ፍላጎቱን ሲያሳውቀን እና ድምፁን ሲያሰማን በእግዚያብሄር ህልውና ውስጥ ጊዜን እናሳልፋለን ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68:4) ን ይመልከቱ። እርሱን በመጥራት፣ ቃል የገባውን የመገለጥ ህይወት በመኖር እና በተቀበልነው ምሪት መሰረት በመስራት እምነታችን በተግባር ላይ እናውል።

ማስታወሻዎች

  1. የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መግቢያ

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ፣ ራዕይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.ኤ.አ)፣ 94 ን ይመልከቱ።

  3. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ (2007)(እ.አ.አ)፣ 132።

  4. ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “ሁልጊዜ የእርሱ መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲሆን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2006(እ.አ.አ)፣ 30።

  5. በኔይል ኤል. አንዴርሰን፣ “የጌታ ድምፅ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017(እ.አ.አ)፣ 125።