2022 (እ.አ.አ)
የነፍስ ዋጋ
የካቲት 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

የነፍስ ዋጋ

ወንጌልን በማካፈል መስጠት በእውነት መባረክ ነው።

ልጅ እያለሁ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ባላቸው ወንጌልን በቀላሉ እና በብቃት የማካፈል ችሎታ ሁልጊዜ እማረክ ነበር። በኋላም ከእነርሱ እንደ አንዱ ስሆን የግል ምስክርነት ኃይል ተሞክሮ አገኘሁ፤ እናም በዚህ ታላቅ ሥራ የተሰሩ ተዓምራትን አየሁ። ነገር ግን በርግጠኝነት ይህ ተሞክሮ በጣም ጥልቅ የሚሆነው ከወላጆቼ እንዲሁም ከወንድሞቼ እና ከእህቶቼ ጋር በቤት ውስጥ ስሆን ነበር እላለሁ።

በህይወት ዘመኑ አባቴ ከጌታ ጋር ልዩ ዝምድና ነበረው። እናም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በመሪነት፣ በሴሚነሪ እና ኢንስቲትዩት አስተማሪነት በማገልገሉ ወንጌልን እንዴት ማካፈል እንደሚቻል ልምድ አግኝቷል። ጎረቤቶችን ወደኛ ቤተሰብ የቤት ምሽቶች እና ወደሌሎች እንቅስቃሴዎች እንደመጋበዝ ያሉ ተግባራትን እና/ወይም ልምዶችን መስርቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። እንዲሁም በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ወቅት ወንጌልን ሲያካፍል እና ምስክርነቱን ሲሰጥ ይሰማ ነበር። በእርሱ አርአያነት በመነሳሳት የእኛ ህይወት ዘይቤ ሆነ። ብዙ ጊዜ በሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን በመታገዝ ዛሬም ድረስ የቤተክርስቲያኗ አባላት በሆኑ አንዳንድ ልጆቹ የመለወጥ ሂደት ላይ በጌታ እጅ መሣሪያዎች ሆነናል።

የአገልግሎትን እጹብ ድንቅነት ከቀላልነቱ ጋር የበለጠ ለመረዳት እንድችል የረዱኝን እነዚህን ልምዶች እወዳቸዋለሁ። በዚህም በት እና ቃ 18፥10፣ 15 ውስጥ የተካተቱትን “የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሆነ አስታውሱ”፣ “እናም በቀኖቻችሁ ሁሉ ንስሃን ወደ እነዚህ ህዝብ በመጮህ ብታገለግሉ እናም አንድም ነፍስ ቢሆን እንኳን ወደእኔ ዘንድ ብታመጡ በአባቴ መንግስት ከእርሱ ጋር ደስታችሁ እንዴት ታላቅ ይሆናል!” የሚሉትን ጥበብ የተሞሉ ትምህርቶች ተግባራዊ በማድረግ የነፍስን ዋጋ ዕውቀት አግኝቻለሁ። ስለዚህም ጳውሎስ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነው” ባለ ጊዜ የተሰማውን ስሜት የተሻለ እንደተረዳሁት ማረጋገጥ እችላለሁ”1

የግል እና ጥልቅ ከሆኑ ተሞክሮዎች በመነሳት ወንጌልን እስከ ምድር ዳርቻ (ለምሳሌ ከመንገድ ማዶ ላለው ጎረቤት ማድረስ) በሕይወታችን እና በቤተሰባችን አባላት ሕይወት ውስጥ ብዙ በረከቶችን እንደሚያመጣ አውቃለሁ። ከዚህ በመነሳት ፍሬውን ከበላ በኋላ ቤተሰቡ እና ሌሎችም መብላት እንዳለባቸው መፈለግ የጀመረውን የሌሂን ስሜቶች የተሻለ መረዳት እንችላለን። “Oh, There’s One who smiles on high” በሚለው በመዝሙር 294 ቃላት ውስጥ በጣም በሚያምር ሁኔታ እንደተገለፀው ይህንን ግዴታ በቁርጠኝነት፣ በታማኝነት እና በፍቅር እንወጣ” በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

ማስታወሻዎች

  1. የሃዋርያት ስራ 20:35 ይመልከቱ።

አትም