“ሩት እና ኑኃሚን፣” ወርሀዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)
“ሩት እና ኑኃሚን”
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)
ሩት እና ኑኃሚን
ኑኃሚን እና ቤተሰቧ በድርቅ ምክንያት ወደአዲስ አገር መጡ። ሩት ከተባለች ወጣት ጋር ተገናኙ። ሩት የኑኃሚንን ወንድ ልጅ አገባች።
ከዚያም የሩት ባለቤት ሞተ። ሩት በጣም አዘነች።
ኑኃሚንም በጣም አዘነች። የሚንከባከባት አንድም የቀራት ቤተሰብ አልነበራትም። ወደመጣችበት አገር ተመልሳ ለመሄድ ወሰነች፡፡
ኑኃሚን ወደ ቤተሰቧ እንድትመለስ ለሩት ነገረቻት። ነገር ግን ሩት ኑኃሚንን ትወዳት ነበር። ከኑኃሚን ጋር ለመምጣት እና እርሷን ለመንከባከብ ቃል ገባች።
ሩት እና ኑኃሚን ድሆች ነበሩ። ስለዚህ ሩት ምግባቸውን ለማግኘት ጠንክራ ትሰራ ነበር።
አንድ ቀን ቦዔዝ የተባለ ሰው ከእርሻዎቹ በአንዱ የተራረፈ እህል ስትበስብ አያት።
ቦዔዝ ደግ ነበር። ተጨማሪ እህል ለሩት እንዲተው ለአገልጋዮቹ ነገራቸው።
በኋላም ሩት እና ቦዔዝ ተጋቡ። ወንድ ልጅም ወለዱ። ኑኃሚን ልጁን በመንከባከብ ረዳች።
ሌሎችን በመንከባከብ መርዳት እችላለሁ። ለተቸገሩ ደግ ለመሆን እችላለሁ።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Printed in USA. እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የMonthly Friend Message, June 2022 ትርጉም። Amharic። 18315 506