2021 (እ.አ.አ)
አምላክ ምንድን ነው?
ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)


“አምላክ ምንድን ነው?፣” ሊያሆና፣ ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)

አምላክ ምንድን ነው?

እግዚአብሔር አብ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አላማ ያላቸው ሶስት የተለያዩ አካላት ናቸው።

ምስል
የመጀመሪያው ራዕይ

ዝርዝር ከመጀመሪያው ራዕይ፣ በጃን ማክናውተን

አንድ ጊዜ የአንድ ጋዜጣ አርታኢ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላቶች በምን እንደሚያምኑ ጆሴፍ ስሚዝን ጠየቀው። በምላሹም ነቢዩ የእምነት አንቀጾች ብለን የምንጠራችውን 13 የእምነት አረፍተ ነገሮችን ጻፈ። የመጀመሪያው አረፍተ ነገር እንዲህ ይላል “በዘላለም አባት፣ በእግዚአብሔር፣ እናም በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እናም በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን” (የእምነት አንቀፆች 1፥1)። እነዚህ ሶስቱ አምላክ የምንለውን ይመሰርታሉ።

የዘላለም አባት፣ እግዚአብሔር

እግዚአብሔር ከሞት የተነሳ የስጋና አጥንት ሰውነት አለው። እርሱ የመንፈሶቻችን አባት ነው። እርሱ እያንዳንዱን ልጆቹን ሙሉ በሙሉ ይወዳል። እግዚአብሔር ፍጹም ነው፣ ሁሉም ሃይል አለው እንዲሁም ሁሉንም ያውቃል። እርሱ ጻድቅ፣ ይቅር ባይ እና ደግ ነው። ከመወለዳችን በፊት በመንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እንኖር ነበረ። እንድንማር እና እንድናድግ ወደ ምድር ልኮናል። የእግዚአብሔር ታላቁ ፍላጎትም እያንዳንዱ ልጆቹ ከሞት በኋላ እንደገና ከእርሱ ጋር ለመኖር መመለስ ነው። ወደ እግዚአብሔር መገኛ ለመመለስ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል እንዳለብን እግዚያብሄር ያስተምረናል።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም እያስተማረ።

ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም እያስተማረ፣ በሮበርት ቲ.ባሬት

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት የተነሳ የስጋና የአጥንት ሰውነት አለው። እርሱ የእግዚአብሔር የበኩር ልጅ ነው። ከመወለዳችን በፊት አዳኛችን እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው። ይህ ማለት ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ምሳሌ ሊሆንልን፣ ወንጌሉን ሊያስተምር፣ የሃጢያት መስዋእቱን ሊከፍል እንዲሁም ከሞት ነጻ ሊያወጣን ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ንስሃ ስንገባ ለኃጢያቶቻችን ስርየት ማግኘት እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ለመረዳት እንዲችል እና እኛን ለማገዝ ሲል በብዙ ነገሮች ተሰቃየ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ ከዚያም እያንዳንዱ እንደገና በህይወት መኖር ይችል ዘንድ ዳግም በህይወት ኖረ።

ምስል
የክርስቶስ መቀበር

ፎቶግራፍ ከጌቲ ምስሎች

መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ ስጋዊ አካል የሌለው የአምላክ አባል ነው። እሱ መንፈስ ነው። መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ ከመንፈሶቻችን ጋር መነጋገር ይችላል። እግዚአብሔረር እውን እንደሆነ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ ይመሰክርልናል። መንፈስ ቅዱስ የፍቅር፣ የምሪት ወይም የመጽናናት ስሜት በመስጠት እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ ይሠራል። ስንጠመቅ እና ማረጋገጫ ስናገኝ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንቀበላለን። ከተጠመቅን በኋላ የእግዚያብሄርን ትእዛዛት ስንጠብቅ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ሊሆን ይቸላል።

ምስል
የመጀመሪያው ራዕይ

የመጀመሪያው ራዕይ፣ ምስል በዋልተር ሬን

የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ

በጊዜ ሂደት ሰዎች ስለአምላክ ግራ ተጋብተዋል። ሰዎች በእግዚአብሔር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ምንነት ላይ አልተግባቡም። ጆሴፍ ስሚዝ ያየው የመጀመሪያ ራዕይ በጣም አስፈላጊ የነበረበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ አካል እንዳላቸው እና ሁለት የተለያዩ አካላት እንደሆኑ አየ።

ምስል
ማዳመጥ

ማዳመጥ በማይክል ጃርቪስ ኔልሰን

የተለያዩ ነገር ግን አንድ የሆኑ

ቅዱት መጻህፍት እና የዘመናችን ነቢያት እግዚያብሄር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አላማ ያላቸው የተለያዩ አካላት እንደሆኑ ያስተምሩናል፦አለሟችነታችን እና ዘላለማዊ ህይወታችን (ሙሴ 1፥39 ይመልከቱ)። እንደ አንድ ቡድን አባላት በየቀኑ እኛን ለመርዳት አብረው ይሰራሉ። ለሃጢያቶቻችን ንስሃ ስንገባ እና ትክክለኛውን ስንመርጥ ወደ እነርሱ መቅረባችን ሊሰማን ይችላል።

ስለ አምላክ የሚያመለክቱ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች

  • የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ በአላማ አንድ ናቸው (ዮሃንስ 10፥30 ይመልከቱ)።

  • የሰማይ አባት ልጁን አነጋገረው (ማቴዎስ 3፥16–17 ይመልከቱ)።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን አነጋገረው (ዮሃንስ 11፥41 ይመልከቱ)።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን አንድ እንሆን ዘንድ ጸለየ (ዮሃንስ 17፥11 ይመልከቱ)።

  • ጆሴፍ ስሚዝ የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ተመለከተ (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17 ይመልከቱ)።

  • መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ ይመሰክራል (ዮሃንስ 15፥26 ይመልከቱ)።

አትም