የአካባቢ አመራር መልዕክት
ወንጌልን አካፍሉ
ወንጌልን ማካፈል ዛሬ በምድር ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስራ አካል ነው፣ ይሁንና መውደድን፣ ማካፈልን እና መጋበዝን እንደመማር ቀላል ነው።
ወንጌል ማለት “መልካም ዜና” ማለት ነው። መልካም ዜናው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ዘር ከመቃብር ሁላችንንም የሚያድነን እና እያንዳንዱ ግለሰብን እንደ ስራው ወይም ስራዋ የሚሸልም ፍፁም የሆነን የሃጢያት ክፍያ ማድረጉ ነው።
በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት በአዳኙ የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያለመሞትን እና የዘላለም ሕይወትን በረከቶች ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ያመጣል። ወንጌል ብቻ ነው ይሄን ለማድረግ አቅም ያለው።
በሕይወት ዛፍ ራዕይ ላይ ፍሬው አንድን ሰው ሊያስደስት የሚችል ዛፍን እንዳየ ሌሂ ተናገረ። ፍሬው እጅግ በጣም በሆነ ደስታ መንፈሱን ሞላው። የሕይወት ዛፉ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና የክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ እንደሚወክል ኔፊ ተማረ፦ “የሕይወት ዛፉ … የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።”1 እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን ፍቅር የሚገልፀው ኢየሱስን እንደ ቤዛችን በመስጠቱ ነው፦ “እግዚአብሔር አለምን ከመውደዱ የተነሳ አንድያ ልጁን እንዲሁ አሳልፎ ሰጠ።”2
ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ ማለትም በሁሉም ሰዓት እና በሁሉም ቦታ እንደ የእግዚአብሔር ምስክር መቆም የጥምቀት ቃልኪዳናችን አካል ነው ። አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን አለ፣ በነፃ የተቀበላችሁትን በነፃ ስጡ።3 ሁሉንም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል “ጥቁር እና ነጭ፣ ምርኮኞች እና ነፃ የወጡ፣ ወንዶች እና ሴቶች።”4 እግዚአብሔር ሁላችንንም እኩል ይወደናል እና በረከቶቹ ለአንድ ቡድን ሳይሆን ለሁሉም ልጆቹ ነው። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እያንዳንዱ የሰማይ አባት ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ለመምረጥ እና ወንጌሉን ከመላ በረከቶቹ ለመቀበል እድል እንደሚገባው አስተማሩ። ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች እውነትን መማር፣ ወደ እግዚአብሔር መመለስ እና ለሃጢያታቸው ይቅርታን መቀበል ይፈልጋሉ።
1. እግዚአብሔርን እንዲሁም ሌሎችን ስለምንወድ ወንጌልን እናካፍል
ፍቅር የሚለው ቃል በ1ኛ ዮሐንስ 4 ውስጥ ከ20 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። ዮሐንስ እንዲህ አስተማረ፣ “ፍቅር እግዚአብሔር ነው” “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” እና የእግዚአብሔር ፍቅር በአንድያው ልጁ ስጦታው አማካኝነት ተገል ጿል።5
ለእግዚአብሔር ፍቅር የምናሳይበት መንገድ ሌሎችን በመውደድ እና በማገልገል ነው።6 ሌሎችን ለመውደድ እና ለማገልገል ስንጥር የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ እንከተላለን። ሌሎችን ስንወድ እና ስናገለግል ንጉሥ ቢንያም ያንን “ጥበብ” ብሎ ይጠራዋል። ይህ ፍቅር ወደ ሁሉም ኃይማኖቶች፣ ዘሮች እና ባህሎች እንድንዞር የሚያነሳሳን ማበረታቻ ነው።7
2. ሌሎችን ሳንፈርድባቸው ወንጌልን ማካፈል እንችላለን
የሞዛያ ልጆች “ማንኛውም የሰው ነፍስ … መጨረሻ የሌለውን ቅጣት መቀበል … እንዲንዘፈዘፉ እና እንዲንቀጠቀጡ አድርጓቸዋል።8 ወደ ጌታ ሲለወጡ፣ ልቦቻቸው ለሌሎች በርህራሄ ተሞልቶ ነበር እና የተቀበሉትን የማካፈል ፍላጎታቸው ጥያቄ የለውም ነበር። ስለላማናውያን ማንነት አልፈረዱባቸውም ነበር፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች የመሆን ብቃትን በሌሎች ላይ ይመለከቱ ነበር። የወንጌልን እውነታዎች በመኖር የምናገኘውን ደስታ ለጓደኞች እና ለሌሎች ማሳየት እንችላለን። ይህን በማድረግ ለዓለም ብርሃን እንሆናለን።9 አባል ላልሆኑ ጓደኞች እና ለሌሎች በአካል፣ በፅሁፍ መልዕክት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ወንጌልን መግለፅ እንችላለን።
ወንጌልን ለማካፈል ፍላጎቱ ካለን እና ለምሪት ከጸለይን የሰማይ አባታችን ይረዳናል። በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር ወንጌልን ለመካፈል መንገዶችን እንድናገኝ ይረዳናል።
3. በተለመደ እና ተፈጥሮአዊ በሆኑ መንገዶች ሌሎችን ጋብዙ
ሌሎች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ ለመጋበዝ ባለሞያ መሆን አይጠበቅብንም። ይህን ለማድረግ፣ ከቀን ተቀን የበጎ ተግባራት አንስቶ በዩቱብ፣ በፌስ ቡክ፣ በኢንስታግራም ወይም በትዊተር እስከሚደረጉ ግላዊ ምስክርነቶች እንዲሁም ከምታገ ኟቸው ሰዎች ጋር እስከምታደርጓቸው ቀላል ንግግሮች ብዙ የተለመዱ እና ተፈጥሮአዊ መንገዶች አሉ።
እያንዳንዳችን ጓደኞቻችንን፣ ጎረቤቶቻችንን እና የስራ ባልደረቦቻችንን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ለመጋበዝ ብዙ እድሎች አሉን። ይህን ሁሉ የምናደርግ ከሆነ፣ ልክ እንደሐዋርያው ጳውሎስ “በወንጌል አላፍርምና ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።”10 ማለት እንችላለን።
በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በወንጌሉ እና በቤተክርስቲያኑ አማካኝነት የሚገኙትን በረከቶች መጥተው እንዲመለከቱ መጋበዝ እንችላለን።11 ኑ እና ሰዎችን እንድናገለግል አግዙን፣ ኑ እና የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ሁኑ።
ግብዣዎቻችን በሰው መሻት እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን እሱ ወይም እሷ እነዚያን ግብዣዎች ይቀበላሉ። ብዙ ጊዜ መጋበዝ ማለት ቤተሰባችንን፣ ጓደኞቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን በምናደርገው ነገር ላይ ማካተት ማለት ነው። አዳኙ ሁሉም ወንጌሉን እንዲቀበሉ እና ለዘላለም ሕይወት እንዲዘጋጁ ይጋብዛል።12
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት እህት ሙቶምቦ እና እኔ በቤተሰብ ምሽታችን ላይ አባል ላልሆኑ ጓደኞቻችን እና ጎረቤቶቻችን ወንጌልን እንዴት ማካፈል እንደምንችል ተወያየን። ማንን መቅረብ እንደሚገባን እንዲሁም ጓደኞቻችንን እንዴት መቅረብ እንደምንችል ለማወቅ ጌታ መነሳሳት እና ምሪት እንዲሰጠን ጸለይን። ከሳምንት በኋላ በቤተሰብ የቤት ምሽታችን ላይ ጆን ብዬ የምጠራውን አንድ ጎረቤታችንን ለመጋበዝ ወሰንን። የቤተሰብ የቤት ምሽታችንን ከተካፈለ በኋላ ጎረቤታችን በመገረም እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን አብሮን መሄድ ይችል ዘንድ ጠየቀ። ምንም እንኳን ከቤተሰቦቹ ተቃውሞ ቢገጥመውም የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን አብሮን ተሳተፈ። ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ጆን ከሚሲዮናውያን ጋር እንዲገናኝ ያቀረብንለትን ግብዣ ተቀበለና በሚሲዮናውያን አማካኝነት በቤታችን ውስጥ ተማረ።
የጆን ባለቤትም ከባሏ ጋር ትምህርቱን ለመካፈል ስትወስን ተአምር ተከሰተ። የረጅም ጉዞ መጀመሪያ ነበር ምክንያቱም ጆን እውነታዎችን ለራሱ ለማወቅ ስለፈለገ። ጥምቀትን ለመቀበል ጆንን እና ባለቤቱን ከሶስት ወራት በላይ ፈጀባቸው። ወደ ክርስቶስ ተለወጡ እና የተመለሰችውን ቤተክርስቲያኑን ለመቀላቀል መረጡ። ጆን በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ ሲመላለስ ስናይ ልባችን ሁሌም በደስታ ይሞላል።
ልምዳችሁ ከእኛ የተለየ ሊሆን ይችላል። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መልካም ዜና ስታካፍሉ በፍቅር እና በትዕግስት አድርጉት። በቅርብ ለመጠመቅ ነጭ ልብስ እንዲለብሱ ብለን በማሰብ ብቻ ከሌሎች ጋር መስተጋብር መፍጠር የለብንም። መጥተው የሚያዩ ሰዎች ምናልባት ቤተክርስቲያኗን ላይቀላቀሉ ይችላሉ፤ የተወሰኑት በሌላ ጊዜ ሊቀላቀሉ ይችላሉ። ያ የእነሱ ምርጫ ነው። ነገር ግን ለእነሱ ያለንን ፍቅር አይቀይርም። ግለሰቦች እና ቤተሰቦች መጥተው እንዲያዩ፣ መጥተው እንዲያግዙ እና መጥተው እንዲቀላቀሉ የመጋበዝ ቀጣይነት ያለው ሙከራን አይቀይርም። ጠቃሚው ነገር ተስፋ አለመቁረጣችሁ ነው፤ ለማስተካከል በምታደርጉት ሙከራ ቀጥሉ። እውነት እንደሆኑ የምታውቋቸውን ነገሮች ለሌሎች ለማካፈል ባላችሁ የቀን ተቀን ፍላጎታችሁ ምክንያት የበለጠ ደስተኛ እንደምትሆኑ ቃል እገባላችኋለሁ።
4. ከጌታ ቃል የተገቡ በረከቶች
ወንጌልን ለሚያካፍሉ ሰዎች ጌታ እንደዚህ ሲል ቃል ገብቷል “የተባረካችሁ ናችሁ የሰጣችሁት ምስክርነት መላዕክት እንዲመለከቱት በሰማይ ተመዝግቧልና እናም በእናንተም ተደስተዋል።”13
ውድ ወንድሞች እና እህቶች እውነትን የሚፈልግን ሰው፣ ለነፍስ ጥያቄዎች መልስን የሚሻን ሰው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የሚፈልግን ሰው በመንገዳችሁ ላይ ጌታ እንዲያስቀምጥ እንድትጸልዩ እጋብዛችኋለሁ። አዳኙ እንዲህ አስተማረ፣ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ …
“እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ …
“በጎቹ ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል።”14
ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ አሉ፣ “ማንኛውንም ሰው የሚረዳ ነገርን ስናደርግ … ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳኖችን እንዲገቡ እና እንዲጠብቁ ስናደርግ፣ እስራኤልን ለመሰብሰብ እየረዳን ነው።”15
ወንጌልን ማካፈል ዛሬ በምድር ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስራ አካል ነው፣ ይሁንና መውደድን፣ ማካፈልን እና መጋበዝን እንደመማር ቀላል ነው። በምንኖርበት ቦታ ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መልካም ዜና ለማካፈል እድሎች አሉን።
ቲየሪ ኬ. ሙቶምቦ እንደ አጠቃላይ ሰባ ባለስልጣን የተሾሙት በሚያዚያ 2020 (እ.አ.አ) ነበር። ከፅሃዪ ናታሊ ሲንዳ ጋር ትዳራቸውን መስርተዋል፤ የስድስት ልጆችም ወላጆች ናቸው።