“በአባታችን እቅድ ውስጥ ያለው መለኮታዊ ፍቅር፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)
ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)
በአባታችን እቅድ ውስጥ ያለው መለኮታዊ ፍቅር
ምንባብ
ዳግም በተመለሰችው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ የሰማይ አባታችን እቅድ ልዩ የሆነ አረዳድ አለን። ይህ የሟችነት ህይወት አላማን፣ ከእርሱ የሚከተለውን መለኮታዊ ፍርድ፣ እናም የሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች የመጨረሻውን የክብር እጣ ፈንታ የምንመለከትበትን ለየት ያለ እይታ ይሰጠናል። …
… ዳግም በተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኩል የተገለጠው አስተምሮት ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች—በዚህ ጊዜ በግምት ውስጥ በማንከታቸው ጥቂቶች በስተቀር—በስተመጨረሻ በክብር ደረጃ ውስጥ እንደሚገቡ ያስተምራል። …
… ከእነዚህ ትልቁም እንደአባታችን እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ የምንሆንበት በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍ መደረግ ነው። …
… ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን አላማ ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር ለሚፈልገው የመጨረሻ እጣፈንታቸውን ብቁ እንዲሆኑ መርዳት ነው። …
ለእኛ መሰረታዊ የሆነው ከፍ መደረግ ሊገኝ የሚችለው በወንድ እና በሴት መሀል ባለው ለዘለአለማዊ ጋብቻ ቃል ኪዳኖች ታማኝ በመሆን ብቻ እንደሆነ የሚገልጸው የእግዚአብሔር ራእይ ነው። ይህ መለኮታዊ አስተምሮ “ጾታ አስፈላጊ የሆነ የግለሰብ ቅድመ ህይወት፣ ሟች እና ዘለአለማዊ መለያ እና አላማ እና ባህሪ ነው” ብለን የምናሰተምርበት ምክንያት ነው [“ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ChurchofJesusChrist.org]። …
… እኛ በማይሻር አስተምሮ ላይ የተመሰረተው የቤተሰብ አዋጅ የዘለአለማዊ እድገታችን ዋናው አስፈላጊ ክፍል ለሚካሄድ የሚችበት የቤተሰብ ግንኙነቶችን አይነትን እንደገለጸም እናረጋግጣለን። …
… እነዚህን ዘለአለማዊ እውነቶች ለሌሎች ለማካፈል መሻት አለብን። ነገር ግን ከሁሉም ባልንጀሮቻችን ባለን የፍቅር እዳ፣ እኛም ሁሌ ውሳኔዎቻቸውን እንቀበላለን። የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ እንዳስተማረው፣ “የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር” እየኖረን ወደፊት መቀጠል አለብን [2 ኔፊ 31፥20]።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Printed in USA. እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የMonthly Liahona Message, May 2022 ትርጉም። Amharic። 18351 506