2022 (እ.አ.አ)
የአባቶች አለቃዎች፦ ማን ነበሩ እና ለምን ይህ አስፈላጊ ነው
የካቲት 2022 (እ.አ.አ)


“የአባቶች አለቃዎች፦ ማን ነበሩ እና ለምን ይህ አስፈላጊ ነው፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)

ዘፍጥረት 11–50

የአባቶች አለቃዎች

የአባቶች አለቃዎች፦ ማን ነበሩ እና ለምን ይህ አስፈላጊ ነው

ምናልባት ስለ አብርሐም፣ ይስሀቅ እና ያዕቆብ ሰምታችሁ ይሆናል። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለእነርሱ ብዙ ጊዜ እናነባለን እናም በዚህ አመት ብሉይ ኪዳንን በምታጠኑበት ጊዜ ስለእነርሱ የበለጠ ትሰማላችሁ። ለእነሱ ብዙ ትኩረት ሲሰጡ፣ በጣም አስፈላጊ መሆን አለባቸው፣ አይደል? ነገር ግን “ከሺህ አመታት በፊት የኖሩ ሦስት ሰዎች ዛሬ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው?” ብላችሁ ራሳችሁን ትጠይቁ ይሆናል። እንግዲህ፣ የዚያ መልስ ቁልፍ ያለው በዘለአለማዊ ቃል ኪዳኖች እና እግዚአብሔር በሰጣቸው ቃል የተገቡ በረከቶች ላይ ነው።

አብርሐም

ምስል
አብርሐም

ሰዕል በ ጀሮም ቮግል

አብርሐም ታላቅ ነቢይ ነበር። እርሱም ጻድቅ እና ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ ነበር።

ተጠመቀ፣ ክህነትን ተቀበለ እና ከሚስቱ ከሳራ ጋር ለዘለአለም ታተመ።

ዘሩ ታላቅ እንደሚሆን እና እርሱ እንደተቀበለው አይነት በረከት እንዲያገኝ ከአብርሃም ጋር እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገባ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሙላት ለምድር ሕዝቦች ይወስዳሉ።

ይስሀቅ

ምስል
ይስሀቅ

ይስሀቅ የአብርሐም እና ሣራ ወንድ ልጅ ነበር።

አብርሐም ይስሀቅን እንዲሰዋ እግዚአብሔር ነገረው። አብርሐም ይስሀቅን ይወደው ነበር ግን ለእግዚአብሔር ታዛዥ ለመሆነ መረጠ። አብርሐም ይስሀቅን ከመሠዋቱ ትንሽ ቀደም ብሎ አንድ መልአክ አብርሐምን እንዲያቆም ነገረው። አብርሐም እና ይስሀቅ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኞች መሆናቸው የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የኃጢያት ክፍያ ምሳሌ ነው።

ይስሀቅ እንደ አብርሃም አይነት በረከቶች እንደሚሰጠው ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል።

ያዕቆ

ምስል
ያዕቆ

ልክ እንደ አባቱ እና አያቱ፣ ያዕቆብም ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር።

በታማኝነቱ ምክንያት፣ ጌታ የያዕቆብን ስም ወደ እስራኤል ለወጠው፣ ትርጉሙም “በእግዚአብሔር ፊት የሚያሸንፍ” ወይም “እግዚአብሔር ያሸንፍ” (Bible Dictionary [የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት]፣ “እስራኤል” ይመልከቱ)።

ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት። እነዚህ ልጆችና ቤተሰቦቻቸው የእስራኤል ነገዶች በመባል ይታወቃሉ።

እግዚአብሔር ከአብርሐም ጋር የገባው ቃል ኪዳን ከያዕቆብና ከልጆቹ ጋር ታድሷል።

የአባቶች አለቃዎች እና እናንተ

እንደ ቤተክርስቲያኗ አባል፣ እናንተ የአብርሐም፣ የይስሀቅ እና የያዕቆብ ዘር አካል ናችሁ። ከእግዚአብሔር ጋር የገቡት ቃል ኪዳን እናንተን ይመለከታል!

የአዳኝን ምስክርነት ለመሸከም እና ወንጌልን ለመካፈል በረከት እና ሀላፊነት አላችሁ።

እንዲሁም ሁሉም ሰው ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡና እንዲጠብቁ እናም የክህነት ስርዓቶችን እንዲቀበሉ እንድትጋብዙ ተጠርታችኋል። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ይህ ሁሉ እስራኤልን የመሰብሰብ ክፍል እንደሆነ፣ ይህም “ዛሬ በምድር ላይ እየተከናወነ ያለው እጅግ አስፈላጊ ነገር” ነው ብለዋል (“የእስራኤል ተስፋ፣” [worldwide youth devotional [የአለም አቀፍ የወጣቶች መንፈሳዊ ስብሰባ] ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ 8፣ ChurchofJesusChrist.org)።

አትም