2021 (እ.አ.አ)
የሰማይ አባታችን ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል
ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)


“የሰማይ አባታችን ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል፣” ሊያሆና፣ ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ሐምሌ 2021 (እ.አ.አ)

የሰማይ አባታችን ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል

የእግዚአብሔርን የደስታ ዕቅድ ስናስታውስ ሕይወት ከባድ በሚሆንበትም ጊዜ እንኳን ደስታን ማግኘት እንችላለን።

ምስል
ክርስቶስ ከህጻናት ጋር

በምድር ላይ ከመወለዳችን በፊት፣ ሁላችንም ከሰማይ አባት ጋር እንደ መንፈስ ልጆቹ አብረን ኖርን። ልጆቹ እንዲማሩ እና እንዲያድጉ ለመርዳት ዕቅድን አቀረበ። በዕቅዱ አማካኝነት እንደ እርሱ የበለጠ መሆን እናም የዘላለም ሕይወትን ለማጣጣም ብቁ መሆን እንችላለን። ይህ ዕቅድ እውን መሆን የሚችለው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሃጢያቶቻችን ለመሰቃየት የሃጢያት ክፍያ የሚባልን መስዋዕትነት ለመክፈል ወደ ምድር በመምጣቱ ምክንያት ነው። ።

የሰማይ አባት ዕቅድ የሚከተሉት ዕቅድ ተብሎ ይጠራል

እነዚህ እና ሌሎች ቅዱሳን መጽሐፍት እንደሚያሳዩት፣ የሰማይ አባት እንደ እርሱ እንድንሆን፣ ወደ እርሱ እንድንመለስ እና በእውን ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል ( ሙሴ1፥39ይመልከቱ)።

እንድንማር እና እንድናድግ ወደ ምድር መጣን

እግዚአብሔር አካላዊ ሰውነት ማግኘት ወደምንችልበት ወደ ምድር ላከን ( ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26–27ይመልከቱ)። ምድራዊ ሕይወትን ለመለማመድ እንዲረዳን አካላት ያስፈልጉን ነበር።

እግዚአብሔር ሁሌም ደስተኛ እንደማንሆን ያውቅ ነበር። ሃዘኖች፣ ህመም እንዲሁም ሞት ያጋጥሙናል። ነገር ግን በሕይወት ፈተናዎች ውስጥ የሰማይ አባት እንድንማር እና እንድናድግ ይረዳናል።

እግዚአብሔር እንዲሁም ነፃ ምርጫን ማለትም ክመልካም እና ክክፉ መምረጥ መቻልንም ሰጠን። የምናስበውን እና የምናደርገውን ራሳችን እንድንመርጥ ፈቀደልን። ትክክለኛውን ነገር ለመምረጥ እንድንማር ለመርዳት ቅዱሳን መጽሐፍትን እና በሕይወት ያሉ ነብያትን ሰጥቶናል ( አብርሐም 3፥25ይመልከቱ)።

ምስል
የህይወት ዛፍ

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን ይሞክሩ

እግዚአብሔር ልንከተል የሚገባንን ምሳሌ ሳይሰጠን ወደ ምድር አላከንም ( ዮሐንስ 13፥15ይመልከቱ)። መንገዱን ያሳየን ዘንድ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው። እርሱን እንዴት መከተል እንደምንችል ለመማር እርሱ ማን እንደሆነ እና በምድራዊ ሕይወቱ ውስጥ ምን እንዳደረገ ለመማር ቅዱሳን መጽሐፍትን ማንበብ እንችላለን። እግዚአብሔርን በመታዘዝ እና ሌሎችን በመውደድ እንደ ክርስቶስ ለመሆን የተቻለንን ማድረግም እንችላለን።

ስህተት ስንሰራ ይቅርታ እንጠይቃለን እናም እኛን ለመቀየር እንዲረዳን የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ኃይል ላይ እንመረኮዛለን። በእያንዳንዱ ቀን የበለጠ እንደ እርሱ ለመሆን ስንጥር ደስተኛ መሆን እንችላለን።

ሞት የመጨረሻ አይደለም

ስንሞት መንፈሶቻችን ወደ መንፈስ አለም ይሄዳሉ። እዚያ ትንሳኤን እየተጠባበቅን መማራችንን እንቀጥላለን።

በትንሳኤ ወቅት አካላችን እና መንፈሳችን አንድ ላይ ይዋሃዳሉ። አካላቶቻችን ፍፁም ይሆናሉ እንዲሁም ሞትን ወይም ህመምን በፍፁም መልሰን አናይም ( አልማ 11፥44–45ይመልከቱ)። ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተ እና በድጋሚ ወደ ሕይወት እንደመጣ ሁሉ እኛም ሁላችንም በድጋሚ እንኖራለን።

እግዚአብሔር ሲፈርድብን ተግባራችንን እና ምኞታችንን ከግምት ውስጥ ያስገባል። ትዕዛዛቱን እና ለሰማይ አባት የገባናቸውን ቃልኪዳኖች ለመጠበቅ ከሞከርን ከእርሱ ጋር በድጋሚ ለመኖር እንችላለን።

ሕይወት ከእግዚአብሔር እና ከቤተሰቦቻችን ጋር በሰማይ ውስጥ

በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከእግዚአብሔር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንኖራለን። ከእነሱ ጋር ከታተምን እዚያ ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘላለም አብረን መኖርም እንችላለን። ሰላምን፣ ደስታን እና እረፍትን እናገኛለን ( ሞዛያ2፥41ይመልከቱ)።

ምድራዊ ሕይወታችን አንዳንድ ጊዜ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ከተከተልን በዚህ ሕይወት ደስታን እና በሚመጣው ሕይወት ዘላለማዊ ሃሴትን እናገኛለን።

ቅዱሳን መፅሃፍት ስለ የደስታ ዕቅድ ምን ይላሉ?

ሕይወታችንን የምንኖርበት መንገድ ጠቃሚ ነው። እግዚአብሔር እንደ ሃሳቦቻችን እና ተግባሮቻችን ይፈርደናል እና ይሸልመናል ( አልማ 41፥3ይመልከቱ)።

ሰይጣን የደስታችን ጠላት ነው። ምድራዊ ሕይወታችንን በአግባቡ እንዳንጠቀም እና ሃጢያት እንድንሰራ ይፈትነናል። ልክ እንደ እርሱ መከረኛ እንድንሆን ይፈልጋል ( 2 ኔፊ 2፥27ይመልከቱ)።

እግዚአብሔር ለእኛ ባለው ዕቅድ ላይ እምነት ሲኖረን ምንም አይነት ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም እንኳን ሰላም ሊኖረን ይችላል። ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመኖር መጓጓት እንችላለን ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥23ይመልከቱ)።

ሁሉም ሥነ ጥበብ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

አትም