2021 (እ.አ.አ)
የቤተክርስቲያን አስፈላጊነት
ህዳር 2021 (እ.አ.አ)


“የቤተክርስቲያን አስፈላጊነት፣“ ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ህዳር 2021(እ.አ.አ)

የቤተክርስቲያን አስፈላጊነት

ፅሁፎች

ምስል
ቤተመቅደስ

ዛሬ፣ መልእክቴ በቤተክርስቲያናቸው መገኘት ወይም መሳተፍ ስላቆሙ እንደነዚህ ስላሉ መልካም እና ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ ስላላቸው ሰዎች የተመለከተ ነው። “አብያተ ክርስቲያናት“ ስል ምኩራቦችን፣ መስጊዶችን ወይም ሌሎች ሃይማኖታዊ ተቋማትን ጨምሬ ነው። በእነዚህ ሁሉ ላይ ያለው ተሳትፎ በአገር አቀፍ ደረጃ በእጅጉ መቀነሱ ያሳስበናል። …

በቤተክርስቲያን የሚደረግ ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ የተሻልን ሰዎች እንድንሆን እና በሌሎች ሰዎች ህይወትም ላይ የተሻለ ተጽዕኖ የምናሳድር እንድንሆን ይረዳናል። …

… በቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከሚጥሩ ድንቅ ሰዎች ጋር እንገናኛለን። ይህም በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ብቻችንን እንዳልሆንን ያስታውሰናል። ሁላችንም ከሌሎች ጋር ትስስር እንዲኖረን እንፈልጋለን እናም በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረግ ትስስር ልንለማመዳቸው ከምንችላቸው ከሁሉም ከሚሻሉት ጥቂቶቹ ናቸው።

… የቤተክርስቲያን ተሳትፎን የሚተዉ እና በግል በሚደረግ መንፈሳዊነት ላይ ብቻ የሚተማመኑ ከእነዚህ አስፈላጊ የወንጌል ነገሮች ራሳቸውን ይለያሉ፦ ከክህነት ሃይል እና በረከቶች፣ ዳግም በሙላት ከተመለሰው ትምህርት እንዲሁም ያንን ትምህርት በተግባር ለማዋል ከሚያስችሉ ተነሳሽነቶች እና እድሎች። …

ከመንፈሱ ጋር ባለ ወዳጅነት አማካኝነት ከሚገኝ ሰላም እና ደስታ በተጨማሪ በቤተክርስቲያናችን የሚሳተፉ አባላት የጥበብ ቃልን በመኖር የሚገኙትን በረከቶች እና የአስራት ህግን ለሚኖሩ ቃል የተገባውን ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ብልጽግና በመሳሰሉት ወንጌልን በመኖር የሚገኙ ፍሬዎች ይደሰታሉ።

… የትምህርት ሙላት እንዲሁም የእርሱ የማዳን እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ የማድረግ ስርዓቶች የሚገኙት ዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ብቻ ነው።

አትም