2022 (እ.አ.አ)
በማዕበሎች ውስጥ መረጋጋት
ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)


“በማዕበሎች ውስጥ መረጋጋት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)

በማዕበሎች ውስጥ መረጋጋት

ምንባቦች

ባህር ማማ

ለራሳችን እና ለምንወዳቸው ሰዎች የምንጨነቀው፣ ከፊት ባሉት ማዕበሎች ውስጥ የደህንነት ቦታ እንዳሉ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል ላይ ተስፋ አለ። …

የንጉሥ ቢንያም ትንቢታዊ ቃላት በእኛ ዘመን ተግባራዊ ናቸው። …

አዳኝ በሆነው ብቸኛው አስተማማኝ የደኅንነት ዓለት ላይ እንድንገነባ ህዝቡንና እኛን ጋብዞናል። ትክክልና ስህተት የሆነውን የመምረጥ ነፃነት እንዳለን እንዲሁም ምርጫችን ከሚያስከትላቸው መዘዞች መራቅ እንደማንችል ግልጽ አድርጓል። …

ተፈጥሮአችን እንደ ትንሽ ልጅ፣ ለእግዚአብሔር ታዛዥ እና የበለጠ አፍቃሪ ለመሆን ይቀየራል። ያም ለውጥ በመንፈስ ቅዱስ በኩል በሚመጡት ስጦታዎች እንድንደሰት ብቁ እንድንሆን ያደርገናል። የመንፈስ ወዳጅነት ማግኘታችን ያጽናናል፣ ይመራናል እና ያበረታናል።

የህይወት ማዕበሎች ሲመጡ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን የእምነት ዓለት ላይ ስለቆምን መረጋጋት እንችላለን። ያም እምነት ወደ ዕለታዊ ንስሐ እና በዘወትር ቃል ኪዳንን ወደማክበር ይመራችኋል። ከዚያም እርሱን ሁልጊዜ ታስታውሳላችሁ። እናም በጥላቻ እና በክፋት ማዕበል ውስጥ፣ የተረጋጋ እና ተስፋ ይሰማችኋል።

… እንደ ትሁት እና አፍቃሪ ልጅ፣ የእርሱን እርዳታ ተቀበሉ። በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያቀርባቸውን ቃል ኪዳኖች ፈጽሙ እና ጠብቁ። እነርሱም ያጠነክሯችኋል። አዳኝ ወደ እርሱ እና ወደ የሰማይ አባታችን በሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ማዕበሎችን እና የደህንነት ቦታዎችን ያውቃል። እርሱ መንገዱን ያውቀዋል። እርሱ መንገዱ ነውና።