“ምረጡ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)።
ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)
ምረጡ
ኢያሱ ሕዝቡ ጌታን የመከተልን ትክክለኛ ምርጫ እንዲያደርግ አሳሰበ።
ምረጡ
ለመምረጥ እና በራሳችን ለመስራት ያለን ችሎታ ነጻ ምርጫ ይባላል። ይህም የሰማይ አባት እቅድ አስፈላጊ ክፍል ነው። የዚህ ህይወት አንዱ ዓላማ እንደእርሱ መሆን እንችል ዘንድ የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ለማክበር እንደምንመርጥ ማሳየት ነው። በምርጫዎቻችን መሰረት ይፈረድብናል። (2 ኔፊ 2፥27፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥78፤ አብርሃም 3፥25ን ተመልከቱ።)
ይህን ቀን
ኢያሱ፣ ሕዝቡ “ዛሬ፣” ወይንም አሁኑኑ እንዲመርጥ አሳሰበ። አንዴ አስፈላጊ ምርጫዎችን ማድረግ እንችላለን፤ ከዚያም በእነሱ ላይ ቁርጠኛ በመሆን ለመቀጠል እንሞክራለን። (መዝሙር 37፥5ን ተመልከቱ።)
አገልግሉ
በዚህ ጥቅስ መሰረት ማገልገል ማለት ማምለክ፣ መርዳት፣ ማክበር እንዲሁም ራሳችሁን ለሌላ ሰው አሳልፋችሁ መስጠት ነው። ጌታን ማገልገል ይኖርብናል (ሙሴ 1፥15ን ተመልከቱ)።
አማልክት
እስራኤል እውን እና ህያው እግዚአብሔርን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ብቻ እንዲያመልኩ ታዘው ነበር(ዘጸአት 20፥2–5ን ተመልከቱ)። ኢያሱ ህዝቡ ማምለክ የማይገባቸውን የሌሎች አማልክትን ምሳሌዎች ሰጠ። በህይወታችን ውስጥ ያሉ ሌሎች አማልክት ንብረቶችን፣ የሌሎች ሃሳቦችን፣ ሌሎች ፍላጎቶችን እንዲሁም ከጌታ የሚያርቀንን ማንኛውም ነገር ሊያካትቱ ይችላሉ።
እኔና ቤቴ
ኢያሱ እራሱን እና ቤተሰቡን ወክሎ ተናገረ። እነርሱም ጌታን እንደሚያገለግሉ ተናገረ። ቤተሰቡን በጽድቅ ለመምራት እና ጌታን እንዲከተሉ ለማስተማር ፈለገ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥40ን ተመልከቱ)፡፡
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Printed in USA. እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የMonthly For the Strength of Youth Message, June 2022 ትርጉም። Amharic። 18315 506