2021 (እ.አ.አ)
አንድን መንደር ለማዳን አንድ ልጅ አስፈጓል
ሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)


“ አንድን መንደር ለማዳን ወንድ ልጅ አስፈጓል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)፣ 10–11።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሚያዝያ 2021(እ.አ.አ)

አንድን መንደር ለማዳን ልጅ አስፈጓል

ቶም ፋኔኔ ገና አስራ ሁለት አመቱ ነበር፣ ነገር ግን ሳሞአ በሚገኘው መንደሩ ላይ አስከፊ በሽታ ሲከሰት ታላላቅ ነገሮችን እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበለት።

የታመመን የመንደር አባል የሚረዳ ልጅ ያላት ሳሞአ ደሴት

ስዕል በጄምስ ማድሰን፤ ፎቶ ከጌቲ ኢሜጅስ

የዚህ አመት የወጣቶች ጭብጥ ሀሳብ እንደሚለው፣ እናንተ “የታላቁን ስራ መሰረት እየጣላችሁ” ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33)። በቤተክርስቲያኗ ታሪክ በሙሉ፣ ወጣቶች የእግዚአብሔርን መንግሥት በመገንባቱ ወሳኝ ጊዜያት ውስጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። አንዱ ምሳሌም እነሆ።

የደሴት ወረርሸኝ

ከ100 ዓመታት በፊት በፓስፊክ ውቅያኖስ ሳሞአ ደሴቶች ውስጥ ቶም ፋኔኔ የተባለ አንድ ወጣት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት በህይወት እና በሞት ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ትልቅ እገዛ ነበር።

ቶም ይኖር የነበረው በአካባቢው የሚገኙ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እንደ መሰብሰቢያ እና እንደ ማህበራዊ ማእከል በተመሰረቱት ሳኡኒአቱ በተባለ መንደር ውስጥ ነበር። ልክ በሌሎቹ ዘመናት እና ቦታዎች እንደነበሩት እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን፣ የእግዚአብሔርን መንግስት በጋራ ለመገንባት ሲሰሩ ፈተናዎች እንዲሁም ተዓምራቶች አጋጥሟቸዋል። የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ወደ መንደሩ በገባበት በ1918 (እ.አ.አ) አንድ ፈተና መጣ።

ህመሙ እንደተከሰተ በጣም አስከፊ ነበር እናም በፍጥነት ተዛመተ። በግምት ወደ 400 የሚጠጉት የመንደሩ አባላት በዚህ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆኑ። ለመንቀሳቀስ የሚችሉት ሁለት ብቻ ነበሩ፦ አንድ ሽማግሌ እና የ12 ዓመቱ ቶም።

እምነት እና ሀይለኛ ስራ

የቶም ቤተሰቦች ከዚህ በፊት በታመሙበት ወቅት እምነታቸውን አሳይተው ነበር እና በዚህም ምክንያት ተዓምራቶችን አይተዋል። የቶም ታናሽ ወንድም አዪላማ ከጥቂት ዓመታት በፊት ታምሞ ነበር። አባታቸው ኤሊሳላ አዪላማን ለመንከባከብ ምን ማድረግ እንዳለበት የተወሰኑ መመሪያዎችን የሰጠው ሕልም አይቶ ነበር፦ የዊሊ-ዊሊ ዛፍ ፈልግ፣ ጥቂት ቅርፊቶችን ውስድ እና ጭማቂውን ለማውጣት ጨቅጭቀው። ኤሊሳላ ይህን አደረገና ጭማቂውን ወደ አዪላማ አመጣ፣ እርሱም ጠጣውና ብዙም ሳይቆይ አገገመ። ስለዚህ ቶም በእምነት መስራት በሽታን ለማሸነፍ እንዴት እንደሚረዳ ተመልክቷል።

በ1918ቱ (እ.አ.አ) የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ወቅት፣ ቶም የመንደሩን ሰዎች ለመንከባከብ ጠንክሮ በመስራቱ እምነት አሳይቷል። “በየቀኑ ጠዋት ከቤት ወደ ቤት ሰዎችን ለመመገብ እና ንፅህናቸውን ለመጠበቅ እንዲሁም ማን እንደሞተ ለማጣራት እሄድ ነበር” ብሏል።

ከምንጭም በባልዲዎች ውሃ ቀድቶ ወደ እያንዳንዱ ቤት ውሃ ያመጣ ነበር። ጭማቂውን ለበሽተኞች ለማምጣት ሲል በኮኮናት ዛፎች ላይ በመውጣት፣ ኮኮናት ይለቅምና ሽፋኑን በመግፈፍ ይሸነቁራቸዋል። በመንደሩ የነበሩትን ዶሮዎች ሁሉ አርዶ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ሾርባ ሰራ።

ልዩነት ማምጣት

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት፣ ሳሞአ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አንድ አራተኛ የሚሆኑት በኢንፍሉዌንዛ ሞተዋል። በቶም መንደር የሚገኙ አንዳንድ ሰዎችም እንዲሁ ሞተዋል። ቶም የገዛ አባቱን ኤሊሳላን ጨምሮ ከ20 በላይ የሆኑትን ለመቅበር መቃብሮችን በመቆፈር እርዳታ ሰጥቷል።

ነገር ግን በቶም ልፋት እና በፍቅር የተሞላ እንክብካቤ ምክንያት በመንደሩ ውስጥ ብዙ ሰዎች በህይወት ተርፈዋል። ለእነዚያ ሰዎች እና በሳሞአ ይካሄድ ለነበረው የጌታ መንግሥት ግንባታ ትልቅ ልዩነት አምጥቷል። እርሱም “የታላቁን ሥራ መሠረት [እየጣለ]” ነበር።

እናም በራስዎ መንገድ፣ እርስዎም እየሰሩ ነው።

ቶም ያደረጋቸውን ዓይነት ነገሮች እንዲያደርጉ ላይጠሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን በእውነቱ ለእርስዎ፣ ለሌሎች እና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመገንባት በሚከናወነው ሥራ ላይ ትልቅ ልዩነት በሚያመጡ በተለያዩ መንገዶች እምነትን እየተለማመዱ ነው።

በጎነትን፣ ትዕግሥትን፣ ደግነትን እና ፍቅርን በማሳየት ለቤተሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ እና ለሌሎች ምሳሌ እየሆኑ ነው። ሌሎችን እያገለገሉ ነው። በቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና በጸሎት እየተሳተፉ ነው። ዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት እያጋሩ ነው።

በዚህ ባለፈው ዓመት ብዙዎቻችሁ የወረርሽኝን ውጤት እየተቋቋማችሁ እንኳን እነዚህን ነገሮች በማድረግ ቆይታችኋል። ምናልባት ውሃ እና ኮኮናት አላመጡም ይሆናል እንዲሁም 400 ሰዎች ወደ ጤናቸው እንዲመለሱ አላስታመሙም ይሆናል፣ ነገር ግን በብዙ መንገዶች ለሰዎች ማጽናኛን፣ ተስፋን፣ ደስታን እና ሰላምን አምጥተዋል

ዕድሜዎ ከእምነትዎ እና ለሌሎች ለመስራት እና ለማገልገል ካለዎት ፍላጎት አንፃር ብዙም ግምት የሚሰጠው አይደለም። እንደ ቶም ፋኔኔ ያሉ ካለፉት ጊዜያት የተገኙ ምሳሌዎች፣ እርስዎ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ መሠረት ለመጣል እንደሚያስፈልጉ እንዲያዩ ሊረዱዎት ይችላሉ።