2022 (እ.አ.አ)
የመጀመሪያ ክፍል
የካቲት 2022 (እ.አ.አ)


የመመሪያ መጽሃፍ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች

የመጀመሪያ ክፍል

የመጀመሪያ ክፍል በቤተክርስቲያኗ ከ18 ወር እስከ 11 አመት ለሆናቸው ልጆች የተዘጋጀ የሚደነቅ ፕሮግራም ነው። ስለመጀመሪያ ክፍል ከመመሪያ መጽሃፉ የወጡ ጥቂት መርሆዎች ቀጥሎ ቀርበዋል፦

የመጀመሪያ ክፍል—የወላጆች እና የመሪዎች ሚና፦

ወላጆች ወንጌልን ለልጆቻቸው የማስተማር እና እንዲኖሩት የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 68፥25–28 ይመልከቱ)። የመጀመሪያ ክፍል መሪዎች እና አስተማሪዎች፣ ወላጆች ይህንን ሃላፊነት ይወጡ ዘንድ የመጀመሪያ ክፍል ትምህርቶች፣ የመዝሙር ጊዜዎች እና አገልግሎት እንዲሁም አክቲቪቲዎች ልጆች የአዳኙን ምሳሌ እንዲከተሉ መርዳታቸውን [በማረጋገጥ] ይደግፋሉ።

መሪዎች ወንጌልን በመኖር ረገድ የቤተሰብ ድጋፍ ለማያገኙ ልጆች ጠንቃቃ መሆን አለባቸው።

የመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜዎች

የመዝሙር ጊዜ ልጆች የሰማያዊ አባት ፍቅር እንዲሰማቸው እና የደስታ እቅዱን እንዲማሩ ይረዳል። ልጆች ስለወንጌል መርሆዎች ሲዘምሩ መንፈስ ቅዱስ ስለእውነትነቱ ይመሰክርላቸዋል። ቃላቶቹ እና መዝሙሩ በልጆቹ አዕምሮ እና ልብ ውስጥ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ይቀመጣሉ።

የመዝሙር ጊዜ ከትምህርት ጊዜ ይለያል። በመዝሙር ጊዜ ልጆች በዝማሬ በንቃት በሚሳተፉበት ጊዜ ይማራሉ። የመጀመሪያ ክፍል የመዝሙር መሪዎች የወንጌልን መርሆዎች ያስተምራሉ፤ ሆኖም ያንን የሚያደርጉት በመሰረታዊነት በመዝሙር አማካኝነት ነው።

የመጀመሪያ ክፍል—አስተማሪዎች

አዋቂዎች ልጆችን በቤተክርስቲያን ውስጥ መዝሙር ሲያስተምሩ ቢያንስ ሁለት ሃላፊነት የሚሰማቸው አዋቂዎች መኖር አለባቸው። ሁለቱ አዋቂዎች ሁለት ሴቶች፣ ሁለት ወንዶች ወይም የተጋቡ ጥንዶች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ የማይቻል ከሆነ መሪዎች ክፍሎችን መቀላቀል አለባቸው። መሪዎች እና አስተማሪዎች በwww.ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.org. ላይ ያለውን ስልጠና ማጠናቀቅ አለባቸው።

እንደ ተለዋጭ አስተማሪም ቢሆን ወጣቶች በመጀመሪያ ደረጃ ክፍል ማስተማር የለባቸውም።

የመጀመሪያ ደረጃ ክፍል አስተማሪዎች እና የጨቅላ ህጻናት መሪዎች የመዝሙር ጊዜን እና የሽግግር ጊዜን ጨምሮ በሁሉም ጊዜ ከልጆቹ ጋር ይሆናሉ። በመዝሙር ሰዓት አስተማሪዎች ከተማሪዎቹ ጋር ይሳተፋሉ። አስተማሪዎች የመጀመሪያ ክፍል ፕሮግራም ካለቀ በኋላ ከቤተሰባቸው አባላት አንዳቸው እስኪመጡ ድረስ ከህጻናት ልጆች ጋር ይሆናሉ።

አትም