2021 (እ.አ.አ)
ይቅር ለማለት ጥንካሬ ማግኘት
ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)


“ይቅር ለማለት ጥንካሬ ማግኘት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)፣ 10–11።

ኑ፣ ተከተሉኝ

ይቅር ለማለት ጥንካሬማግኘት

ጌታ ሌሎችን ይቅር እንድንል አዞናል። ይህንን ጨምሮ ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ ይረዳናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥10

ምስል
አንዲት ሴት እጆቹን ወደ እርሷ ወደዘረጋ ሰው እየተመለከተች

ሥዕል በጀምስ ማድሰን

አንዳንድ ትእዛዛትን መጠበቅ ከሌሎች በበለጠ የሚከብዱ ይመስላሉን?

ብዙ ሰዎች የሚፈሩት እነሆ፦ “እኔ ጌታ ይቅር የምለውን ይቅር እለዋለሁ፣ ነገር ግን አናንተ ለሁሉም ሰዎች ይቅርታን ታደርጉ ዘንድ ይጠበቅባችኋል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥10)

ቆይ፡፡ ሁሉንም ያስቀየሙንን ሰዎች ይቅር ማለት አለብን? ደግሞስ ያ ይቻላልን?!

አንድ ሰው የማይገባ ነገር ስለተናገራችሁ ወይንም በእራት ጠረጴዛው ላይ ያለውን የመጨረሻ ዳቦ ስላነሳ ይቅር ማለት አንድ ነገር ነው። ነገር ግን ቁስሎቹ ጥልቅ በሚሆኑበት ጊዜስ? እነዚያ ከባድ ቅያሜዎች የሕይወታችንን ጎዳና ሊያበላሹ ወይም ሊለውጡ በሚችሉበት ጊዜስ?

አንዳንድ ጊዜ በጣም የጎዳንን ሰው ይቅር የማለት ችሎታችን ከአቅማችን በላይ እንደሆነ ሊሰማን ይችላል።

መልካም ዜና እነሆ፦ በኢየሱስ ክርስቶስ እርዳታ አማካኝነት በራሳችን ልናደርግ በምንችለው ነገር በፍፁም የተወሰንን አይደለንም።

ያስፈልጋት የነበረው እርዳታ።

ኮሪ ቴን ቡም የተባለች አንዲት ታማኝ ኔዘርላንዳዊት ክርስቲያን እግዚአብሔር አንድን ሰው ይቅር ማለት እንድትችል እንዲረዳት የመጠየቅ ኃይልን በቀጥታ አገኘች።

እርሷ እና እህቷ ቤትሲ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ታስረው ነበር። ኮሪ እና ሌሎች በናዚ የእስር ቤት ጠባቂዎቹ አሰቃቂ ጥቃቶች ደርሰውባታል። እንዲያውም እህቷ ቤቲ በዚያ ጥቃት ሳቢያ ለሞት ተዳረገች። ኮሪ ተረፈች።

ከጦርነቱ በኋላ ኮሪ ሌሎችን ይቅር በማለት የሚገኝን የፈውስ ኃይልን አገኘች። ብዙውን ጊዜ መልእክቷን ህዝብ በተሰበሰበበት ታካፍል ነበር። ሆኖም አንድ ቀን ቃላቶቿ እጅግ ወሳኝ በሆነ ፈተና ላይ ወደቁ።

ከአንድ የህዝብ ንግግር በኋላ በካምፖቹ እጅግ ጨካኝ ከነበሩት የእስር ቤት ጠባቂዎች አንዱ ቀርቦ ኮሪን አነጋገራት።

ከጦርነቱ ማግስት ጀምሮ ክርስቲያን እንደሆነ እና የእስር ቤት ጠባቂ እያለ ለፈጸማቸው አስከፊ ነገሮች ንስሐ እንደገባ ለኮሪ ነገራት።

እጆቹን ዘርግቶም እንዲህ አላት፣ “ይቅር ትይኛለሽ?”

ምንም እንኳን ሌሎችን ይቅር ስለማለት የተማረች እና ያካፈለች ብትሆንም ኮሪ በተለይ የዚህን ሰው እጅ መጨበጥ እና ይቅር ማለት አልቻለችም—የሆነ ሆኖ በራሷ አልቻለችም።

በኋላ እንዲህ ስትል ፅፋለች፣ “ምንም እንኳን የሚያናድዱ የበቀል ሐሳቦች በውስጤ ግልብጥ ብለው ቢመጡም እንኳን ኃጢአት መሆናቸውን አየሁ። ጌታ ኢየሱስ ይቅር በለኝ እንዲሁም ይቅር እንድለው እርዳኝ በማለት ፀለይኩኝ።

“ፈገግ ለማለት ሞከርኩኝ [እንዲሁም] እጄን ለመዘርጋት ታገልኩኝ። አልቻልኩም። ጥቂት የሙቀት ብልጭታም ሆነ ፍቅር ምንም አልተሰማኝም። እናም እንደገና በፀጥታ ፀሎቴን አደረስኩኝ። ኢየሱስ፣ ይቅር ልለው አልችልም። ይቅርታህን ስጠኝ።

“እጁን እንደያዝኩኝ በጣም አስገራሚው ነገር ተከሰተ። በልቤ ውስጥ ለዚህ እንግዳ ከመጠን በላይ ሊባል የሚችል ፍቅር ሲመነጭ ከትከሻዬ አንስቶ በክንዴ እና በእጄ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሞገድ ከእኔ ወደ እሱ የሚያልፍ ይመስል ነበር።

ስለዚህም የዓለም ፈውስ የሚመጣው በእኛ መልካምነት ላይ ተመስርቶ እንዳልሆነ ሁሉ በእርሱ እንጂ በእኛ ይቅርታ ላይ ተመስርቶ እንዳልሆነም ተገነዘብኩ። ጠላቶቻችንን እንድንወድ ሲነግረን ከትእዛዙ ጋር ፍቅርን ራሱን ሰጥቶናል።” 1

ይቅር የማለትን ትእዛዝ ጨምሮ ትእዛዛቱን ትጠብቁ ዘንድ ሊረዳችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል—አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜም። ልክ ኮሪ ቴን ቡምን እንደረዳት እናንተንም ሊረዳችሁ ይችላል።

የሚገባችሁ ፈውስ

ህይወት አስቸጋሪ ናት። ውስብስብ ናት። እንዲሁም ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር የመምረጥ ነፃነት በሰጣቸው ሰዎች የተሞላ ነው።

አንድ ሰው ሆነ ብሎ ከባድ ህመም የሚያስከትልባችሁ ምርጫ ሲያደርግ ወይም በአጋጣሚም ቢሆን እንደዚያ በሚያደርግባችው በእነዚያ ጊዜያት እርዳታ ለማግኘት ስትጸልዩ እና ይቅር ለማለት ስትጣጣሩ የፈውስ ኃይልን ለመቀበል ትችላላችሁ።

ሌሎችን ይቅር ማለት ለነፍሳችሁ ፈውስን ያመጣል። በእግዚአብሄር እርዳታ ያስቀየማችሁን ሰው ይቅር ስትሉ ወደ ኋላ ሊያደርጋችሁ የሚችልን አስፈሪ ሸክም ከትከሻችሁ ላይ ታወርዳላችሁ። ወደ እውነተኛ ፈውስ የሚወስደው መንገድ አስቸጋሪ በሚመስልበትም ጊዜ እንኳ በእግዚር ዘንድ ብቻችሁን እንድትሄዱ በፍፁም አይጠበቅባችሁም።

አትም