2021 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር ዕቅድ ራዕይ
ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)


“የእግዚአብሔር ዕቅድ ራዕይ” ጓደኛ ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)

የእግዚአብሔር ዕቅድ ራዕይ

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን አብን እና ወልድን አዩ

ሥዕል በአፕርይል ስቶት

አንድ ቀን ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን ቅዱሳን መጽሐፍትን እያነበቡ ነበር። ራዕይን አዩ። የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን አዩ።

የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ

ከመወለዳችን በፊት በሰማይ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንኖር እንደነበር ተማሩ።

ወላጅ ያዘነ ልጅን ሲያቅፍ

ኢየሱስን እንዴት እንደምንከተል እና መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንደምናዳምጥ ለመማር ወደ ምድር መጣን። መጥፎ ምርጫዎችን ስናደርግ ትዕዛዛትን መጠበቅን እና ንስሃ መግባትን እንማራለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብር ወጣ

ከሞትን በኋላ እንነሳለን። ጻድቅ ከሆንን ከሰማይ አባታችን ጋር በድጋሚ መኖር እንችላለን።

አባት ለሴት ልጆቹ ሲያነብ

በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ስለእግዚአብሔር ዕቅድ መማር እችላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከቤተሰቤ ጋር ለዘላለም መሆን እችላለው።

የሚቀባ ገፅ

የሰማይ አባት ለእኔ እቅድ አለው

ቤተሰብ

ክርስቶስን እንዴት ትከተላላችሁ?