2022 (እ.አ.አ)
ቃል ኪዳኖች ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኙናል
የካቲት 2022 (እ.አ.አ)


“ቃል ኪዳኖች ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኙናል፣” ሊያሆና፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)

ቃል ኪዳኖች ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኙናል

ቃል ኪዳኖችን መግባት እናም ማክበር በረከቶችን ያመጣሉ

ቃል ኪዳን በእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል ያለ ስምምነት ነው። ከእርሱ ጋር ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ሁኔታዎችን ያዘጋጃል። እርሱ የጠየቀውን ስናደርግ፣ እኛም ብዙ በረከቶችን እናገኛለን። እናም በረከቶችን የምናገኘው በምድር ላይ ብቻ አይደለም—ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ ከእግዚአብሔር እና ከቤተሰባችን ጋር በሰማይ ለመኖር አንድ ቀን እንመለሳለን።

ምስል
ጥምቀት

ቃል ኪዳኖች እና ስነ-ስርዓቶች

በአንዳንድ ስነ-ስርዓቶች ጊዜ ቃል ኪዳኖችን እንገባለን። ተመልሰን ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እነዚያን ስነ-ስርዓቶች መቀበል እና እነዚያን ቃል ኪዳኖች ማክበር ያስፈልገናል። እነዚህ ስነ-ስርዓቶች የሚፈጸሙት በክህነት ስልጣን ነው። እነዚያ ስነ-ስርዓቶችም ጥምቀትንና መረጋገጥን፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መቀበልን (ለወንዶች)፣ እና በቤተመቅደስ ውስጥ የምንቀበላቸውን ስርዓቶች ያካትታሉ። በቅዱስ ቁርባን ላይ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች ያድሳሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ይመልከቱ)።

ምስል
ቅዱስ ቁርባን

ቃል ኪዳኖች በጻድቅነት እንድንኖር ይረዱናል

በጥምቀት ጊዜ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል፣ እርሱን ሁልጊዜ ለማስታወስ፣ እና ትእዛዛትን ለማክበር ቃል እንገባለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37 ይመልከቱ)። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር እንደሚገኝ ቃል ይገባል።

ሰዎች ክህነትን ሲቀበሉ፣ ለእግዚአብሔር ክህነት ሀይል ብቁ ለመሆን ቃል ይገባሉ። እግዚአብሔርም እንደሚባርካቸው ቃል ይገባል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥33–40 ይመልከቱ።)

ምስል
የብራዚል ረሲፌ ቤተመቅደስ

የብራዚል ረሲፌ ቤተመቅደስ ስዕል በጄምስ ፖርተር

በቤተመቅደስ ውስጥ የምንገባቸው ቃል ኪዳኖች

የቤተክርስቲያኗ አባላት በቤተመቅደስ ውስጥ መንፈሳዊ ስጦታቸውን ሲቀበሉ፣ በጻድቅነት ለመኖር እና ለወንጌሉ መስዋዕት ለማድረግ ቃል ይገባሉ። እነርሱም ከእግዚአብሔር ሀይል እንደሚሰጣቸው ቃል ይገባላቸዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥32109፥22 ይመልከቱ)።

በቤተመቅደስ ውስጥ በሚታተሙበት ጊዜ፣ ባል እና ሚሰት ለዘለአለም ይጋባሉ እና፣ እርስ በእርስ እና ለእግዚአብሔር ታመኝ እንዲሆኑ ቃል ይገባሉ። እግዚአብሔርም ወደ እርሱ እንደሚመለሱ እና እንደ ቤተሰቦች ለዘለአለም እንደሚኖሩ ቃል ይገባል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19–20 ይመልከቱ።)

ምስል
ወንጌል ሰባኪዎች

እኛ የቃል ኪዳን ህዝቦች ነን

እነዚያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የሚቀላቀሉት፣ የቃል ኪዳን ህዝቦች ይሆናሉ። እንዲሁም የአብርሐምን ቃል ኪዳን በረከቶች እና ኃላፊነቶች ይወርሳሉ (ገላትያ 3፥27–29 ይመልከቱ)። የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሰዎች አካል መሆን ማለት ወደ ክርስቶስ ስንቀርብ እርስ በርሳችን እንረዳዳለን። ደግሞም የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ለማጠናከር እንሰራለን ማለትም ነው። ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅ ከእግዚአብሔር ኃይል እና ብርታት እናገኛለን።

አትም