የቃልኪዳን መንገዴ
ብርሃኑን አጋሩ
ወንጌልን ለቤተሰብ አባላት ለማካፈል ደፋሮች እንሁን።
ደፋር ሁኑ! ወንጌልን ከመመስከር፣ ትክክለኛውን ከመምረጥ፣ ለእውነት ከመቆም፣ የደግነት ተግባራትን ከማድረግ እና ሌሎችን ከማገልገል አንጻር እነዚህን ቃላት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እናነባቸዋለን? ብርሃኑን በማጋራት ረገድ ደፋሮች ነን? አይቀበሉንም ብለን በመስጋት ለቤተሰብ አባላት ለማካፈል እናመነታለን?
የሌሂን የህይወት ዛፍ ራዕይ ታስታውሳላችሁ? “ከዚህች ፍሬ ስካፈልም ይህም ነፍሴን በደስታ ሞላው፣ ስለሆነም ቤተሰቦቼም ደግሞ ይካፈሉት ዘንድ መመኘት ጀመርኩ፤ ከሌላው ፍሬ ሁሉ በላይ አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁና።”1 የደህንነት አቅዱ ምን ያህል ውድ እንደሆነ እንዳወቀ ወዲያውኑ ሊያካፍል ፈለገ—እናም ደፋር ለመሆን አልፈራም። ላማን እና ልሙኤል ሁልጊዜ እንደማይቀበሉ ያውቅ ነበር ሆኖም ለእነርሱ ካለው ታላቅ ፍቅር የተነሳ አካፈለ።
የዛሬ ሃምሳ አመት ወጣት የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ አንድ አባል የነበረች ጓደኛዬ ደፋር ነበረች። በቀጥታ ‘ወርቃማ ጥያቄዎችን’ ጠየቀችኝ፦ “ስለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ምን ታውቂያለሽ?” “የበለጠ ለማወቅ ትፈልጊያለሽ?” የበለጠ በተማርኩኝ፣ የበለጠ በተረዳሁኝ እና የወንጌል ምስክርነት ባገኘሁኝ ጊዜ ለቤተሰቦቼ ማካፈል ፈለኩኝ—ምንም እንኳን ብዙዎቹ ላይቀበሉ የሚችሉ እንደሆነ ባውቅም። እናም በእርግጥም አልተቀበሉም! ነገር ግን ደፋር የመሆን ፍላጎቴ ጠንካራ ነው። “ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ” በድፍረት ነገር ግን በእርጋታ ልጋብዛቸው የምችልባቸውን መንገዶች ያለማቋረጥ አስባለሁ።
ምናልባት እነዚህን ጥቆማዎች ግምት ውስጥ ልናስገባ እንችላለን፦
ቃላቶቻችን እና ተግባራቶቻችን ማንነታችንን ያንጸባርቃሉ። “በተግባር እና በአስተሳሰብ ገር እና አፍቃሪ ሁኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው እነዚህን ነውና።”2
ደስታ እና ተግዳሮቶች በሚያጋጥሟቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ፍቅር፣ ድጋፍ እና በእነርሱ ላይ ያላችሁን መተማመን ግለጹ። ስናየው በቀስታ ወደጌታ እጅ እንጠቁም እንዲያውቁትም እንርዳቸው።
ጸሎትን እና የቅዱሳን ጽሁፎችን ጥናት በተመለከተ መልካም አርዓያ ሁኑ። በቤተሰቦቻችን ውስጥ ካሉ ግንኙነቶች እና ተሞክሮዎች ጋር ስለሚያያዙ ያሉንን መልካም ሀሳቦች እና ተነሳሽነቶች እናጋራ።
በፍቅር እና በደስታ እናገልግላቸው። እንዲሁም “በጣም አስተዋይ እና ረዳት የሆናችሁት ለምንድን ነው?” ብለው ቢጠይቁን በትህትና “የበለጠ ክርስቶስን ለመምሰል እና የእርሱን ምሳሌ ለመከተል እየጣርን እንደሆነ” መናገር እንችላለን።
እና የወንጌል ጥያቄዎች ሲመጡ፣ እነዚያን መርሆዎች ለማካፈል እና ‘ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ’ ለመጋበዝ አንፍራ።
የሌሂን ምሳሌ እንከተል፦ በምስጋና፣ በፍቅር እና በደስታ ሁላችንም “ደፋር እንሁን!” ብርሃኑን ለማጋራት በየቀኑ ብዙ መልካም አጋጣሚዎች አሉ።