2021 (እ.አ.አ)
መስማት፣ ማዳመጥ፣ መከተል
ጥር 2021 (እ.አ.አ)


“መስማት፣ ማዳመጥ፣ መከተል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ጥር 2021(እ.አ.አ), 32።

ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥር 2021(እ.አ.አ)

መስማት፣ ማዳመጥ፣ መከተል

ምስል
በመስበኪያ ሰገነት መስማት፣ ማንበብ እና መናገር

ምስል በ Guev Design

በትምህርት እና ቃልኪዳኖች የሚገኘው የመጀመሪያው ቃል አዳምጡ የሚል ነው( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 1:1።) ን ይመልከቱ። ይህም ማለት “ለማዳመጥ መስማት” ማለት ነው። ማድመጥ ማለት “እርሱን መስማት”—አዳኝ የሚለውን ማድመጥ እና ከዚያም የእርሱን ምክር መከተል ማለት ነው። “እርሱን ስሙት” በሚሉት በእነዚያ ሁለት ቃላት፣ እግዚአብሔር ለዚህ ህይወት ውጤታማነት፣ ደስታ፣ እና ሀሴት ንድፍ ሰጥቶናል። የጌታን ቃል መስማት አለብን፣ እነርሱንም ማድመጥ እና እርሱ የነገረንን መከተል አለብን።

እርሱን ለመስማት የት መሄድ እንችላለን ?

ወደ ቅዱሳት መጻህፍት ለመሄድ እንችላለን። ደግሞም በቤተመቅደስ ውስጥም እርሱን መስማት እንችላለን። የመንፈስ ቅዱስን ሹክሹክታ ለመለየት ያለንን ችሎታ ስናሳድግ፣ በግልፅ እርሱን መስማት እንችላለን። እናም በመጨረሻም፣የነቢያትን፣ የባለራዕያትን፣ እና የገላጮችን ቃላት ስንከተል እርሱን እንሰማዋለን

አዳኙ የተናገረውን፣ እና አሁን በነቢያቱ በኩል የሚናገረውን ሆን ብለን በበለጠ ለመስማት፣ ለማድመጥ እና ለመከተል ስንጥር ምን ይሆናል? ፈተናን፣ ትግልን እና ድክመትን ለመቋቋም በተጨማሪ ኃይል እንደምትባረኩ ቃል እገባለሁ። በቤተሰቦቻችሁ ግንኙነቶች፣ እና በየዕለቱ ስራዎቻችሁ ተዓምራትን እንደምታዩ ቃል እገባለሁ። እናም ምንም እንኳን በህይወታችሁ ውስጥ ሁካታ ቢጨምር እንኳን ደስታን የመሰማት አቅማችሁ እንደሚጨምር ቃል እገባለሁ።

አትም