“ጆሴፍ ስሚዝ እና የወርቅ ሰሌዳዎች፣” ጓደኛ፣ ጥር 2021(እ.አ.አ), 42-44
የቅዱሳን መጻህፍት ታሪኮች
ጆሴፍ ስሚዝ እና የወርቅ ሰሌዳዎች
ጆሴፍ ስሚዝ ነብይ ነበረ። ቤተክርስቲያኑን ወደ አለም እንዲመልስ ኢየሱስን ረድቶታል።
ጆሴፍ ወደየትኛው ቤተክርስቲያን መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፀለየ። ኢየሱስም ወደ ማናቸውም ቤተክርስቲያን አትሂድ አለው። የትኞቹም የእርሱ ቤተክርስቲያኖች አልነበሩም።
መልዓኩ ሞሮኒ ጆሴፍን ጎበኘው። ሞሮኒ የተባለ መልአክ ተገለጸለትና በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ ስለተጻፈ መጽሐፍ ለጆሴፍ ነገረው። በአቅራቢያ ባለው ኮረብታ ውስጥ ተቀብሮ ነበር።
በሰማይ አባት እርዳታ፣ በሰሌዳዎቹ ላይ ያሉትን ፅሁፎች ጆሴፍ ተርጉሟል። እነዚህ ፅሁፎች መፅሐፈ ሞርሞን ሆነዋል።
አሁን መጽሃፈ ሞርሞንን ማንበብ እንችላለን። እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሄድ እንችላለን!