2021 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢያት እና ከሞት አዳነን
ሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢያት እና ከሞት አዳነን፣” ሊያሆና፣ ሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ሚያዝያ 2021(እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢያት እና ከሞት አዳነን

በመስዋዕቱ ምክንያት ሁላችንም ዘለአለማዊ ሰላም እና ደስታ ለማግኘት እድል ይኖረናል።

ክርስቶስ ምድርን ሲፈጥር

ክርስቶስ ምድርን ሲፈጥር፣ በሮበርት ቲ.ባሬት

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን እንጠቅሰዋለን። ያም ለኃጢያቶቻችን ዋጋ ስለከፈለ እና የሞትን ሀይል በማሸነፉ ምክንያት ነው። አዳነን! የኃጢያት ክፍያ ተብሎ የተጠራው ለእኛ የከፈለው መስዋእት እስካሁን ከተከሰቱት ሁሉ በላይ እጅግ አስፈላጊው ሁነት ነው። በእርሱ ምክንያት ሞት መጨረሻው አይደለም። በእርሱ ምክንያት ለኃጢያቶቻችን ስርየት ማግኘት፣ እንደገና ንፁህ መሆን፣ እና በየእለቱ የተሻለ ማደግ እንችላለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ የበኩር ልጅ ነበር

ወደምድር ከመምጣታችን በፊት ከሰማያዊ ወላጆቻችን ጋር እንኖር ነበር። እንደ በኩር ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶች ይህችን ወብ አለም በመፍጠር ረዳ። አዳኛችን ለመሆን ተመረጠ እንዲሁም ፍጹም ምሳሌ እንዲሆን፣ ወንጌሉን ለማስተማር እና ለእኛ የኃጢያት ክፍያን ለመፈጸም በምድር ለመወለድ ተስማማ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ ሲጸልይ

አባቴ ሆይ፣ በሲመን ዱዊ

ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያታችንን ዋጋ ከፈለ

ኢየሱስ በቅርብ እንደሚሞት ሲያውቅ ጌቴሴማኒ ወደሚባለው የአትክልት ስፍራ ለመጸለይ ሄደ። በዚያ ፀሎት ወቅትም የኃጢያቶቻችንን ዋጋ መክፈል ጀመረ። እኛ እንዳንሰቃይ እርሱ በፈቃደኛነት ተሰቃየ—ንስሃ ከገባን። ከኃጢአቶቻችን በመራቅ በምትኩ አዳኙን ስንከተል፣ ይቅርታን እና ፈውስን ማግኘት እንችላለን። በጌቴሴማኒ ውስጥ ባጋጠመው ነገር ምክንያት ኢየሱስ እያንዳንዳችንን መሆን ምን እንደሚመስል በትክክል ተረድቷል። እርሱ የእኛ ሀዘኖች፣ ህመሞች እና ጉዳቶች ሁሉ ተሰምተውት ነበር። ይህ የኃጢያት ክፍያ የመጀመሪያ ክፍል ነው።

የክርስቶስ መቀበር

የክርስቶስ መቀበር፣ በካርል ሄንሪች ብሎክ

ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸነፈ

ከጌቴሴማኒ ጸሎቱ በኋላ ኢየሱስ ተላልፎ ተሰጠ፣ ተያዘ፣ እንዲሁም በመስቀል ላይ እንዲሞት ተፈረደበት። ምንም እንኳን እርሱ ሁሉን ቻይ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ራሱን በመስቀል ላይ እንዲሞት ፈቀደ። ተከታዮቹ በፍቅር አስከሬኑን በመቃብር ውስጥ አኖሩ። ምንም እንኳን አካሉ ቢሞትም መንፈሱ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ አሁንም ህያው እንደነበረ አላስተዋሉም ነበር። ከሶስት ቀናት በኋላ ኢየሱስ እንደገና ወደ ህይወት መጥቶ ሞትን ድል ማድረግ እንደሚችል በማረጋገጥ ጎበኛቸው። ይህም የኃጢያት ክፍያውን አጠናቀቀ። ኢየሱስ ከሞት በመነሳቱ ምክንያት እያንዳንዳችን ከሞትን በኋላ እንደገና በህይወት እንኖራለን።

ህያው ነው

ህያው ነው፣ በሲሞን ዱዊ

የገና እና የፋሲካ ትርጉም

አብዛኛው ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ለማስታወስ የሚረዱ ሁለት በዓላትን ያከብራል። በገና ወቅት፣ ኢየሱስ ለእኛ መሰቃየትን እና መሞትን የሚያካትት ቢሆንም ወደ ምድር የመምጣቱን ተልእኮ ለመቀበል ፈቃደኛ ስለነበረ በአመስጋኝነት እናስታውሰዋለን። ፋሲካ አዳኝ በኃጢአትና በሞት ላይ ያገኘውን ድል ያከብራል፣ ይህም ዘላለማዊ የወደፊት ደስታን ተስፋ ይሰጠናል።

ክርስቶስ ጴጥሮስን እና እንድርያስን ሲጠራ

ክርስቶስ ጴጥሮስን እና እንድርያስን ሲጠራ፣ በጄምስ ቴይለር ሀርውድ

ቅዱሳን መጻህፍት ስለ አዳኙ የኃጢያት ክፍያ ምን ይላሉ?

ኢየሱስ በትክክል ስለሚያውቀን፣ እኛን “ለመደገፍ” ወይም ለመርዳት ይችላል ( አልማ 7፥11–12ተመልከቱ)።

አዳኙ ሀዘናችንን እና ስቃያችንን ይረዳል ( ኢሳይያስ 53፥2–5ተመልከቱ)።

እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ስለሚያፈቅር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ኢየሱስን ላከ ( ዮሀንስ 3፥16–17ተመልከቱ)።

ኢየሱስ፣ እኛንም ጨምሮ፣ ተከታዮቹ ከክፋት እንዲጠበቁ እና ከእርሱና ከሰማይ አባት ጋር አንድ እንዲሆኑ ጸለየ ( ዮሀንስ 17ተመልከቱ)።

አዳኛችን እርሱን እንድንከተል እና ወደእርሱ እንድንመለስ ይጋብዘናል ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19፣ 23–24132፥23ተመልከቱ)።