2022 (እ.አ.አ)
የካቲት 1998(እ.አ.አ)፦ የቤተመቅደስ ትንቢታዊ ተስፋ
የካቲት 2022 (እ.አ.አ)


የዚህ ወር በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

የካቲት 1998(እ.አ.አ)፦ የቤተመቅደስ ትንቢታዊ ተስፋ

ት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ (1910–2008) በናይሮቢ ኬንያ ውስጥ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በየካቲት 17፣ 1998 (እ.አ.አ) ደረሱ። በሆቴላቸው በታላቅ የጉባኤ አዳራሽ ውስጥ ከኢትዮጲያ፣ ከሶማሊያ፣ ከታንዛኒያ እና ከዩጋንዳ የተጓዙቱን ጨምሮ 900 ለሚሆኑ አባሎች ንግግር አደረጉ። አባሎች ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ የገንዘብ አቅም በሌላቸው አካባቢዎች፣ የሚሳተፉ ተወካዮችን ለመላክ እና ተመልሰው ልምዳቸውን ከእነሱ ጋር እንዲያካፍሉ ገንዘባቸው አዋጡ።

“የትም ይገኙ የትም በእግዚአብሔር ቅዱሳን መካከል ያደገ የፍቅር ሃያል ትስስር ነበረ፣” አሉ ፕሬዚዳንት ሂንክሊ በንግግራቸው ውስጥ። “ግሩም እና ድንቅ ነገር ነው። ፊታችሁን ስመለከት፣ በሶልት ሌክ ታበርናክል ውስጥ ያሉትን ሰዎች ፊት ስመለከት የማገኘውን ተመሳሳይ የፍቅር ትስስርን ማየት እችላለሁ። ሁላችንም የዚህ ታላቅ ቤተሰብ—የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባሎች ነን።”

ፕሬዚዳንት ሂንክሊ እንዲህም አሉ፦ “በእምነት እና በትዕግስት የምንጓዝ ከሆነ በዚህ መሬት ላይ የዚህን ህዝብ ፍላጎት ለማገልገል ቤተመቅደስ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ ጥርጣሬ በአእምሮዬ ውስጥ የለም። በተወሰኑ ዓመታት ውስጥ ይሆናል ብላችሁ አሁን እንዳትገምቱ፣ … ነገር ግን ይሆናል።”

ቅዳሜ 11 ቀን ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)፣ የኬንያ ናይሮቢ ቤተመቅደስ መሬት ለስራ ተጀመረ። የአካባቢ ፕሬዚዳንት እና የቀድሞ የቤተክርቲያኗ አባል የሆኑት ሽማግሌ ጆሴፍ ደብሊው. ሲታቲ ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን የቤተመቅደስ መሬት ባረኩ። የፕሬዚዳንት ሂንክሊ የኬንያ የቤተመቅደስ ትንቢት አሁን እውን ሆነ።

አትም