2022 (እ.አ.አ)
የመሰብሰቢያ አዳራሾች
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የመመሪያ መጽሐፍ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች

የመሰብሰቢያ አዳራሾች

የመሰብሰቢያ አዳራሾች እንደየአካባቢው ፍላጎቶች እና ሁኔታዎች በመጠን እና በአይነት ይለያያሉ። የመሰብሰቢያ አዳራሽ በቤተክርስቲያን የተሰራ ወይም የተገዛ ቦታ፣ የአባላት ቤት፣ የአካባቢ ትምህርት ቤት ወይም የማህበረሰብ ማእከል፣ በሊዝ የተያዘ ቦታ ወይም ሌላ የተፈቀደ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ማጽዳት እና መጠገን

የአካባቢው መሪዎች እና አባላት፣ ወጣቶችን ጨምሮ፣ እያንዳንዱን ህንፃ ፅዱ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲሆን የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው። ይህም ፦

  • የህንፃውን ቅዱስ ተፈጥሮ መንፈሱ የሚገኝበት ቦታ አድርገው ለመጠበቅ።

  • ጥልቅ ክብርን ለማበረታታት።

  • የክብር እና የአክብሮት ምስልን ለማቅረብ።

  • የህንፃውን አገልግሎት የመስጫ ዘመን ለማራዘም ይረዳል።

የጽዳት መርሃ ግብሩ በአባላቱ ላይ ሸክም መሆን የለበትም። ለምሳሌ፣ ወደ ህንፃው የሚደረግ ጉዞ ፈታኝ ከሆነ፣ አባላት በህንፃው ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ የሳምንታዊ ክንውኖች አካል አድርገው ማጽዳት ይችላሉ።