2021 (እ.አ.አ)
የመጠየቅ እና በሚሰጠው መልስ ላይ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ እምነት
ህዳር 2021 (እ.አ.አ)


“የመጠየቅ እና በሚሰጠው መልስ ላይ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ እምነት፣“ ሊያሆና፣ ህዳር 2021(እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ህዳር 2021(እ.አ.አ)

የመጠየቅ እና በሚሰጠው መልስ ላይ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ እምነት

ፅሁፎች

ምስል
ሰው እየፀለየ

ከእግዚአብሔር መገለጥን የመቀበያው መንገድ በአዳም እና ሔዋን ጊዜ ከነበረው አልተቀየረም። ለሁሉም የተጠሩ የጌታ አገልጋዮች ከመጀመሪያው ጀምሮ እስካሁኑ ቀን ድረስ ያው ነው። ለእናንተም ሆነ ለእኔ ተመሳሳይ ነው። ሁልጊዜም ቢሆን የሚደረገው እምነትን በመለማመድ ነው። …

… መልስ የምትፈልጉላቸው ጥያቄዎች አሏችሁ። ቢያንስ በአገልጋዮቹ አማካኝነት መልሶችን ከጌታ እንደምትቀበሉ ተስፋ ለማድረግ የሚያስችል በቂ እምነት አላችሁ። ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ ከተናጋሪዎቹ መልሱን ለመጠየቅ እድል አታገኙም፣ ሆኖም አፍቃሪ አባታችሁን በጸሎት መጠየቅ ትችላላችሁ።

ፍላጎቶቻችሁን የሚያሟሉ እና ለመንፈሳዊ ዝግጅታችሁ የሚሆኑ መልሶች እንደሚመጡ ከልምድ አውቃለሁ። …

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁ እምነት በኃጥያት ክፍያው ተጽዕኖ አማካኝነት ወደተለሳለሰ ልብ አምርቶ ከሆነ፣ ለጸሎቶቻችሁ መልስ የሚያመጣው የመንፈስ ሹክሹክታ ይበልጥ ሊሰማችሁ ይችላል። …

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት አብን መልስ ወደመጠየቅ እንደሚመራን፣ ያው እምነት ደግሞ የእርሱን መመሪያ ለመስማት እና ለመታዘዝ ቆራጥ እና ጉጉ እንሆን ዘንድ የአዳኙን የደግነት ተግባር ያመጣል። …

የቆምንበት ዓለት ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን፤ ይህች ራሱ የሚመራት ቤተክርስቲያኑ እንደሆነች፤ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በህይወት ያሉ የእርሱ ነቢይ እንደሆኑ እንደሚመሰክርልን ምስክርነቴ ነው።

ያው ተመሳሳይ እምነት ይኖራችሁም ዘንድ እጸልያለሁ።

ምስል
ቤተመቅደስ

የኮርዶባ አርጀንቲና ቤተመቅደስን ማጠናከር

አትም